>

ወያኔ በቆየ ቁጥር እየበሰለና የበለጠ ዘመናዊ ዘራፊ እየሆነ መጥቷል! (አቤል ዮሴፍ)

ወያኔ በቆየ ቁጥር እየበሰለና የበለጠ ዘመናዊ ዘራፊ እየሆነ መጥቷል!
አቤል ዮሴፍ
ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ በኢህአደግ ሲመረጥ፤ ድራማ እንደሆነና፤ ወያኔ ኢህአደግን ከህዝባዊ አመጹ ቃጠሎ ለመታደግ እንደሆን ይታወቃል፤ ምንም አብዛኛዉ በ አለማችን የሚሰሩ ተንኮሎችን የመገንዘብ ብቃት ባይኖረዉም።
በጣም የሚገርመው፤ ከምርጫዉ በፊት ወያኔ አዉቆ የሽፈራዉ ሽጉጤን መመረጥ እንደሚፈልግ አበሰረ፤ ይህ ተንኮል ሆን ተብሎ የተደረገ ነዉ፤ ምክንያቱም ወያኔ ሸፈራዉን ሆነ የራሳቸውን ሰው ጠቃላይ ሚኒስተር በማድረግ ነገሮችን ማባባስ አደጋ ዉስጥ እንደሚከታቸው ያዉቃሉ፤ ስለዚህ ማድረግ ያለባቸውን፤ እራሳቸው ኮትኩተዉ ያሳደጉት ታማኝ፤ ነገር ግን፤የወያኔ ሰዉ መሆኑ  ከህዝብ የተደበቀዉን አብይን ማስቀመጥ ነዉ፤ ጥሩ ዉጤት የሚያመጣና የመጣዉን ማእበል አቅጣጫ ሊያስቀይረዉ የሚችል።
አስቂኙ ድራማ
በዚህም ድራማ ላይ፤ ኦህዴድና ብ አዴን ከወያኔ ጋር እንደተቃረኑ ሆኖ ቀረበ፤ በምርጫዉም ሰ አት ደመቀ መኮነን ከምርጫዉ እራሱን በማንሳትና አብይን በመደገፍ የ አብይን መመረጥ አበሰረ።
አብይም አድርግ እንደተባለው፤ የ አክተርነት ሙያዉን ብራድ ፒትን ወይም ዊል ስሚዝን በሚያስንቅ ሁኔታ እየተወዛወዘ፤ የዋሁን ህዝብ ሰለበው።
በወያኔ ስጋዉ ተግጦ አጽሙ የቀረዉ፤ በሃገሩ እንደሁለተኛ ዜጋ እንዲኖር የተፈረደበት ህዝብም አዳኝ ያገኘ ይመስል፤ አብይ አብይ ማለቱን ቀጠለ፤ ነገር ግን ህዝቡ ያልተረዳዉ አብይ የመል አክ ካባ የደረበ፤ የሰይጣኑ የመለሰ ዘናዊ የበኩር ልጅ እንደሆነ ነዉ ያለገባው።
ኢህዴድም ይሁን ብአዴን የወያኔ ፍጡሮች በዉስጥም የተሰገሰጉት፤ ሞራል የሌላቸው፤ አሳማዎችና ጥቅም ካገኙ እናታቸውን ሊያዋዉሉ፤ የሚችሉ ርካሾች ናቸው።
ወያኔም ከመጀመሪያዉ ለዚህ አይነት የክህደት ስራ እንዲሰማሩ የሚመለምላቸው፤ ስነምግባር የጎደላቸውን፤ ለገንዘብና ለቁሳቁስ የሚሳሱ፤ በመጠጥና በሴት በቀላሉ ሊጠመዱ የሚችሉ፤ ደካሞችን ነዉ።
የተካኑበት የማስመሰል ጥበብ
ሆን ተብሎ ወያኔ የተዳከመ በማስመሰል፤ ኢህአደግን እንደገና ማጠናከርና፤ ህዝቡን ሸብበዉ የያዙበትን የጭቆና ቀንበር ማጠናከር ነዉ የተያዘው።
አሁን የሚለውየው፤ ወያኔ ኢህአደግ በመሳሪያ አፈሙዝ ወይም በጉልበት ከመጠቀም ይልቅ፤ ህዝብን በማጭበርበርና አጭበርባሪዎችን ከፊት በማምጣት ማታለል ነዉ ምርጫዉ፤ይህም የሆነበት ምክንያት በጉልበት አፈነዋለሁ ብሎ የሞከርው ህዝባዊ  አመጽ ጉልበት በተጠቀሙ መጠን እየበረታ መምጣቱና ለነሱም አደገኛ ሁኔታ መሆኑን ስለተረዱ፤ ሌላ አማራጭ መምረጣቸው ነዉ።
ይህን ዘዴም የ አሜሪካን ኢምፐሪያሊዝም ከ ቬትናም ሽንፈት በህዋላ፤ ሌሎች ሀገራትን አንጥሩ ሃብት (natural resource as well as cheap labour) ለመዝረፍ በቀጥታ ወታደራዊ ሃይል ከመጠቀም፤ በተዘዋዋሪ አጭበርባሪዎችን በሚሽነሪ (missionaries, either religious or medical) ፤ በ ፒስ ኮር (peace core) ፤ ኢኮኖሚ አማካሪ (economic or military advisors) ወዘተ በማለትና፤ መሪዎችን ጉቦ በመስጠት፤ ለኢኮኖሚ ብዝበዛ በራቸዉን እንዲከፍቱ ማድረግ ነዉ።
ወያኔ በቆየ ቁጥር እየበሰለና የበለጠ ዘመናዊ ዘራፊ እየሆነ መጥትዋል፤ ስለዚህ ህዝባችን እንደዚህ አይነቱን መሰሪ ለመታገል፤ የበለጠ መንቃት ይኖርበታል።
Filed in: Amharic