>

"..ልጄ ያ ሁሉ አልፎ በመንግስት ቴሌቪዥን አየሁህ.." እናቴ - ታማኝ በየነ 

“..ልጄ ያ ሁሉ አልፎ በመንግስት ቴሌቪዥን አየሁህ..” እናቴታማኝ በየነ 
ስለ ራሴ ለመጻፍ አስቤ ግብዝነት ይመስልብኛል ብዬ ትቸው ነብር ነገር ግን አናቴን ካናገርኳት በኋላ ያሉትን ይበሉ ብዬ ይችን ሃሳቤን ላካፍላችሁ ወሰንኩ።
አናቴን ደውዬ አንዴት ነሽ ስላት አሁንማ ምን አሆናለሁ አግዜብሄር አድሜየን አርዝሞ ቤት ውስጥ ቁጭ ብዬ በመንግስት ቴሌቪዥን አየውህ።ህዝቡ ፎቶህን ይዞ ሲያመሰግንህ ተመለከትኩ።ይባስ ብለው ምስልህን አንደ ሃውልት አሰርተው ተሸክመው ሲዞሩ ሳይ ማልቀስ ጀመርኩ ወዲያው ደግሞ ቤታችን በጩኽት ተደበላለቀ ምንድን ነው ስል የከተማው ወጣቶች ናቸው አሉኝና የሀገራችንን ሰንደቅአላም አልብሰውኝ ፎቶ ተነሳን ። ታዲያ ያን ሁሉ የጭንቅ ጊዜ አሳልፎ ይሄን ላሳየኝ አምላክ ምስጋና አንጅ ለቅሶ አይገባም ብዬ ማልቀስ አቆምኩ አለችኝ።አኔም አንግዲህ የአናቴን አንባ የአበሰ ይሄን ቀን አንዳይ አድሜ ለሰጠኝ አምላኬ ክብር ምስጋና ይድረሰው።
ይሄ ቀን አንዲመጣ ህይዎታቸውን ያጡ አካላቸው የጎደለ ቤተሰባቸው የተበተነ ቃላት የማይገልጸውን መከራ ስለ አኛ ሲሉ የተቀበሉ ብዙዎች ናቸው የነዚህን ሁሉ መስዋአትነት የምናስከብረው ያሰብነውጋ ስንደርስ ነውና በኢትዮጵያዊነታችን እንጽና ። በአዲስ አበባ ወልቂጤ ቡታጅራ ወልድያ ደብረታቦር ደብረብርሃን ባህርዳርና በሌሎችም ስማቸውን ባልጠራኋቼው ከተሞች የተካሄዱት ኢትዮጵይያዊነትን የማክበር ሰልፎች ያሳደረብኝ ስሜት በቃላት የማይገለጥ ነው። ከዚህ ታላቅ ሀገራዊ ጉዳይ ጋር አኔንም በቁም ነገር ስላሰባችሁኝ ከወገቤ ዝቅ ብዬ ምስጋና አቀርብላችኋለሁ።
ስለ ሁሉም ነገር አግዚአብሄር ይመስገን።
Filed in: Amharic