>
5:26 pm - Sunday September 17, 5933

ከዐብይ ጋር መጣላት ይቻላል??? (ሔቨን ዮሐንስ)

ከዐብይ ጋር መጣላት ይቻላል???
ሔቨን ዮሐንስ
አስተዋይ ስትሆን ጠላትህን ወዳጅ አድርገህ ሸክምህን ትጭነዋለህ። ጅል ስትሆን ደግሞ ሸክምህን የሚያግዝህን ወዳጅህን ታሳድደው እና በስጋት ውስጥ ሆነህ ጥላህን ሳይቀር ስትሸሽ ትኖራለህ። ዛሬ ከወደ ዋሺንግተን ያየነውም ይኽንኑ ምሥጢር ነው።
ዶክተር ዐብይ ቅን እና ብልህ ነው። ጠላቶቹን የሚቀንስ ወዳጆቹን የሚያበዛ ! ብዙዎች ወዳጅ ዘመዶቻቸውን ሲሰበስቡ እና ለሥራቸው አጋዥ ሲያደርጉ ዓይተን እናውቃለን። እንደ ዶክተር ዐብይ ጠላቶቻቸውን ሰብስበው ከጎናቸው ማሠለፍ የሚችሉ ግን እጅግ ጥቂቶች ናቸው። አሁን የምደነቀው ከዐብይ ሃሳብ ጋር በሚቆሙት አይደለም። ሰይጣን እንኳን የሚችለው በማይመስለኝ ከዐብይ ሃሳብ ተቃርነው በሚቆሙ ሰዎች እጅግ እደነቃለሁ!!!
ታማኝ ከአብይ ጣምራ ልቦች!!!
 
የፍቅር እና አንድነት የፅናት ተምሳሌት ከሆነው ከባለ ማተቡ ጎንደር አማራ የተፈለፈለው እርግብ ለ27 ዓመት በፅናት እንድህ ብሎ ይጮህ ነበር ። ” አንድ ህዝብ አንድ ባንድራ “በየረገጠበት ምድር ይናገራል ይጮሀል ኢትዮጵያ አንድ ናት አንድ ህዝብ አንድ ባንድራ እያለ መጮሁን አያቆምም በቃ በዚቹ ሀሳቡ ፀና ። ወያኔ ከሚወዳት ሀገሩ ድርሽ እንዳይል ቢያደርገውም ኢትዮጵያዎች በተጎዱበት ቦታ እየረገጠ ማልቀሱንና መጮሁን ድምፅ ማስተጋባቱን አላቆመም ። በቃ አይደክመውም ጥቃት አይወድም ታማኝ በየነ ለሀገሩ ታምኖ የኖረ ነው ።
ታማኝ በየነ ኢትዮጵያዊ ነው ብሔር ሲሉት ኢትዮጵያ ይላል ኦሮሞ ሲነካ ያመዋል አፋርም ሲነካ ያመዋል ትግራይም ስትነካ ያመዋል አማራም ሲነካ ይነስረዋል ብቻ ማንም ሲነካ ያመዋል ።እሱና ደቡብ አፍሪካ ኢትዮጵያን እንዳለ እንደ ጮኸ ባንድራዋን አዝሎ ኢትዮጵያ እንዳለ የተገደለው የቀድሞው ሰራዊት ወታደር ነብሮ አንድ ናቸው ።በቃ ኢትዮጵያ ተደግማባቸዋለች ። ኢትዮጵያን በምንም መልኩ ሳያነሱ አይውሉም ።ታማኝም ሆደ ቡቡና አልቃሻነቱ እንድሁም ደግሞ ለጥቃት እንደ መይሳውና ገብርየ አይበገሬነቱ ይገዳደሩታል ። ታማኝን ለኢትትዮጵያ ህዝብ ማስረዳት ለቀባሪ ማርዳት ይሆንብኛል ። ነገር ግን ዛሬ በሚገባው ቦታ የሚገባውን ንግግር ተናገረ ። ታማኝ አክባሪህ ነኝ!
Filed in: Amharic