>

በዐማራ ምድር በሰሜን ኢትዮጵያ ጨረቃም ደም ለበሰች አሉኝ። (ዘመድኩን በቀለ) 

በዐማራ ምድር በሰሜን ኢትዮጵያ 
   ጨረቃም ደም ለበሰች አሉኝ።
            ዘመድኩን በቀለ 
~ እኔ ግን ሳስበው ይኼ” እንደጀመርነው እንጨርሰዋለን ብለው የጻፉት መፈክር ” ለግድቡ አይመስለኝም። ይልቁኑ ከኢትዮጵያ ምድር እንዲጠፋ፣ እንዲወገድ ሳይጨርሱት የማይተዉት፣ የማይለቁትም ከምድሪቱ እንዲጸዳ የሚፈለግ ነገድ ያለ ይመስለኛል። አከተመ ።
~ ጓደኞቼ ለእኔ የታየኝንና የተሰማኝን የውስጤን እውነት እንዲህ ጽፌዋለሁ። በዚህ መልክም ተንፍሼዋለሁ። እናንተም እንደታያችሁ መጠን እንደ አረዳዳችሁ የውስጣችሁን ስሜት የመጻፍ መብታችሁ እንደተጠበቀ ነው። ነገር ግን ለምን እንደመንጋው አታስብም እንደመንጋውም አትጽፍም ለሚሉኝ መልሴ “ግዴታ የለብኝም” የሚል ይሆናል። እኔ ዘመዴ የማስበው፣ የምጽፈው፣ የምኖረውም እንደዘመድኩን በቀለ ብቻ ነው። ይኸው ነው።
#ETHIOPIA | ~ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ይላል ” #ለደም ከተማ ወዮላት! በሁለንተናዋ ሐሰትና ቅሚያ ሞልቶባታል፤ ንጥቂያ ከእርስዋ አያልቅም።” ትን ናሆም 3፣1።
~ በምድራችን ላይ የግፍ ጽዋ ሲሞላና ሲትረፈረፍ፣ ንጹሐን በግፍ ሲጨፈጨፉ ጨረቃ ቀልታና ደም መስላ መታየቷ የቆየ ልማድ እንደሆነ ነው ሲተረክ የኖረው። ይኽን ሁኔታ ሳይንስ የጨረቃ ግርዶሽ፣ የቀይ ጨረቃ መገለጥ ፣ ቅብጥርስዮ፣ ምንትስዮ እንደሚለውም አውቃለሁ። እኔ ግን ዕለተ አርብን አስታውስበታለሁ። የንፁሕ ሰው ደም በከንቱ በፈሰሰ ጊዜ ሁሉ እንኳን ሰው ፍጥረታት በሙሉ ያዝናሉ። ፀሐይም ጨለመች፣ ጨረቃም ደም ሆነች፣ ከዋክብትም ረገፉ እንዲል ታላቁ መጽሐፍ።
አሁን “ደግ ሰው ከምድር ጠፍቶአል፥ በሰውም መካከል ቅን የለም፤ ሁሉ #ደምን ለማፍሰስ ያደባሉ፥ ሰውም ሁሉ ወንድሙን በመረብ ለመያዝ ይከታተለዋል።” ሚክ 7፣ 2። መጽሐፍ ቅዱስ መረብ ሲል ምን አስታወሰኝ የእኛውን የኢንፎሬሜሽን መረብ የሚባል መሥሪያቤት አስታወሰኝ። ሰውን ለመያዝ መረብ የሚዘረጋ፣ እንቅልፍ አጥቶ የሚከታተል፣ ከያዘም በኋላ ብልት የሚያኮላሽ፣ እንደበግ የሚያርድ፣ ደም ለማፍሰስ የሚባዝን፣ የሚያደባ፣ ደም ካላፈሰሰ የማይረካ፣ ደም ምሱ የሆነ ተቋም። እሱ ነው መረብ ፣ እሱ ነው የንጹሐንን ደም መጣጭ። ታዲያ ምን ያደርጋል ይኼ መረብ አይከሰስም፣ አይወቀስም፣ በመደመር ሂሳብ ዘና፣ ፈታ ብሎ ተንደላቅቆ ይኖራል።
ወዳጄ እነርሱ እንደሆኑ … “ደምን ለማፍሰስ እግራቸው ፈጣን ነው፤ ጥፋትና ጕስቍልና በመንገዳቸው አለ፥ የሰላምን መንገድ አላወቁአትምና እግዚአብሔርን መፍራት በዓይናቸው ፊት የለም።” መዝ 14፣ 6። ከክርስቲያን ሀገር ተወልደው፣ ከክርስቲያን አፈር ተፈጥረው እንዴት ሰው የክርስቲያን ግብር አይኖረውም? በምድር ጠያቂ በጠፋ ጊዜ ግን እግዚአብሔር መጠየቅ ይጀምራል። የእሱ ፖሊሶች ጉቦ አያውቁም፣ ለምርመራ የሲአይኤን እርዳታም አይፈልጉም። የመንገድ ላይ ካሜራ ቢነቀል እነሱ ከማየት አያግዳቸውም። ሰውም ባይኖር፣ በምድር የውስጠኛው ክፍልም ውስጥ ወንጀሉ ቢሠራ ከእግዚአብሔርና ከእግዚአብሔር ሠራዊት ዕይታ ሊያመልጡ አይችሉም። የአቤልን ደም አፍስሶ ከፈጣሪ ፊት ለመሰወር አይቻልም።
እናም ይህን ሁሉ ግፍ ያየ የተመለከተው ጻድቅም እንዲህ አለ። እነሆ…አምስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ፥ ስለ እግዚአብሔር ቃልና #ስለ_ጠበቁት_ምስክር የታረዱትን የሰዎች ነፍሳት ከመሠዊያ በታች አየሁ።
ከዚያም … ስድስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ አየሁ፥ ታላቅም የምድር መናወጥ ሆነ፥ ፀሐይም እንደ ማቅ ጠጕር ጥቁር ሆነ፥ #ጨረቃም_በሞላው_እንደ_ደም_ሆነ፥ ራእይ 6-13።
እናም ዛሬ ብዙ ጓደኞቼ በኢትዮጵያ ሰማይ በተለይ በዐማራው ምድር በባህርዳርና በጎንደር መሃል የነበሩ ዜጎች በሰማይ ላይ ስትታይ ያመሸችውን ጨረቃ ደም ለብሳና አዝና ቀልታ መታየቷን ፎቶ አንስተው ሲልኩልኝ አምሽተዋል። ሳይንስ የጨረቃ ግርዶሽ ቢለውም እኔ ግን የንጹሕ ሰው ደም ነው በጨረቃዋ ላይ ፈስሶ የታየው ባይ ነኝ። በሥላሴ ዙፋን ፊት የፈሰሰ የንጹህ ሰው ደም።
አዎ … የ100 ሚልዮን ዜጎች ግምትና ወኪል ኃላፊነትንም ተሸክሞ የነበረውን የቤተክህነት የአብነት ትምህርት ቤቱ  ሊቅ ደም ነው በጨረቃዋ ላይ የፈሰሰው። ሟቹ አንድ ግለሰብ አይደለም። የ100 ሚልየን ዜጎች ግምት የሆነ ሰው ነው፤ ከ30 ዓመታት በላይ ሀገሩን ኢትዮጵያን ለማበልጸግ ሲል አባቱን የኩራዝ ጭስ በሞላው ቤት አስቀምጦ ለኢትዮጵያ ብልጽግናና ብርሃን ይወጣ ዘንድ እንደሻማ እየቀለጠ ሌት ተቀን ቤተሰቦቹን ተለይቶ በየበረሃው ሲባዝን የኖረው የሊቀ ዲያቆናት ኢንጅነር ስመኘው በቀለን ንጹሕ ደም፣ የእሱ ደም ነው ትናንት በኢትዮጵያ ምድር በወጣችው ጨረቃ ላይ ፈስሶ የታየው ደም።
አቦ ወዳጄ ነፍስህን በአባቶቻችን በአብርሃም፣ በያዕቆብና በይስሐቅ አጠገብ ያሳርፍልን።
መቼም … የኢትዮጵያ መንግሥትና ፖሊስ የተፈጸመ ወንጀልን ምርመራ መጀመራቸውን፣ ውጤቱንም በቅርቡ ለህዝብ እንደሚያሳውቁ ማወጅ መናገር እንጂ ወንጀለኛውን ይዘው ለፍርድ ማቅረብ እንዳይችሉ፣ ፍላጎቱም እንደሌላቸው አውቃለሁ። ይኽ አይነት ልምዱም ባህሉም እንደሌላቸውም አውቃለሁ። እንዲያውም የሟችን ሾፌር በድንገት ከሥራ አስወግደው። ሟች ጠባቂም፣ ምስክርም እንዳይኖረው አድርገው ሲያበቁ፣ ሟች ከመሞቱም በፊት ሟቹ ከሚገደልበት ስፍራ የመንገድ ላይ ካሜራ አንስተው ሀገር የሚያኽል ሰው በቀን በጠራራው ያውም በመስቀል አደባባይ ላይ ከገደሉና ካስገደሉ በኋላ ሚሽኑን ማለቁን ሲረዱ ያነሱትን ካሜራ መልሰው የሚተክሉ ጨፍኑ ላሞኛችሁ አይነት የድሮ አራዳ አይነት መሪዎች በሞሉበት ሀገር እንዴት የንጹሐን ገዳይ ይታወቃል? ሀገር ሞቶ ሳለ እየሳቀ፣ ደግሞም ፈገግ እያለ መግለጫ የሚሰጥ የፖሊስ አዛዥ ባለበት ሀገር እንዴት ፍትህ ይገኛል?
ወገኔ በተለይ በአዲስ አበባ የመንገድ ላይ ካሜራዎች መነሳታቸውን ባያችሁ ጊዜ፣ መብራትና ኔትወርክ ድንገት በተደጋጋሚ ዕልም ድርግም ማለቱን በተመለከታችሁ ጊዜ፣ በተለይ ነገዳችሁ ከነገደ ዐማራ የሆናችሁ ባለ ብሩህ አዕምሮ እና በከፍተኛ ሀገራዊ ሃላፊነት ላይ ያላችሁ ኢትዮጵያውያን ጥንቃቄ አድርጉ። የተጋበዛችሁበት ቤት ሁሉ እየሄዳችሁ እጃችሁን ታጥባችሁ ለመመገብ አትጣደፉ፣ የሚያምረው ክትፎ በውስጡ ምን እንደተቀበረ፣ የሚያምረው ጮማ በላዩ ምን እንደተቀባ፣ ሻይና፣ ቡናው፣ ውስኪና ቢራውንም እንዳገኛችሁ አትገሽሩ። አለማየሁ ኦቶምሳ፣ የጋምቤላው ባለሥልጣን በዚህ አይነት መንገድ እንደተወገዱም ይነገራል። በተለይ ሹፌሮቻችሁን መንግሥት በቀየረባችሁና መኪናችሁን ራሳችሁ እንድታሽከረክሩ በተደረገ ጊዜ ያን ጊዜ የህይወታችሁ ፍጻሜ እንደሆነ እውቁ። እንዲያም ሆኖ ገዳዮቹ ከሹፌርና ከሥራ ባልደረባችሁ ጋርም ሆናችሁ ቢሆን ይምሯችኋል ማለትም አይደለም። የዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ ሥራ አስኪያጅ የተገደሉት ከጸሐፊያቸውና ከሹፌራቸው ጋር መሆኑን የታወቀ የተረዳነው ነገር ነው።
ሟቹ የሰሜን ሸዋ ሊቀጳጳስ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ጎርጎሬዎስም የዚህ ድራማ ሰለባም መሆናቸው መዘንጋት የለበትም። [ እንዴትና በእነማን እንደተገደሉ እንደእግዚአብሔር ፈቃድ ወደፊት እተርክላችኋለሁ ” ከአንዱ በቀር እንዳስገደሏቸው የሚጠረጠሩ ግለሰቦች አሁንም በህይወት እንዳሉ ይታወቃል። ብዙ ሊቃነ ጳጳሳት በመኪና መገልበጥ ስም ታፍነውና በመስቀላቸው አንገታቸውንና ልባቸውን እየተወጉ እንደተገደሉም በቤተክህነቱ የሚወራ እውነት ነው። በተለይ ዐማራ ሆነህ ስምና ማዕረግ ካለህ ኢትዮጵያ በመጨረሻ ቀርጥፋ ትበላሃለች። ጎጃሜው መጋቤ ብሉይ ሰይፈሥላሴ በእነ አቦይ ስብሐት ከከሸፈው ከአሜሪካው የሲኖዶስ እርቅ ጉባኤ በኋላ በሁኔታው ተናደው ወደ ሀገር ቤት ሲመለሱ አውሮፕላን ውስጥ ሆዴን ቆረጠኝ ብለው በአፍ በአፍንጫቸው ደም ተፍተው በፍጥነት የሞቱበትንም መንገድ ማስታወሱ አይከፋም። ለዚህ ነው ብዙ ምስጢር የሚያውቁት የዓለም ጤና ድርጅት ፕሬዘዳንቱ ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም በአውሮፕላን ሲጓዙ በጠኔ ፍግም ይሏታል እንጂ እህል በአፋቸው፣ ውኃም ጭምር አይቀምሷትም የሚባለው። ኢንዴዥያ ነው።
እናም ጌታ ሆይ” በሬዬን ሰርቀው ሲያበቁ እናፋልግህ ብለው አብረውኝ መንገድ ከጀመሩ ሰዎች ጋር ሆኜ መቸም ቢሆን በሬዬን እንደማላገኘው አንተ ታውቃለህ። እናም በቀል የአንተ ነው። ” አቤቱ፥ ተነሥ በቀልህንም ተበቀል፤ ሰነፎች ሁልጊዜም የተላገዱህን አስብ።” መዝ 74፣ 22።
የገደለው ባልሽ፣ 
የሞተው ወንድምሽ፣
ሀዘንሽ ቅጥ አጣ፣ 
ከቤትሽ አልወጣ ።
ሻሎም !   ሰላም !
Filed in: Amharic