አዲሱ የፖለቲካ ጨዋታ – ስልታዊ የሆነ መደመር!!!
ቬሮኒካ መላኩ
አርከበ እቁባይና ደብረፂዮን ገ/ሚካኤል የሚመሩት የህውሃት ቲም ” ለስትራቴጅክና የምንጊዜም ጠላታችን አማራ ስንል የማኩረፉን ጊዜ አቁመን ስልታዊ የሆነ መደመር ያስፈልጋል ” በማለት ከአቢይ አህመድ ጋር ተደምረዋል ።
እነ ደብረፂዮን በተጨማሪም ” በወልቃይትና በራያ ጉዳይ በፍጥነት እያስገመገመ የመጣውን አደጋ ብቻችንን ተነጥለን መቋቋም የማንችልበት ደረጃ ደርሰናል ። በዚህም መሰረት ለጊዜው ተደምረን አሁንም ቢሆን በፌደራልም በክልሎችም ሰፊ መዋቅር ስላለን ቢያንስ እየመጣ ያለውን አደጋ እየተከላከልን ባለን መዋቅር ስልታዊና የተጠና ማጥቃት በመፈፀም የበፊቱን የበላይነታችንን ማስመለስ ይቻላል ” የሚል ጥናታዊ ፅሁፍ አቅርበው ተደምረዋል።
ጠ/ሚ አቢይ አህመድ እነ ደብረፂዮንን መደመር ከፖለቲካ አንፃር 5 ፐርሰንት ደምሮ ከ35% በላይ መቀነስ አጣብቂኝ ውስጥ እንደሚያስገባው አውቆ ለጊዜው በላይኛው ጥርሱ ፈገግ እያለ አርከበን በሄደበት ሁሉ እንደ ጅራት እያስከተለው ይገኛል ።
አሁን አማራ ከምንጊዜውም በላይ ስትራቴጅክ እና የተጠና ስልት የሚከተል አመራር ያስፈልገዋል።
