>

የመድረኩ ንጉስ "ከሞት ጋር ታግሎ" ተረታ!!! (ወሰን ሰገድ ገ/ ኪዳን)

የመድረኩ ንጉስ “ከሞት ጋር ታግሎ” ተረታ!!!
ወሰን ሰገድ ገ/ ኪዳን
በባለቅኔ ፀጋዬ ገ/መድህን ተዓምራዊ ብዕር የተቀረፀውን የአፄ ቴዎድሮስ ገፀ ባህርይ “ነፍሱን አያውቅም”። ሁለመናውን ይነዝረው ያንዘረዝረው ነበር፡፡ በዚህም የተነሳ የ”ቴዎድሮስን የመጨረሻ ስንብት”ቃለ ተውኔት እያነበነበ ሽጉጡን በጣም ወደ ጭንቅላቱ አስጠግቶ ይተኩስ ስለነበር ጆሮው ታውኮ ነበር፡፡
.
በአጭሩ አፄ ቴዎድሮስ እና እሱ በመንፈስ የተጣበቁ ነበሩ፡፡ ዛሬ ከዚህ ዓለም መለየቱን በሰማሁ ጊዜ ከፀጋዬ ገ/መድህን “የቴዎድሮስ ስንብት” የሚከተለው ክፍል ወደ ህሊናዬ መጣ፦
“ሆኖም ጐስቋላ አልምሰልሽ፥ የሚያዝንልኝ አልፈልግም
ጠላትሽን በክንድሽ እንጂ፥ በእንባሽ ወዝ ባላሸንፍም
የልቤን ፍቅር በሰተቀር፥ እማወርስሽም ውል የለኝ
የኮሶ ሻጭ ልጅ ደሃ ነኝ፡፡ …..
ደሞም ያላንቺ የለኝና
ድሌም የተሰፋ ጐሕ ባይሆን፥ ከሞት ጋር ትግል ነውና
ከዚህ ሌላ ትእዝብት ውረሽ፥ ሳይነጋ እንዳስመሸሽብኝ
ጊዜና ትውልድ ይፍረደን፥ ሳልነቃ እንዳስረፈድሽብኝ፡፡
ያም ሆኖ ለራስሽ እንጂ ለኔ ከቶም አታልቅሺ
አንቺ ነሽ እንባ እምትሺ፤ …..” 

ነፍስ ይማር!!

Filed in: Amharic