ያሬድ ጥበቡ
ነጋዴው ይሁን ህዝቡ ግልፅ አይደለም፣ በዳላስ ዶክተር አቢይን ለማንገስ ቆርጧል ። ባነሩ፣ ቲሸርቱ፣ ቆቡ፣ የሴልፎን ሽፋኑ ሁሉ አቢይ ነው። አቢይና የኢትዮጵያ ባንዲራ ። በቀደሙት ዓመታት ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ይዘውት የቆዩትን የበላይነት ዘንድሮ አቢይ ቀምቷቸዋል ። የሚገርም ለውጥ ነው ። በተለይ ወጣቱ በአቢይ ሰክሯል። ይህን ታሪካዊ ኩነት ብዙ ሚዲያዎች በቪዲዮ ቀርፀውታል ብዬ አስባለሁ። ይህን መሰል ድጋፍ ያለውን መሪ ዲሲ ሲመጣ ህዝቡን እንዳያገኝና፣ ጥቂት መቶዎች ብቻቸውን ተጠራርተው ሊያገኙት አቅደዋል የሚል ሹክሹክታ ሰማሁ ልበል? እውነት ከሆነ የሚደንቅ ማይምነት ነው። ስታዲየም የሚሞላውን እንግዳችንን እንዴት ለብቻቸው ሊያገኙት አሰቡ? ሃይ፣ ተዉ ባይ ያስፈልጋል። አቢይን ማግኘት ያለብን አስር ሺዎች በኮምካስት ስታዲየም እንጁ፣ ጥቂቶች በደብዳቤ ተጠራርተው መሆን የለበትም። ጁላይ መጨረሻ ላይ የሚመጣም ከሆነ፣ ታዳሚው ጊዜውን ፕላን ማድረግ እንዲችል፣ ቀኑ፣ ቦታው፣ ሰአቱ ለህዝቡ በቶሎ መነገር ይኖርበታል። እኔ ያለኝን ወርውርያለሁ፣ እናንተስ ምን ትላላችሁ?
አንድ ስሙን መጥቀስ የማልችለው ወዳጄ ከዲሲ ደውሎ በጋለ ስሜት “አቢይን ስለመጋበዝ ከአዘጋጆቹ አንዱ ደውሎ ‘ለሁለት ሺህ ሰዎች ያህል በጥሪ ልናደርገው አስበናል ሲለኝ፣ ለምን ለህዝቡ በሙሉ ክፍት አታደርጉትም ብለው፣ ግዴለህም አንተ እኮ ከሚጋበዙት መሀል ነህ አለኝ” ብሎ መረጃ ባቀበለኝ ላይ ተንተርሼ ነው ፅሁፉን የፃፍኩት። ኋላ የእንግዳ ተቀባይ ኮሚቴው ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሰጠ ሰማሁ። ፍላጎቴ አቢይን ህዝቡ ያግኘው የሚል በመሆኑ፣ አዘጋጆቹ ተመሳሳይ እቅድ ካቀረቡ ችግር አይኖርም ማለት ነው።
ሌላው….
… በፍቅር ተደምረን እናግኘው፣ በአንድነት ዘመን መቧደን እንደተባለው አያምርብንም። ደግሞ ይቺን የጠየቃትን አንድ ብር እንዳንከለክለው። ኢትዮጲያዊያን ሳይማር ያስተማረንን ባተሌ ወገናችንን፣ ከሞያሌ እስከ መቀሌ፣ ከጅግጅጋ እስከ ወለጋ፣ ከሀረር እስከ ጎንደር፣ ከድሬዳዋ እስከ አድዋ፣ ከጅማ እስከ አዳማ፣ ከጋምቤላ እስከ ዲላ፣ ከሀዋሳ እስከ ማንኩሳ፣ ከሎጊያ እስከወልድያ ከልብና በፈቃደኝነት ውለታውን የምንከፍልበት የተስፍ ዘመን ላይ ነን ። Abiy will Make Ethiopia Great Again, (AMEGA)