>
5:30 pm - Thursday November 1, 1364

የኦሮሞ የትግል አርማና የኢትዮጵያ ሀገራዊ ሰንደቅ አላማ (ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ ጂግሳ)

የኦሮሞ የትግል አርማና የኢትዮጵያ ሀገራዊ ሰንደቅአላማ
ከፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ ጂግሳ
ስለ ኦሮሞ የትግል አርማ እና የኢትዮጽያ ሀገራዊ ሰንደቅ አላማ ግንዛቤ ላይ ውዥንብር አለ። ነገሩን ሰፋ አድርገን ማየት ይገባናል።
ቄሮዎች ይዘው የሚወጡት የኦነግ የትግል አርማን ነው። እንደ ትግል አርማ ሊያዝ ይቻላል።ሆኖም ሀገር አቀፍ ሁሉንም ኢትዮጵያውያን የሚያካትት አንድ ሰንድቅ አላማ ያስፈልጋል።
የዛም ሰንደቅ አላማ ቀለሞች ለጊዜው አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ናቸው። ይህም ሰንደቅ አላማ የተፈለሰፈው የዛሬ 3300 ዐመት አካባቢ ነው።
 ፈልሳፊውም እስያን በስሙ ያስጠራው የኦሮሞ እና የመላው ኢትዮጵያእያን የዘር ግንድ የሆነው አጼ እስያኤል ነው። የሁላችንም አባት ነው። በነገራችን ላይ ይህ የኦነግ የትግል አርማ እንደ አርማነቱ እንኳን ለውይይት እና ለምርጫ ቀርቦ በሰፊው የኦሮሞ ህዝብ አልጸደቀም።
 እኔ አቋሜ በእዚህ ላይ ግልጽ ነው። ሰፊው የኦሮሞ ህዝብ ካጸደቀው እንደ ትግል አርማ በኦሮሚያ አስተዳድር ሊውለበለብ ይችላል። ከእሱ ጋር ደግሞ ሀገራዊው (national) ሰንደቅአላማ መሰቀል አለበት።
ለምሳሌ በየአንዳንዱ የአሜሪካ እስቴት የእስቴቱ መለያ አርማ ይውለበለባል. ከእሱ ጎን ለጎን ደግሞ የዩናይትድ ስቴት ሰንደቅአላማ ይሰቀላል። የመላውን ሀገር አርማ በመንግሥት ህንጻዎች ላይ መስቀል ግዴታ ነው።
የሁለቱ ነገሮች ልዩነት ግልጽ ቢሆንልን ጥሩ ነው።
በመጨረሻም የኦሮሞ ወጣቶችን የምመክረው ሰለትግላችሁ ከሚያውጀው አርማ በተጨማሪ  ለኢትዮጵያዊነታችሁም የሚመሰክረውን አረንጓዴ ቢጫ እና ቀዩን ሰንደቅአላማ ይዛችሁ ውጡ።
 ይህን ስታደርጉ ለእርሱ ሰንደቅ አላማ ክብር ከሚሰጡትና ደማቸውን ካፈሱሰለት ሌሎች ኢዮያጵያውያን (የኦሮሞ ስመጥር ጀግኖችን ጨምሮ) አንድነትና ፍቅር ይኖራችኋል። ኃይላችሁም ይጎለብታል። ለድልም ቶሎ ትቀርባላችሁ።
Filed in: Amharic