>

ጥረት አንድ ነጥብ አራት ቢሊዮን ብር ተዘረፈ!!! (አርአያ ተስፋ ማርያም)

ጥረት አንድ ነጥብ አራት ቢሊዮን ብር ተዘረፈ!!!
አርአያ ተስፋ ማርያም
 
በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሰውና የብአዴን ንብረት የሆነው ጥረት አንድ ነጥብ አራት (1.4) ቢሊዮን ብር እንደተዘረፈ ታማኝ የቅርብ ምንጮች ጠቆሙ። የተጠቀሰውን ገንዘብ የዘረፈው አቶ ምትኩ በየነ የተባለ የጥረት ዋና ስራ አስፈጻሚ እንደሆነ ሲታወቅ ግለሰቡ “አመመኝ. ህክምና ያስፈልገኛል” በሚል ሰበብ አሜሪካ መምጣቱን ምንጮች አረጋግጠዋል። በአማራ ክልል የዋግህምራ ዞን አስተዳዳሪ የነበረውና በኋላም የጥረት ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆነው አቶ ምትኩ በየነ በቤልጂየም የማስተርስ ዲግሪውን እንደሰራ የጠቆሙት ምንጮች ወደ ስልጣን ያመጣው የብአዴን ሹም ታደሰ ጥንቅሹ መሆኑን አስታውቀዋል።
ከ1.4 ቢሊዮን ብር ዘረፋ ጀርባ የነታደሰ እጅ እንዳለበት ያጋለጡት ምንጮች አያይዘውም ጠ/ሚ/ር አብይ በመንግስትና በፓርቲ ተቋማት ላይ በሹማምንት የተፈፀሙ ሙስናዎችን የሚያጣራ ቡድን ሰይመው ምርመራ እየተደረገ መሆኑንና በነታደሰ በኩል ከፍተኛ መደናገጥ በመፈጠሩ ዋና ዘራፊው ከአገር እንዲወጣ ማድረጋቸውን አመልክተዋል።
 የአቶ ምትኩ ባለቤት “ባለቤቴን ልጠይቅ” በሚል አሜሪካ መምጣታቸው ሲታወቅ ድምፃቸውን በማጥፋታቸው የተደበቀቡት ከተማ ሊታወቅ አለመቻሉን ምንጮች ጠቁመዋል። የሙስና ማጣራቱ እነ አባይ ፀሀዬንም እንደሚያካታት ምንጮች አስታውቀዋል።
Filed in: Amharic