>

የትግራይ ክልል በራያ ህዝብ ላይ ዛሬ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጇል!!! (ደጀኔ አሰፋ)

የትግራይ ክልል በራያ ህዝብ ላይ ዛሬ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጇል!!!
ደጀኔ አሰፋ
በዛሬው እለት ሰኔ 30 ቀን 2010 ዓ.ም ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ የትግራይ ክልል ም/ቤት በራያ ህዝብ ላይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ  ማወጁን #በራያ_አላማጣ እና #በራያ_ዋጃ ላይ በሴኩሪቲ በታጀቡ መኪናዎች ላይ በተጫኑ ማይክራፎኖች  እየዞሩ አስታውቀዋል!! በዚህም መሰረት ወጣቶች ሶስት አራት ሆነው እንዳይንቀሳቀሱ ተከልክሏል ምንም አይነት ሰልፍም ሆነ ስብሰባ ታግዷል በከተሞቹ ከፍተኛ ውጥረት ነግሷል!!  በጠሚ ዶ/ር አብይ አመራር የተጀመረውን ለውጥ እንደግፋለን ብሎ ዛሬ ሰልፍ የወጣውን #የራያ_ዋጃ_ጥሙጋ ህዝብ እና በአንፃሩ ትህነግ  የጠ/ሚ ዶ/ር አብይን አመራር እንቃወማለን በሚል እያሰናዳ በነበረው የተቃውሞ ሰልፍ ዙሪያ ለመወያየት ትላንት ዘጠኝ ሰአት ላይ በከተማዋ በተደረገ ስብሰባ እምቢ ባለው በራያ አላማጣ ህዝብና የራያ ተወላጅ ካቢኔዎች አቋም የተበሳጨው ትህነግ ይህን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዳወጀ ተነግሯል!!
——-
ይህን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተከትሎ አመሻሹ ላይ በ 17 አውቶብስ የትህነግ ሰራዊት ወደ ራያ የገባ ሲሆን 7 አውቶብሶች ወደ #ራያ ዋጃ 10 የሚሆኑት ደግሞ #ራያ አላማጣ እንዲሰፍሩ ተደርጓል!! ይህን የድጋፍ ሰልፍ አስተባብረዋል በተባሉ ወጣቶች ላይ ከፍተኛ ድብደባ ወከባና አፈና እየተካሄደ ሲሆን በሃያና ሰላሳ ሜትር ርቀት ላይ ሰራዊቱ ወጣቱን ለመግደልና ለማሸበር መሳሪያ አንግቶ በተጠንቀቅ ቆሟል፡፡  የጠ/ሚ ፎቶ ያለበት ቲሸርት የለበሰ ቆመጥ ይቀምሳል ቢሆንም ግን ወጣቱ ለብሶ መደብደብን እና ነጻነቱን ማስከበሩን መርጧል:: የቤት ለቤት አሰሳ በመጀመሩ በልዩ ሁኔታ በባንዳዎች ጥቆማ ወጣቶቹ በነዚህ አረመኔዎች እጅ እንዳይወድቁ በማሰብ #የራያ_ቆቦ ወንድሞቻቸው መኪና በመላክ ብዙ ወጣቶችን ከራያ ዋጃ ወደ ራያ ቆቦ እያሸሹ ይገኛሉ!! ውጥረቱ በመቀጠሉ ሳቢያም ነገ በራያ አላማጣ ተመሳሳይ ነገር ሊኖር እንደሚችል ይገመታል፡፡ በዚህ ሰዓት ግን ከተማዎቹ ጭር ብለዋል!!
————-
በዚህ ጉዳይ ላይ የፌደራል መንግስት እጅግ ከፍተኛ ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ እንዲገባበት እያሳሰብኩ ምናልባት ግን እንደ መነሻ ማቅረብ የምፈልገው የትግራይ ክልል መስተዳድር ይህን የማድረግ ስልጣን አለው ወይ ካለውስ በምን ሁኔታ የሚለውን ስንመለከት የህገ-መንግስቱን አንቀፅ 93 (ለ)ን እናገኛለን፡፡ በዚህ አንቀፅ መሰረትም የክልል አስፈጻሚ አካላት  የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጅ የሚችሉት በክልሉ የተከሰተን የተፈጥሮ አደጋን ወይም ወረርሽኝን ለመከላከል ብቻ ነው ይላል::
ይህም ማለት አሁን ባለው የራያ ጉዳይ የተከሰተው የተፈጥሮ አደጋ ወይም ወረርሽኝ ባለመሆኑ የክልሉ መንግስት አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የማወጅ ስልጣን የለውም፡፡ ስለዚህም የክልሉ መንግስት ህግ ጥሷል ሌሎች የሰብአዊ መብቶችንም በመጣስ ላይ ይገኛል፡፡ ህገ-መንግስቱን በመጣሱም ሳቢያ የፌደራል መንግስቱ ህገ-መንግሰቱን የማስጠበቅ ግዴታ ስላለበት ክልሉ ያወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በመሰረዝ የክልሉን ስልጣን መገደብ አለያም የክልሉን ስልጣን ጠቅልሎ በፌደራል መንግስቱ ስር ማስገባት ይኖርበታል ማለት ነው፡፡
በእንግሊዝኛው ያየን እንደሆነ:  State Executives can decree State of Emergency (SoE) ONLY to prevent a NATURAL DISASTER OR EPIDEMIC. This would be interpreted as IT IS ONLY the Federal Government that can Decree State of Emergency on account of “break down of law and order”.  Thus, the Federal government even can SUSPEND the Autonomy of the Region and bring it under the Federal Government if it egregiously violets the Constitutional Order” እንደ ማለት ነው፡፡
——-
በመሆኑም የትግራይ ክልላዊ መንግስት በሰኔ 30 ቀን 2010 ዓ.ም በራያ ህዝብ ላይ ያወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የህገ-መንግስት ጥሰት እንዳለው ለፌደራል መንግስቱ አበክረን ለማሳሳብ እንወዳለን፡፡ ነገር ግን ይህን ተገንዝቦ የክልሉ መንግስት በፌደራል መንግስቱ በሚጠየቅበት ጊዜ አላወጅንም ቢሉ እንኳን ድፍን የራያ ህዝብ በምስክርነት ይቆማል!! እሱንም ማድረግ እንደምንችል ለመጠቆም እንወዳለን፡፡ ከዚህ ባሻገር ግን ሰሞኑን በሙሉ  የትህነግ ቡድን ከግብረ-አበሩ ጋር ሆኖ በሃገሪቱ የህገ-መንግስት ጥሰት አለ እያሉ ለህገ-መንግስቱ ያላቸውን ጥብቅና ሲያሳዩ የነበሩት በእውነት ለህገ-መንግስቱ ተቆርቁረው ነው ወይስ አዲሱን አመራር “ፋታ ማሳጣታቸው” ነው የሚል ጥያቄን ያጭራል? በርግጥ ግን እንዲህ ህገ-መንግስት ለመናድ መታተር ትህነግ  በፌደራል መንግስቱ ስልጣኑ ሊገደብ አይገባም? በእውነት ትህነግ በዚህ ጊዜ ይህን ማድረግ የፈለገበት አንድምታስ ምን ይሆን?  የፌደራል መንግስትስ እንዲህ ያለውን ሆን ተብሎ የታቀደበትን የህገ-መንግስት ጥሰት እንዴት ይመለከተዋል? እንዴትስ ይፈታዋል?? በትህነግ የጦስ ዶሮ ሊደረግ የታሰበው የራያ ህዝብ የኢትዮጵያ ዜጋ አይደለምን?
አንድ መሆን ማለት አንድ አይነት መሆን ማለት አይደለምና ፍትህ ይከበር!! !!! የህዝባችን ድምፁ ይሰማ! ደህንነቱም ይጠበቅ!!
Filed in: Amharic