ብአዴን ተናግቷል!!!
ቬሮኒካ መላኩ
ፓርቲው ውስጣዊ በሆነ አንደኛ ደረጃ ቅራኔ (Primary contaradiction ) ውስጥ ገብቶ አንዱ ሌላውን ደፍጥጦ ለመውጣት እየታገለ ነው። በአንድ በኩል እነ በረከት ስምኦን ፣ ህላዌ ዮሴፍ ፣ ገነት ገ/እግዚአብሄር የሚባሉ የሚመሩት በደምም በሰነልቡናም አማራ ያልሆኑ የአማራ ቀንደኛ ጠላቶች የተሰለፉ ሲሆን ።
በሌላ በኩል ደሞ ባለፉት አመታት የሚጠበቅባቸውን ስራ እንኳን ባይሰሩም የአማራ ህዝብ ህመም የሚያማቸው ፣ ቁስሉ የሚጠዘጥዛቸው እነ ደመቀ መኮንን ፣ ገዱ አንዳርጋቸውና ዶ/ር አምባቸው የመሳሰሉት ተሰልፈዋል ።
…
እርግጥ ብአዴን ብዙ ግፍ ያደረሰብን ድርጅት ቢሆንም አሁን ቁስላችንን የምናክበት ጊዜ አይደለም።
ይልቁንም በዚህ የውስጥ ሽኩቻ ፀረ አማራ የሆኑት እነ በረከት ስምኦን አሸንፈው እንዳይወጡ አይናችንንም ጆሮችንንም አንቅተን መጠበቅ አለብን። በዚህም መሰረት ማንኛውም የአማራ ወጣት ከእነ ገዱ አንዳርጋቸው ጎን እንድቆም ጥሪ አቀርባለሁኝ።