>

ከባሌ ጎባ ፍጅትና ትርምስ ጀርባ ያሉ የጥፋት እጆች!!!  ኦፕሬሽን እሳት እና ጭድ - ከድር እንድሪስ

ከባሌ ጎባ ፍጅትና ትርምስ ጀርባ ያሉ የጥፋት እጆች!!! 
ኦፕሬሽን እሳት እና ጭድ – ከድር እንድሪስ
ኦፕሬሽን ‘እሳትና ጭድ’ መሰረቱን #በመቀሌ አድርጎ ከክፋት ሰንኮፉን በመላ ሀገራችን የዘረጋው የቀን ጅቦች ስብስብ፣ #በባሌጎባ አዲስ #የዘር / #የሃይማኖት ግጭት በማደራጀት የንፁኃን ደም እንዲፈስ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ #አዲሱንየኦሮሚያ የወረዳ አከላለል እንደመነሻ በማድረግ ቡድኑ #ማዳበሪያ #ሙሉ #ገንዘብ በማደል ያሰማራቸው የጥፋት ተላላኪዎች፣ #አደባባይ #በማፍረስና #የኦነግ #ባንዲራን #በመስቀል እንዲሁም #ቄሮን #መስሎ ንፁሃንን በመግደል ህዝብን ለማፋጀት ላይ ይገኛሉ፡፡ ይህንን ኦፕሬሽን የሚመራው የቀን ጅቦች ቡድን ማዕከሉን መቀሌ ያደረገ ሲሆን #መነሻውን #ከምስራቅ_ዕዝ ( #ሀረር) አድርጎ፣ #ከጭናቅሰን እስከ #ሞያሌ #ዘርን መሰረት ያደረገ ፍጅትና መፈናቀል የማቀናበርና መምራት ሀላፊነት በፀረ-ለውጥ ድብቅ ኮማንድ የተሰጠው ነው፡፡
የዚህ ቡድን የፊት መሪዎች 
1. ጄንራል #አብርሃ/ኳርተር
2. ሜ/ጀነራል #መሀሪ_ዘውዴ
3. ሜ/ጀነራል #ገብረሚካእል_በየነ
4. ብ/ጀነራል #ነጋሲ_ርእሲ
5. ኮሎኔል #ሙልጌታ_አለምሰገድ
6. ሻለቃ #ዘበነ
ይህ ቡድን በሰኔ 16 የ #መስቀልአደባባይ የሽብር ጥቃት ሴራ ተካፋይ የሆነ ሲሆን #በምድርሀይል #የመገናኛ ዋና መምሪያ በመሰባሰብ # አዲስ የሬድዮ መገናኛ ፍሪክውንሲ እንዲዘጋጅ ያደረገ ነው፡፡ የዚሁ ቡድን አባላት የሆኑት ብ/ጄ #ሰመረና ኮሎኔል #ኪዳኔ በመስቀል አደባባይ ሰልፍ ወቅት ለድንገተኛ ችግር ተብሎ በጠቅላይ መምሪያ የተሰበሰቡ የሰራዊት አባላትን ከተሰጣቸው ግዳጅ ውጭ ችግር ከተፈጠረ በቀጥታ እርምጃ በመውሰድ ወደ ቤተ-መንግስት እንዲያቀኑና ቤተ-መንግስቱን እንዲከቡ ኦሬቴሽን የሰጡ ናቸው፡፡
በአሁን ሰአት የዚህ ቡድን አባላት የሆኑት ሰራዊት አባላት የባሌ ጎባውን ግጭት ከጀርባ ሆነው በማቀናበር ላይ እየተሳተፉ እንደሆነ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ የምስራቅ እዝ፣ የ21ኛ ክ/ጦር ዘመቻ ሀላፊ ኮሎኔል #ሀጎስ፣የመረጃ ሀላፊ ኮሎኔል #አዳፍሮምና መገናኛ ሀላፊ ኮሎኔል #አዲሱ፣ የ11ኛ ክ/ጦር የ3ኛ ሬጅሜንት አዛዥ ኮሎኔል ዮሃንስ፣ የ20ኛክ/ጦር አዛዥ ኮሎኔል #ገብረድንግል (የቐንቐ ትምህርት እማራለሁ በሚል እረፍት ወትጦ የሽብር ኦፐሬሽን የሚያቀናጅ/የሚያገናኝ) ግለሰብ ነው፡፡
በቀን ጅቦች ላይ አፋጣኝ እርምጃ ካልተወሰደ ህዝብ በለውጡ ተስፋ ይቆርጣል፣ የቀን ጅቦች አላማም ይህንን እውን ማድረግ ነው!!!
ህዝባችን ንቃ!
በሚቀዱልህ የዘር ጥላቻ እየተመራህ እርስ በርስ አትጋጭ!!!
 
#የጥላቻ_ንግግር_ዘረኝነት_ይቁም
 #Stop_hate_Speech
#Stop_ethinic_Racism 
የኦሮሞ እና የአማራ አክራሪ ብሄርተኞች ነፃነትን እና ዲሞክራሲን ልትወልድ ምጥ ላይ ያለችውን ሀገራችንን ወደሓላ እየመለሳችሓት ነው። ከዚህ ድርጊታችሁ የማትቆጠቡ ከሆነ አማራ እና ኦሮሞ የሚባል ህዝብም አይኖራችሁም። ሀገራችን እስከዛሬ እነ ሶሪያ እና ሊቢያ ላይ ያየነው እልቂት የሚያስንቅ እልቂት ለመፍጠር ተግታችሁ እየሰራችሁ ነው።
የአማራ እና የኦሮሞ ህዝብ ስም እንሰራለን የምትሉ ሚዲያዎችም ( #ልሳነ_አማራ ፣ #OMN ወዘተ) የምታስተላልፉት የዘረኝነት መልዕክት ዛሬን ብቻ ሳይሆን መጪውንም ዘመን የሚያበላሽ ፣ የነገ ሀገር ሳይሄን ጥላቻ እና ቂም ተረካቢዎችን ለማፍራት እየሰራችሁም እንደሆነ ነው እያየሁ ያለሁት።
የስከዛሬው ጥፋት እንተወው እና ከዚህ በሓላ እስኪ ለልጆቻችሁ ለልጅ ልጆቻችሁ አስቡ፣ ይብቃ
እንዴት ሰው የ PhD እና የፕሮፌሰር ትምህርት ደረጃ ላይ ደርሶ ትውልድን ከችግር የሚያወጣ ሳይሆን ትውልድን ዘላቂ ችግር ውስጥ የሚከት ስራ ይሰራል።
አሁን እየተፈጠሩ ያሉት ግጭቶች የብዙ ተዋናዮች/ ስራ ውጤት ቢሆንም እንደ ሚዲያ OMNንም እንደ ዶር #ፀጋየአራርሳ ፣ ፕሮፌሰር #እዝቄልጋቢሳ ፣ #ግርማጉተማ አይነቶቹን ምንም አይነት ሀላፊነት ስሜት የማይሰማቸውን ሰዎች በ OMN ሚዲያ የሚያስተላልፉትን መርዝ በአስቸኳይ ማስቆም አለበት።
በአማራም ስም የተፈለፈሉ ሚዲያዎች እንዲሁ ተመሳሳይ እርምጃ መውሰድ አለባቸው።
የህግ ባለሙያ የሆናችሁ ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖች የጥልቻ እና የዘረኝነት መልዕክትን የሚያስተላልፉ ሰዎችን ወደ ህግ የሚቀርቡበት መንገድ ካለ ሁሉንም አማራጭ እንድትጠቀሙ ይህ የትግሉ አንድ አካል ብታደርጉት።
መንግስት ደግሞ በአስቸኳይ ብሄራዊ የታሪክ እና የባህል ማዕከል || National History and Culture Institute እንዲያቋቁም እና በአስቸኳይ ልዩነት የሚፈጥሩ የታሪክ ክስተቶች ላይ ጥናት ከሁሉም ማህበረሰብ በተውጣጡ የታሪክ ባለሙያዎች እንዲያስጠና እና ሀገራዊ መግባባት እንዲፈጠር በቶሎ መስራት ይኖርብናል።
መንግስትም መፍጠን ይኖርበታል።
Credible intelligence source
Filed in: Amharic