ዶ/ር ዐቢይ አህመድ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በሎሳንጀለስ ከዳያስፖራ ማህበረሰብ ጋር ሲወያዩ ከተናገሩት ዋና ዋና ነጥቦች:-
ልሰርቅ ስደራደር፣ ስጠጣና ስቅም ሞቼ አታገኙኝም፤ ለአገር እየሰራሁ ለአገር እየተጋሁ ምንም ዓይነት ሞት ቢመጣ ክብር አድርጌ ነው የምወስደው፡፡
የደህንነት ፍልስፍናው ጠባቂ ህዝብ የሚለው ነው፡፡
ሪፎርመርን እንጂ ሪፎርምን መግደል አይቻልም፤ ያ ቢቻል ኖሮ ኬኔዲ ሲሞት ጆንሰን ተነስቶ ተዓምር ባልሰራ ነበር፡፡
ኢትዮጵያዊነት አሁንም ሱስ ነው፤ ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው ያሉት ፈላስፋ በየቀኑ ስራቸው ኢትዮጵያዊነት ሱስ መሆኑን ያረጋገጡ ምርጥ መሪ መሆናቸውን ላረጋግጥላችሁ እፈልጋለሁ፡፡
ብዙ ጊዜ ራሳችንን ማዕከል እያደረግን እንጂ ሌሎችን በሚያቅፍ መንገድ ማቀድ ስለማናስብ ብዙ የጎደለ ነገር አለ፣ ከተባበርን ግን ይሟላል ብዬ አምናለሁ፡፡
በእንደዚህ ዓይነት በዓላት ኤርትራውያን ወንድሞቻችና እህቶቻችን አብረውን እንዲሆኑ ልባችንን ከፍተን መቀበል ነው፤ እውነት ለመናገር ኤርትራውያን ፍጹም ፍቅር የተሞላባቸው ናቸው፣ ኤርትራውያን እና ኢትዮጵያውያን ምናችንም አይለያይም፣ የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ ከምትሉ ኢትዮጵያ- ኤርትራ ብላችሁ Positive energy ካመነጫችሁ እዚያ ያለውም ይቀየራል፡፡
የኢሕአዴግ ስም መቀየርን በተመለከተ፣ ስምን የሚቀይርና በግብር እዚያው የሆነ ኢሕአዴግ ከሚሆን ግብሩን የሚቀይርና ግብሩ ስሙን የሚቀይር ኢሕአዴግ ይሁን፤ አስቀድመን ስም ቀይረን በግብር እዚያው ከሆንን ያው ኪሳራ ነው፡፡
ሰውን መግደል ሽንፈት ነው፣ ሰው መግደል ውድቀት ነው፣ ሰው የሚገድል ሰው አይደለም፣ የምንገዳደል ሳይሆን የምንተቃቀፍ መሆን አለብን፡፡
ጥያቄ ስንጠይቅ የእኔ ብለን የምንጠይቅ ከሆነ መልሱ ይራዘማል፣ የእኛ ጥያቄ ጠይቀን መልሱን እኛው እንመልሰው፡፡