>

ከሚወደድ ይልቅ ህግን አስከብሮ የሚፈራ መንግስት ለመሆን መስራትን ነው ወቅቱ የሚጠይቀው !!! (ቬሮኒካ መላኩ)

ከሚወደድ ይልቅ ህግን አስከብሮ የሚፈራ መንግስት ለመሆን መስራትን ነው ወቅቱ የሚጠይቀው !!!
ቬሮኒካ መላኩ
ጠ/ሚ ዶ/ር አቢይ አህመድ አሁንም የምልህን ስማ ። መንግስት በአራቱም አቅጣጫ ተወጥሯል። የአገሪቱ  እጣ ፋንታ አስጊ ደረጃ እየደረሰ ነው ። በዚህም መሰረት የመንግስትህ ጡንቻ እስኪፈረጥም ድረስ  የሚከተሉትን እርምጃዎች ውሰድ
1ኛ~ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጅ። ( እነ ፈረንሳይም ቤልጅዬምም ከአመት በፊት አድርገውታል)
2ኛ~ ጥቅማቸው የተነካባቸውንና ይሄን ወንጀል በማስተር ማይንዲነት የሚፈጥሩና በየቦታው አለመረጋጋት የሚፈጥሩትን  ሁሉ በቁጥጥር ስር አውል።
3ኛ ~ የፀጥታ ሀይሎች  ህግ ለማስከበርና የዜጎችን ዋስትና ለመጠበቅ ተመጣጣኝ እርምጃ እንድወስዱ ቀጭን ትእዛዝ አስተላልፍ።
4ኛ~ መንግስትህን አፅና ። መንግስትህ ፍራጃይል ሆኖ  የሚወደድና የሚፈቀር   መንግስት ከሚሆን ይልቅ ህግ የተከበረበት  የሚፈራ  ጠንካራ መንግስት ቢሆን  ይሻላል።
በጭናክሰን፣ በባቢሌ፣ በጎንደር፣ በባሌ፣ በቤኒሻንጉል፣ ወዘተ የዘፈቀደ ግድያዎች ተበራክተዋል። ስርአት አልበኝነቱ ከመንሰራፋቱም በላይ ኢ- ሰብአዊ ወንጀሎች ተበራክተዋል ለዚህም ማሳያ ይሆነን ዘንድ ከጃዋር መሀመድ ገጽ ያገኘሁትን አሰቃቂ ዜና ላካፍላችሁ።
በምጥ ለተያዘች ነፍስ ጥይት?!
 
  ይህች ከዚህ በታች የምትመለከቷት ነፍሰጡር በደምቢዶሎ ከተማ በትናንትናው ዕለት ምሽት ወደ ህክምና ስትሄድ በጥይት ተገድላለች። በምጥ የተያዘች ነፍስ በጥይት የምትገላገልበት ግፍ በአስቸኳይ መቆም አለበት። ያሳዝናል፤ ልብ ይሰብራል!
  የዚህች ነፍሰ ጡር ገዳዮችም ለፍርድ አይቀርቡም? የኢትዮጵያን ወገኖቻችን ደም በተለያዩ አከባቢዎች እንደጎርፍ እየወረደ ነው። በጭናክሰን፣ በባቢሌ፣ በጎንደር፣ በባሌ፣ በቤኒሻንጉል፣ ወዘተ የዘፈቀደ ግድያዎችና የተጠኑ ማሕበራዊ ሰላም የማደፍረስ ሥራዎች እየተሰሩ ነው። ፍትሕ በአስቸኳይ! ወንጀለኞች ለፍርድ ይቅረቡ!
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ያስብ፤ ሕዝቧን ይባርክ!
Filed in: Amharic