>

የኢንጅነሩ ሞት ልብ ሰባሪ ነው፤ ያም ሆኖ ገዳዮች እንደሚፈልጉት ሀገር ወደሚጎዳ ብጥብጥ ልንወሰደው አይገባም (ጃዋር መሀመድ)

የኢንጅነሩ ሞት ልብ ሰባሪ ነው፤ ያም ሆኖ ገዳዮች እንደሚፈልጉት ሀገር ወደሚጎዳ ብጥብጥ ልንወሰደው አይገባም
ጃዋር መሀመድ  – የ OMN ስራ አስኪያጅ
የኢንጂነር ስመኘው በቀለ  ሞት/ ግድያ በከፍተኛ ጥንቃቄ መያዝ ያስፈልጋል። ተገድሎ ከሆነ የገዳዮች አላማ ሀገርን ወደባሰበት ግጭት መግፋት ነው። ስለዚህ የወንጀሉ ምርመራ  በፍጥነት እና በጥንቃቄ ሊከናወን እና ውጤቱም ቶሎ ለህዝብ ሊገለጽ ይገባል። እስከዚያውም በመላ ምት ብቻ ቡድናዊ ፍረጃን  መጠንቀቅ አስፈላጊ ነው። ይህን ፖሊቲካዊ ግድያ ሊፈጽሙ የሚችሉ ብዙ ብድኖች እንዳሉም ማወቅ አለብን። ገለልተኛ ምርመራ ብቻ ነው ጥርት ያለ መደምደሚያ ሊሰጠን የሚችለው።
የኢንጅነሩ ሞት ልብ ሰባሪ ነው። ይህ መሃንዲስ ለሀገሩ የኖረ እድሜ ልኩን ህዝብ ያገለገል በጣም ወሳኝ ብሄራዊ ፕሮጀክት እያሰራ ለሀገር የተሰዋ ነው። የሱን ሞት ለበለጠ ሀገር ግንባታ እንጂ ገዳዮች እንደሚፈልጉት ሀገር ወደሚጎዳ ብጥብጥ ልንወሰደው አይገባም። ዜጎችም የመንግስት አካለትም በችኮላ እርምጃ ከመውሰድ እንዲቆጠቡ እማጸናለሁ።
የኢንጂነር ስመኘው በቀለ የቀብር ስነስርዓ ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሟል። ትክክለኛ ውሳኔ ነው። አሁን ሁሉም በተረጋጋ ሁኔታ የፖሊስን ምርመራ ሂደት እየተከታተለ እና ውጤት እየጠበቀ ለብሄራዊ የቀብር ስነስርዓቱ ይዘጋጅ:: ጃዋር መሀመድ
Filed in: Amharic