>

ሕግ ህግ ነው!! ሕግ መከበር አለበት!!! (ቬሮኒካ መላኩ)

ሕግ ህግ ነው!! ሕግ መከበር አለበት!!!
ቬሮኒካ መላኩ
 
 ጠቅላይ ሚኒስትሩም ለራሱ ዋስትና የሚሆነው ህጉ እንጅ ቡድኖች አይደሉም።ጠ/ሚ ዶ/ር አቢይ አህመድ አዲስአበባ የተቋቋመችበትን ቻርተርና ህግ በቡልዶዘር  ጠርምሶ ህጉን በቀይ እስኪብርቶ እየሰረዘ ነገ በቴሌቪዥን መጥቶ እኔን  “ህግ ይከበር ፣ ህግ አክብሪ! !”  የማለት የሞራል ብቃት የለውም።
ወይም ለይቶለት እንደ ፊውዳል ዘመን የአውሮፓ ነገስታት እንደ እነ ንጉስ ሊዊ  ዶ/ር አቢይም በይፋ ወጥቶ ከዛሬ ጀምሮ “I am the constitution “, ” I am the Charter!” ,” I am the law !” ይበለንና ቁርጡን አውቀን ፊናችንን እንለይ ።
በተረፈ ህግ የሚጥሱትን በህግ እንጠይቃለን ፣ሌባን እናስራለን”  እየተባለ  አዲስ አበባ መመስረቻ ህግ ሲጣስ የአዲስ አበባ ቁልፍ ሲሰረቅ ዝም ማለት የመርህ ሰው አለመሆን ነው።
 እነ ማንደላን እያደነቁ ፣ እነ መሀተመ ጋንድን እያወደሱ ፣ ስለ እነ ሶቅራጥስ  የሞራል ልእልና ለአርቲስቶች እየሰበኩ  በጎን ተቃራኒውን ሆኖ መገኘት ስሁት ነው ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚያደንቀው አርቲስቶችን ሰብስቦ ስሙን ሲጠቅሰው የነበረው ሶቅራጥስ  በገዥዎች ታስሮ  የሞት ፍርዱን በሚጠባበቅበት እስር ቤት ውስጥ  እያለ ተማሪዎቹ እስር ቤቱን ሰብረው ገብተው ” ና ውጣ!  ከሞት ተርፈሃል ፣ ከአቴንስ የምትወጣበትንም ጀልባ አዘጋጅተናል ”  ሲሉት  ምን አለ?
ሶቅራጥስ እንደዚህ አለ… ” በግሪክ ህግ ተወልጄ ፣ በግሪክ ህግ ልደቴን አክብሬ ፣ በግሪክ ህግ አግብቼ ፣ የግሪክን ህግ ተቀብዬ ኖሬ  በግሪክ ህግ ሞት ሲፈረድብኝ ለማምለጥ ከሞከርኩ ምኑን ሶቅራጥስ ሆንኩኝ? ” በማለት ከእስር የማምለጥ ሙሉ አቅም እያለው እኔ ኖሬ ውሸት፣ ህግ አልባነት  ከሚነግስ እኔ ሞቼ እውነት ትሩር ፣ብሎ በግሪክ ህግ የተፈረደበትን  የሄሞሎክ መርዙን  ጠጥቶ እና እያሰበ ወደ ዘላለም ዝምታ ነጎደ .።
ህግ ካላከበርን ፤ ፍትህና እና እውነት ካልተከበሩ ለዘረኝነት ዘረኝነትማ መለስ ዜናዊ አልነበረም እንዴ?!
አሁንም እንደቃልህ ሆነህ ህግን እስክታከብርና ወደ ትራክህ እስክትመለስ እየጠበቅንህ ነው።
Filed in: Amharic