ጁኒየር ሌፍትናንት ተረፈ መኰንን
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ 27 ዓመት ደከመኝ ሰለቸኝ፣ የክረምቱ ቁር የበጋው ሀሩር ሳይበግረው ከባለቤቱና ከልጆቹ እየተለየ ከአገር አገር በመላው ዓለም እየተንከራተተ ይህ የተስፋ ቀን እንዲመጣ ሲለፋለት የነበረውን ትግል እንደ አንዳንድ ሆዳም ለጥቅም ብሎ ሳይንሸራተት እንደ ስሙ ታማኝ ሆኖ የኢትዮጵያ ህዝብን ያገለገለውን ታማኝ በየነን ከመድረክ መሪነት በወያኔው አሻንጉሊት ካሳ ተክለ ብርሃንና መሰሪ የወያኔ ተላላኪዎች አግለው እርስዎ በማክበር ከትላንት ጀምሮ ሲያፈላልጉትና በግልም ስልክ በመደወል ዛሬ እንዲገኝ አድርገውት ስላመሰገኑልን 27 ዓመት ያገለገለን ምርጥ አምባሳደራችን ስለሆነ እናመሰግንዎታለን!
ውድ ታማኝ ከማንኛውም ኢትዮጵያዊ በላይ እጥፍ ድርብ የደከምክ ስለሆነ ይህን ቀን በማየትህ እንኳን ደስ አለህ/አለን፥ ሌላው በዚህ ታሪካዊ ቀን እኛን የቀድሞው የአገር መከላከያ ሠራዊትንና የፖሊስ ሠራዊትን እንደ ሁልጊዜህ አስታውሰህ ስማችንን ስላነሳህልንና እነዚህ የቀን ጅቦቹ አገር አፍራሽና ዘራፊዎች እንደሚያናፉት የደርግ ወይም የኃይለ ሥላሴ ሠራዊት ሳንሆን የኢትዮጵያ ሠራዊት አገራችንንና ወገናችንን በቅንነትና በታማኝነት እናገለግላለን ብለን ቃል ገብተን አገራችን በጠላት እንዳትደፈር የባህር በሯ ተጠብቆ እንዲኖር በአራቱም መዓዘን በመዘዋወር ያገለገልን መሆናችንን ሁልጊዜም በየምታደርገው ዝግጅት ስለምታስታውሰንና ስለምታከብረን እጂግ እናመሰግንሃለን/እንወድሃለን!! እንዳከበርከን እግዚአብሄር ያክብርልን እረጅም እድሜ ከሙሉ ጤና ጋር!!!
አክባሪ የቀድሞው የአገር መከላከያ የባህር ኃይል ሠራዊት ባልደረባ።
ጁኒየር ሌፍትናንት ተረፈ መኰንን