ሚኪ አምሀራ
ዶ/ር አብይና ኤርትራ
የኤርትራ እና ኢትዮጵያ ሰላም ወደ መጨረሻዉ ምእራፍ የሚደርስ ከሆነ ምናልባትም ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አንድ ትልቅ achievement ተብሎ ሊያዝለት የሚችል ጉዳይ ነዉ፡፡ ነገር ግን ዳር ለማድረስ ብዙ መሰናክሎችና ጉዳዮች ያሉበት ይመስላል፡፡ በተለይም ሻቢያ እና ህወሃት አሁንም ለእየራሳቸዉ ያላቸዉ ጥላቻ እንዲሁም የትግራይ ኢሊትስ የሚባሉትም በተወሰነ መልኩ የሰላሙን ጥረት በበጎ ጎኑ አለማየት አስቸጋሪ ያደርገዋል፡፡ ሻቢያ ህወሃትን ለማበሳጨት ሲል ከህወሃት ጋር ይሄ ነዉ የሚባል ንግግር አለመፈለጉ፡፡ ህወሃት በበኩሉ እሱ ያልመራዉ የስላም አካሄድ እንደማይጥመዉ ማሳየቱ ነገሩን ያከረዋል፡፡ የድሮ ነገስታቶች ብዙ ጊዜ ከትግራይ ገዥወች ጋር አይስማሙም ነበር፡፡ የትግራይ አካባቢ ገዥወች ያምጹባቸዋል፤ ተንኮል ይሸርባሉ እና ለነገስታቶች አስቸጋሪ ናቸዉ፡፡ በዚህም ምክንያት ነገስታቶች ትግራይን የሚይዙት ከኤርትራወች ጋር ስምምነት በማድረግ ነበር ይባላል፡፡ ምናልባትም ዶ/ር አብይ ያወቀበት ይመስላል፡፡ ያዉ ህወሃት እያፈነገጠ ማስቸገሩ ስለማይቀር በላይ በኩል ዙሮ መያዙ ነዉ እንደ ድሮ ነገስታቶች፡፡
የኤርትራ ህዝብ እና ትግራይ
ሁለቱ ህዘቦች ባብዛኛዉ የባህል እና ቋንቋ የመወረረስ ነገር ቢኖርም ለረዥም ጊዜ በፖለቲከኞች ሲራ እና ተንኮል ሲጎዳዱ በመቆየታቸዉ ወደ ህዝቡ ወርዶ አሁን የክላስ ጥያቄ እስከመሆን ደረሷል፡፡ አንዱ እኔ ነኝ የተሻልኩ ሌላኛዉ እኔ አበልጣለሁ የሚል፡፡ እኛ የምናዉቀዉን የቅርቡን እንኳን ብናየዉ የ27 አመት የኢትዮጵያ የዉጭ ጉዳይ ፖሊሲ ኤርትራ ላይ ያተኮረ ነበር፡፡ ከዛም በተጨማሪ ጣሊያኖች ለኤርትራወች እንዲህ ሲሉ እንደመከሯቸዉ ማንኛዉም ኤርትራዊ ይናገራል የኤርትራ የወደፊት ብቸኛዉ ችግር የሚሆን በስተደቡብ ያሉ ጎረቤቶቻችሁ ናቸዉ ብለዋቸዋል፡፡ “ትግራዮች ሲጠግቡ ከራሳችሁ ላይ ይወጣሉ ሲርባቸዉ እግራችሁ ስር ታገኙዋቸዋላችሁ” ይባላል ብሎ አንድ ኤርትራዊ አጫወተኝ፡፡የመጸሃፉን ስም እረሳሁት እንጅ ጥቅሱን ከመጽሃፍ እንደወሰደዉ ነበር የነገረኝ፡፡
ኤርትራ ከኢሳያስ በኋላ
ኤርትራ እና ኢትዮጵያ ወደፊት አንድ ይሆናሉ ብሎ የሚያስብ ብዙ ሰዉ አለ፡፡ በእርግጥ ዝግ አይደለም፡፡ አሁን ኤርትራን አንድ አድርጎ የያዛት ኢሳያስ አፈወረቂ ብቻ ነዉ፡፡ ኢሳያስ የሌለ ቀን ኤርትራም ዉስጥ ከፍተኛ ችግር የሚገጥማት ይሆናል፡፡ ኤትዮጵያ ዉስጥ ትልቁ ጉዳይ የብሄር ችግር ሲሆን ኤርትራ ዉስጥ ደግሞ ሃይማኖት ነዉ፡፡ በሙስሊሙ እና በክርስቲያኑ መካከል ሰፊ የሚባል መቃቃር ተፈጥሯል፡፡ ሙስሊሞች የኤርትራን ኢኮኖሚና ንግድ በስፋት የተቆጣጠሩት ሲሆን ክርስቲያኑ ደግሞ ባብዛኛዉ ከአገር መዉጣትን ይመርጣል፡፡ ሙስሊሞች እነ ኢሳያስ ጀብሃን አፍርሰዉብናል የሚል ቆየት ያለ ቂምም አለባቸዉ፡፡ በዚህ ቂም ምክንያት some group of people in Eritrea are trying to outlive Isayas. አሁን ባለዉ ሁኔታ የሙስሊሙ ወገን ኢኮኖሚዉን የክርስቲያኑ ደግሞ ፖለቲካዉን ይዞ ይገኛል፡፡ ኢሳያስ ኮሙኒስት ቢሆንም የክርስቲያኑ ተወካይ ነዉ ብሎ ህዝቡ ያምናል፡፡ እናም ኤርትራን አንድ አድርጎ የያዛት ኢሳያስ ነዉ፡፡ እሱ የጠፋ ቀን እርስ በእርስ መጋጨታቸዉ አይቀርም፡፡ ህወሃት አቅም ኖሯት ከቆየች ደግሞ ይሄን ከፍተት ለመጠቀም ይሞክራል፡፡ አሁንም አጋዚያን በማለት የክርስቲያኑን አካባቢ ወደ ትግራይ በመጠቅላል አንድ ጠንካራ መንግስት ባካባቢዉ የመመስረት ህልም አለን የሚሉት ከዚህ ተነስተዉ ነዉ፡፡የኤርትራዉ ምእራባዊ አካባቢ ባብዛኛዉ የእስልምና ተከታይ ሲሆን ሁለት ፓስፖርት አለዉ፡፡ አንድ የኤርትራ አንድ የሱዳን፡፡ ጀብሃ በፓርቲዉ ዉስጥ ክርስቲያንም ያስፈልጉናል በማለት እነ ኢሳያስን ያስገባ ሲሆን ኢሳያስ የፖለቲካ አደረጃጀቱን ካጠና በኋላ አፈንግጦ በመዉጣት የፖለቲካ የበላይነት አግኝቷል፡፡ ሙስሊሞች ደግሞ አብዛኛዉ ክርስቲያን ወጣት ከአገር ሲወጣ በየመንገዱ ገንዘብ ሲፈልግ የቤተሰቡ ንብረት እና ሀብት ተሸጦ ነዉ ሱዳንም ሆነ አዉሮፓ የሚደርሰዉ፡፡ ገዥወች ደግሞ ሙስሊሞች ናቸዉ፡፡ ሙስሊሙ ደግሞ በዚህ መሰረት የኢኮኖሚ የበለያነት አግኝቷል ይላሉ፡፡ከተወሰነ አመታት በፊት እኩል የነበረ ቢሆንም አሁን በቁጥር ሙስሊሙ ይበልጣል፡፡ክርስቲያኑ ከ 50 እና 60 አመት በላይ ያለዉ ብቻ ነዉ አገር ዉስጥ ያለዉ ይባላል፡፡
ኢሳያስና ህ.ወ.ሀ.ት
ኢሳያስ አሜሪካ ህወሃት ላይ ፊቷን እንዳዞረች ተረድቷል፡፡ በዚህ ግርግር he wanted to be part of the equation. ለዛም ነዉ ከኢትዮጵያ ጋር የሰላም ድርድሩን የፈለገዉ፡፡ባድሜ እና አዲ ኢሮብ ለኢሳያስ white elephant እንደሚሉት ነዉ፡፡ white elephant ማለት የማትጠቀምበት ነገር ግን ዉድ እና ክቡር እቃ ማለት ነዉ፡፡ ኢሳያስ ከኢትዮጵያ ጋር ይስማማ እንጅ የአድዋወችን ጉልበት የሚቀንስበት መንገድ ያግኝ እንጅ ባድሜ ወደ ኤርትራ ባይካለልም ችግር የለበትም፡፡ በእርግጥ 95 በመቶ የባድሜ ነዋሪ ኢትዮጵያዊ ትግሬ መሆኑን ያዉቃል (መለስ እሽ ብሎ ሲስማማ እራሱ ኢሳያስ አስገርሞት ነበር)፡፡ እሱ የሚፈልገዉ የኢትዮጵያ ወታደር ከዚህ አካባቢ እንዲርቅለት ነዉ፡፡ በህይወት እያለ ይሄን ነገር ጨርሶ ማለፍ ይፈልጋል፡፡ ህወሃት ደግሞ ይሄን ስለሚያዉቅ ዶ/ር አብይ ቢስማማም ወታደሩ እሽ ብሎ አይወጣም እያሉ ነዉ፡፡ ይህ የነሱ ፍላጎት ነዉ፡፡ኢሳያስ አጋሜወችን በተለየም አድዋን ይጠላቸዋል፡፡ ኢሳያስ የዘር ሀረጉ ከተንቤን/አቢያዲ የሚመዘዝ ለእነ አጼ ዮሃንስ በደም የሚቀርብ ነዉ፡፡ ተንቤንና አድዋ ደገም ደሮ እና ጥሬ ናቸዉ፡፡ ተንቤን ለትግራይ ኩታ ገጠም ስለነበሩ ትግርኛ መቻላቸዉ ነዉ ትግሬ ያረጋቸዉ እንጅ አገዉ እና ስሜነኞች ናቸዉ፡፡የዲ.ኤን.ኤ ምረመራ ቢካሄድ ትግራዊ የሚያደርግ ነገር አይኖራቸዉም ቋንቋዉን ከመናገር ዉጭ፡፡
ነገር ግን ሁለቱም የጋራ ኢንተረስት አላቸዉ፡፡ አንዱ ካላንዱ እንደማይኖር ያዉቁታል፡፡ እስከሚካካዱ እና እስከሚጠፋፉ ድረስ አብረዉ ይኖራሉ፡፡ የሁለቱ ሁኔታ ከአጋም የተጠጋች ቁልቋል እንደማለት ነዉ፡፡ ለምሳሌ የኢሳያስ ኮንታክት ፐርሰን የስብሃት ነጋ ታናሽ እህት ናት፡፡ ይህች ሴት የመከላከያ ሚኒስትሩ የስብሃት ኤፍሬም ሚስት ነች፡፡ ስብሃት ነጋ እና ስብሀት ኤፍሬም የረዥም ጊዜ ጓደኞች ናቸዉ፡፡ እናም ግንኙነታቸዉ እንዲህ ዉስብስብ ነዉ፡፡ባንድ ወቅት ስብሃት ነጋ በራሱ የኤርትራን ነጻነት የማይሹ ህልመኞች ኤርትራን ከመዉጋታቸዉ በፊት እኛ ነዉ እዚሁ በጦርነት የምናስቀራቸዉ እያለ ይዝት ነበር፡፡
ኤርትራ ዉስጥ በስልጣን ላይ ያለዉ ቡድን አብዛኛዉ ሃማሴኖች ናቸዉ፡፡ ይህ ቡድን አጋሜንና አድዋን አካባቢ አጥብቆ ይጠላል፡፡ እነ ኢሳያስ አጋሜን ብቻ ሳይሆን ከአጋሜ ኩታ ገጠም የሆኑትን ለትግራዮች የስነልቦና እና ባህል ቅርበት ያለቸዉን ያራሱን ግዛት አካለ ጉዛይን እንኳን ይጠላል፡፡ አካለ ጉዛይ ቀደም ብሎ የካቶሊክ ሚሽኖች የገቡበት ቦታ ስለነበር የተማሩ እና ብዙ ሰዉ የወጣበት ነዉ፡፡ በዚህም ምክንያት በሃይለስላሴም በደርግም ዉስጥ በብዛት ነበሩ፡፡ አዲስ አበባ ዩኒቨረስቲም እንዲሁ፡፡ ኢሳያስ ከጀብሃ ወቶ ሌላ ድርጅት ሲመስረት አብዛኛዉ የተማረዉ በዉጭ የነበረዉ የአካለ ጉዛይ አካባቢ ሰዉ ነበር የተቀላቀለዉ፡፡ ከዛም አንድ በአንድ አጠፋቸዉ፡፡ ተሰደዉ ሱዳን የሄዱትን እኳን ምህረት አድርጌላችዋለዉ ኑ ብሎ ጠርቶ ገድሏቸዋል፡፡
አጋዚያን
አጋዚያን የድሮ የእንግሊዝ ጥናት ነዉ፡፡ትግርኛ የሚናገረዉን የኤርትራን ክፍል አካለጉዛይ ከአዲግራት ጋር ኩታ ገጠም ነዉ፤ ሰረአይ ከሽሬ ጋር ኩታ ገጠም ነዉ እና ወደ መሃል ኤርትራ ገባ ብሎ የሚገኘዉን ሃማሴን (ቀብሃ ተራራዉ ይሉታል) ከትግራይ ጋር አንድ በማድረግ የባህር በር ያለዉ ጠንካራ መንግስት እዛ አካባቢ መመስረት ነዉ ፍላጎታቸዉ፡፡ይህ ትግራይ ትግርኝት የሚል ሀሳብ እነ ፕሮፌሰር መድሀኔ የሚባሉት ዋና አቀንቃኝ ናቸዉ፡፡ ኢሳያስ ይሄን ሃሳብ አይደለም ቃሉን እንኳን ሲጠቀመዉ የሚሰማ ሰዉ ቢያገኝ ሁለት ባላ ላይ ይሰቅለዋል፡፡ ህወሃት ግን እየጠበቁ ያሉት የኢሳያስን ሞት ነዉ፡፡ አብዛኛዉ የዚህ ሃሳብ አቀንቃኝ ትግሬወች ጠንካራ መንግስት መስርተን ሌላዉን እንገዛዋለን የሚል አስተሳሰብ ነዉ ያላቸዉ፡፡ ጥያቂያቸዉ የነጻነት ሳይሆን ሌላዉን ብሄር፤ ሃይማኖት ወይም ቡድን በጉልበት እንገዛዋለን ነዉ፡፡እንግሊዞች ለሃይለስላሴ የሙስሊሙ ማህበረሰብ አካባቢ ወደ ሱዳን ይሒድ ለናንተ አይጠቅም ብለዋቸዉ ነበር፡፡ ሃይለስላዜ ግን ፈቃደኛ አልነበሩም፡፡ ወደ ሱዳን ሂድ የተባለዉ የኢርትራ ክፍልም ያኔ አልፈልግም አገራችን ኢትዮጵያ ናት ብለዉ ነዉ የቀሩት፡፡ አጋዚያን የሚሉት እንግዲህ ክርስቲያኑን ከነሱ ጋር በመቀላቀል ቀሪዉን የሙስሊሙን አካባቢ ነጥሎ ወይ ለሱዳን ለመስጠት ወይ እራሱን እንዲችል ለማድረግ ያለመ ይመስላል፡፡
አድዋዎች እና የተቀረዉ ትግራይ
አድዋወች ከኤርትራም እዚሁ ከራሳቸዉ ጋርም የተጣሉ ናቸዉ፡፡ በተለይ ከተንቤን አካባቢ ጋር አይና ናጫ ናቸዉ፡፡ ከሽሬወች ጋርም እንዲሁ ልዩነታቸዉ ሰፊ ነዉ፡፡ ሽሬወች እንዲያዉም አድዋን በመጥላት የሚስተካከላቸዉ የለም፡፡ ብዙ ጊዜ ሽሬወች የማህበራዊ ትስስር የሚያደርጉት ከወልቃይት፤ ደበራቅ ደባት ጎንደር አካባቢ አማራ ነዉ፡፡ያ ብቻ አይደለም አድዋ ከ እሱ 23 ኪሎ ሜትር እርቀት ጋር ካሉት አክሱም ጋር እንኳን አይስማሙም:: ለጊዜዉ አንድ ያደረጋቸዉ ነገር ቢኖረ ህወሃት ለጦርነት የተጠቀመበት ስሎጋን ነዉ፡፡ አማራ ጠላታችን የሚለዉ ስሎጋን፡፡ ኤርትራወችንም ተመሳሳይ ስሎጋን ደርግን ከአማራ ጋር በማያያዝ ያስተምሩ ነበር፡፡
አማራና የኤርትራ ሰላም
ወደ ፊት በሰፊዉ የምመጣበት ቢሆንም በትቂቱ ግን፡፡ ብዙ ኤርትራዉያን ጎንደር፤ደሴ፤ ወልደያና ባህርዳር እንደ ሁለተኛ ቤታቸዉ ይቆጥሩታል፡፡ በተለይ ጎንደር ከአስመራም በላይ የሚወዱት አገር ነዉ፡፡ ወያኔ ሲያባራቸዉ ልጅ ተከፋፍለዉ የተለያዩ ብዙ ሰወች አሉ፡፡ አማራ የኤርትራዉያንን ንብረት አንወርስም ብሎ እንዳለ ቤታቸዉን፤ፋብሪካቸዉን፤ ህንጻቸዉን እየሰበሩ ገብተዉ የያዙት ህወሃትና ዘመዶቻቸዉ ነበሩ፡፡ ይህ ሰላም ለነዚህ ሰወች በጣም ትልቅ ፋይዳ አለዉ፡፡ ዞሮ ዞሮ ግን ለምሳሌ የአሰብ ወደብን መጠቀም ከጀመርን የአማራ ህዝብ በጣም ተጠቃሚ ይሆናል፡፡ በተለይም ጎንደር፤ ደሴ፤ እና ወልድያ በቅርብ እርቀት ስለሚገኙ የንግድ መዳረሻ ይሆናሉ፡፡ ከሸቀጣሸቀጥ በላይ ክልሉ የቱሪዝም መዳረሻ በመሆኑ ኤርትራወች በስፋት ሊጎበኙት የሚመጡበት አካባቢ ይሆናል፡፡ በነገራችን ላይ የኢሳያስ አጎትም ደጃዝማች (ስሙ እረሳሁት) የወሎ ክፍለ ሃገር ገዥ ነበር፡፡ በዚህ ጊዜ ነበር ወ/ሮ ስህን ትምህርት ቤት ይማር የነበረዉ፡፡ ከሱዳን ጋር ያለዉን የደንበር ጉዳይም በፍጥነት በመፍታት የምእራቡ አማራ ከሱዳንና ከኤርትራ ጋር ከፍተኛ የንግድ ትስስር መፍጠር ይቻላል፡፡ ወደፊት የምስራቅ አፍሪካ ብሎክ ተፈጥሮ ከጎረቤት አገሮች ጋር ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ግንኙነት የምናደርግ ከሆነ የመጀመሪያዉ ተጠቃሚ የአማራ ህዝብ ነዉ፡፡ ብቻ ይሄን ህዝብ የሚመጥን ራእይ እና ጥበብ ያለዉ መሪ ያስፈልገዋል፡፡ከጎረቤት አገሮችና ክልሎች ጋር የሚያተናኩሱን ይሄን የወደፊት ተጠቃሚነት በማየት እና ለመጉዳት ስለሚፈልጉ ነዉ፡፡