>

250 ባለስልጣናት ከአገር ውጭ እንዳይወጡ ፓስፖርታቸው ገቢ ተደርጎ የጉዞ እቀባ ተደርጎባቸዋል!!! …(ከድር እንድርያስ)

የአሜሪካ መንግስት አጋርነት በተግባር እየታየ ነው!!!

– ወደሱዳን ሊያመልጡ የነበሩ ትልቅ ባለስልጣን እንዲያዙ አድርጋለች!!!
 
– “አባይ ፀሀየ ከ4 ጋርዶች ጋር አሶሳ በሚገኘው ብላዴና ሆቴል የቁም እስር ላይ ነው!!
 
– 250 ባለስልጣናት ከአገር ውጭ እንዳይወጡ ፓስፖርታቸው ገቢ ተደርጎ የጉዞ እቀባ ተደርጎባቸዋል!!!
…ከድር እንድርያስ
አሜሪካ የምስራቅ አፍሪካን ፖለቲካ በዝምታ ማየትን አልወደደችም በተለይም ደግሞ የአንድ መቶ አስር ሚሊየን ህዝብ አገሩዋን ኢትዮጵያን ዳር ቆማ ማየትን አትሻም።
ከድብቅ ሚስጥር መረጃዎች እንደሚያሳዩት የዶ/ር አብይን ወደ ስልጣን መምጣት ከምር አሜሪካ ደግፋዋለች።
ይህ ብቻ አይደለም ሰሞኑን በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ የተቃጣውን የግድያ ሙከራ በአፅኖት ከመመልከት አልፋ የአለማችን ቁጥር አንድ አነፍንፎ መረጃን የሚያገኘውን ኤፍቢአይን ስለሂደቱ እንዲያጣራ ባስቸኩዋይ ልካለች።
በዚህ የተበሳጩትን የህወሀት ባለስልጣናት ሳይቀር በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመከታተል ላይ እንደሆነች እየተዘገበ ነው። አገሪቱን እናፈርሳለን ወይም ስልጣናችን ይመለስ በማለት ችግር እየፈጠሩ ያሉትን በቀጥታ ወጥመዱዋ ስር እያስገባቻቸው ሲሆን ከ250 በላይ የህወሀት ባለስልጣናት ከአገር እንዳይወጡ የአብይ መንግስት እንዲጠነቀቅ መክራለች። ይህ ብቻ አይደለም በወታደሩ ውስጥ ሴራን እያሴሩ ያሉትን በጥብቅ እየተከታተለች እንዳለችም ነው የተገለፀው ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ትዛዝ እያፈነገጡ ያሉ የሰራዊቱ አባላት በከፍተኛ መረብ ውስጥ ያሰገባቻቸው ሲሆን በቅርብ በአገር እና ህዝብ ክህደት እንዲነሱ የኢትዮጵያን ህዝብ እንደምታግዝ ነው የተነገረው። የደቡብ ኮሪያን የጦር ሰራዊት ባጭር ጊዜ በመደገፍ ታላቅ ጦር እንዲሆን የረዳችው አሜሪካ በወቅቱ ከህዝብ ተቃርኖ በመቆም አሻጥር የሰሩትን የደቡብ ኮሪያ ወታደሮች አንድ በአንድ በመልቀም የማፅዳት ስራን በመስራት ለደቡብ ኮሪካ እንዳደረገች የሚታወቅ ነው።
የመፈንቀለ መንግስት ፈፅሞ በኢትዮጵያ አይደለም መከሰት እንደማይታሰብ በሚገባ ባስተማማኝ ቀጥጥር ስር እንዳስገባችውና የኢትዮጵያ ህዝብ ከስጋት ውጭ እንዲሆንም መክራለች። አስቀድማ እጅግ ዘመናዊ የጦር አውሮፕላን በስጦታ የሰጠችው አሜሪካ የህወሀት ባለስልጠናት ከህዝባቸው ፍላጎት ጋር እንዲቆሙ በተለያየ መንገድ እያሳሰበች ነው። የትራምፕ አስተዳደር በአብይ ላይ የተቃጣው የመግደል ሙከራ የኢትዮጵያን ህዝብ መናቅ ነው በማለት ወርፎታል። ለዚህም አፋጣኝ የሆነ ምላሽ በመስጠት ላይ ያለችው አሜሪካ በዝምታ እንደማታልፍ ተናግራለች። የቻይና መንግስትም ይህ አሳፋሪ ተግባር ነው ከማለት አልፎ በቅርበት እየሰራበት እንዳለም ተገልፀዋል።
ይህ ብቻ አይደለም በአገሪቱ እየተፈጠሩ ያሉ የዘር ግጭቶችን እያባባሰ ያለውን ህወሀት እና አስፈፃሚ ሰወች አሜሪካ ከሳተላይት መረጃን በመስጠት ከ80 በላይ በደቡብ የተፈጠረው ግጭት ላይ ተሳትፈዋል የተባሉት ታድነው እንዲያዙ አርጋለች።
የወታደሩን ክፍልም በጥንቃቄ እያየችው ሲሆን በዶ/ር አብይ ላይ ያሴሩ አሉ ያለቻቸውን በቀጥታ እንዲነሱ በማድረግ የኢትዮጵያ ህዝብ መረጋጋቱ እንዲመጣ በጥብቅ እየተከታተለች እንዳለች የዜና አውታሮች እየዘገቡ ነው። ግጭት እና ብጥብጥ የሚፈጥሩት ሁሉ በራሳቸው ላይ የፈረዱ ናቸው በቅርብ የኢትዮጵያ ህዝብ ገመድ ውስጥ ያስገባቸው ዘንድ በከፍተኛ ድጋፍ ይታገዛልም ብለዋል።
አሜሪካ የኢትዮጵያን ሉአላዊ ሀገር ደፍራ መግባት አትፈልግም ፈፅሞም አታደርገውም ሆኖም የኢትዮጵያ ህዝብ የአብይን መመረጥ በሁሉም መልክ ደግፎታል የህዝቡን ደህንነት ለመጠበቅ የሚረዱ ስልጠናዎችን ለመስጠት እና የተፈፀመውን ችግር ምንጩን ለማወቅ ለማገዝ እና ዘመናዊ መሳሪያዎችን ለአገሪቱ ለመስጠት ብቻ ነው ኤፍ.ቢ.አይ የላከችው የሚል ትክክለኛ መረጃም ወጥቷል ሁሉ ነገር በኢትዮጵያ ህዝብ ሙሉ በሙሉ ሲያዝ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የአገሩ ባለቤት የኢትዮጵያ ህዝብ ስለሆነ ያኔ ድጋፍ ይቆማል ነው ያሉት።
የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያውያን ላይ በእየ እስር ቤቶቹ የተፈፀሙት ሰቆቃዎች በየትኛውም አለም ያልታዩ ሰቅጣጭ ናቸው ከማለትም አልፋ እነኝህን ግፍ ሰሪዎች አድና ለመያዝ የኢትዮጵያን ህዝብ እንደምትተባበር ከመግለፁዋም በላይ ለደህንነት ሲባል ወደ ኢትዮጵያ የገቡ እጅግ የዘመኑ ምስል ቪዲዮ እና ድምፅ ቀራጭ ዘመናዊ ጥቃቅን ሰላይ መሳሪያዎች በስራ ላይ እንዲውሉ ማድረጉዋን ገልፃለች ከዚህም በላም ከሳተላይት ሙሉ በሙሉ መረጃን መንግስት ያገኝ ዘንድ አክሰስ ሰጥቻለሁም ብላለች።
– በትናንትናው እለት ወደሱዳን ሊያመልጡ የነበሩ ከባድ ባለስልጣን እንዲያዙም አርጋለች።
– አባይ ፀሀዬም ከ4 ጋርዶች ጋር አሶሳ በሚገኘው ብላዴና ሆቴል የቁም እስር ላይ ነው!!
– 250 ባለስልጣናት ከአገር ውጭ እንዳይወጡ ፓስፖርታቸው ገቢ ተደርጎ የጉዞ እቀባ ተደርጎባቸዋል!!!
የጀርመን መንግስትም በከፍተኛ ሁኔታ የአውሮፓ ህብረት ትኩረት ሰቶ ይሰራ ዘንድ ግፊት እያሳደረች ሲሆን የአውሮፓ ህብረት ስብሰባ አድርጎ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈፅሙዋል ለጊዜው ለኢትዮጵያ ህዝብ ደህንነት ሲባል በመላ አገሪቱ የተፈፀመውን ነገሩ በመንግስት ደረጃ ብቻ እንዲቀመጥ እና  ሆኖም በህዝቡ ዘንድ ሳይቀር የሚታወቀው በአማራ ህዝብ ላይ ከፍተኛ የዘር ማጥፋት ወንጀል ከመፈፀሙም በላይ እነኝህ የዘር ማጥፋት ወንጀሎች በህክምና ሳይቀር ሆን ተብለው የተሰሩም ናቸው በሚል ትክክለኛ መረጃ እንዳለ እና ይህን ጉዳይ የአውሮፓ ህብረት በጥልቀት እየሰራበት እንዳለም ገልፀዋል። ከሶስት ሚሊዮን በላይ የአማራ ህዝብ በህክምና የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈፅሞበታል ስትል የገለፀች ሲሆን የአውሮፓ ህብረት አገራት ቁጥሩ ወደ አራት ሚሊዮን ይደርሳልም ነው ያሉት።
የፈረንሳይ መንግስት በበኩሉ ይህን ጉዳይ ከዚህ ቀደም ያሳሰበ ቢሆንም የህወሀት ባለስልጣናት ሆን ብለው ማፈን የመረጡ ቢሆንም መረጃውን በሙሉ ለመስጠት ፈቃዱዋን ገልፃለች።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የጠ/ሚ ዶ/ር አብይ ደህንነትን ባስተማማኝ ሁኔታ መጠበቅ አለበት ይህንም ለማድረግ ድጋፍ እንሰጣለን ያሉ በርካታ አገራት እያሳሰቡ ሲሆን በቅርብ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት ልኡሉ ሁለት ዘመናዊ ሄሊኮፍተሮችን እንደሚልኩ ተናግረዋል።
ከዚህ ባለፈ ከዶ/ር አብይ ተቃርኖ በመቆም የህዝብን ደህንነት የሚበጠብጡ ግለሰቦችን በአድራሻቸው ከያሉበት አገር እና ቦታ በመያዝ እንደምትሰጥ ቃል ገብታለች። በየትኛውም ቦታ እና ስፍራ በሶሻል ሚዲያም ሆነ በምንም መንገድ አያመልጡም በማለት የአሸባሪዎችን መረብ የሚበጣጥሰው ኤፍ.ቢ.ኣይ እንደማይለቃቸው ነው የተገለፀው። ከ160 በላይ ግለሰቦችም በዚህ መረብ ውስጥ ገብተዋል ነው የተባለው።
እስካሁን አራት ግለሰቦች በፌስቡክ መረጃ ተይዘው ምርመራ እየተደረገባቸው ሲሆን ቀጣይ ትልቅ ስራም እንሚሰራ ተናግረዋል።
ከዶ/ር አብይ እና ከህዝቡ ፍላጎት ውጭ የሆኑ ለውጡን የማይደግፉ ሽብር ፈጣሪዎችን አንድ በአንድ በመያዝ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጎን እንደምትቆም በውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱዋ በኩል ገልፃለች።
የትግራይ ህዝብም ከዶ/ር አብይ ጋር መቆም መጀመሩ ትልቅ ለውጥ ነው እሱም ነው የሚያዋጣው የትግራይ ህዝብ ከመላው የአገሪቱ ህዝብ ጋር ሆኖ ባገሩ ጉዳይ የለውጡ አካል ነውም ብለዋል።
ዶናልድ ትራምፕም ሙሉ ድጋፌ ለአብይ ነው ብለዋል።
ታላላቅ የአለም አገራት በፍጥነት በመደመር ላይ ናቸው።
Filed in: Amharic