ከዶ/ር ደብረፅዮን አንደበት የተላለፈ መልእክት ነው
ዳዊት ማሩ
ለመሆኑ የነዶክተር ደብረፅዮን / ሕወሓታውያን / ጠላቶች እነማን ናቸው ?…. ይሕን መልስ ለማወቅ ምንም ማሰብ አያስፈልግም ።
የነዶክተር ደብረፅዮን /የወያኔ / ጠላቶች ፦
* የኢትዮጵያ ወዳጆች ናቸው ፣
* መብታቸው የተዘረፉ የኢትዮጵያ ሕዝቦች ናቸው ፤
* ” ኢትዮጵያ የመቶ ሳይሆን የሺህ አመታት ታሪክና እድሜ አላት ” ብለው የሚያምኑ ናቸው ፤
* ሠንደቅ አላማ የመስዋእትነት ፍሬና የማንነታችንም ምስል መሆኑን የሚቀበሉ ናቸው ፤
* መለስ ዘናዊ ” የአክሱም ሐውልት ለወላይታው ምኑ ነው , ” እንዳለው ሳይሆን ፤ ሀሉም ኢትየጽያውያን….ኢትዮጵያ እራሷ ከዳር እስከዳሯ ” የኔ ናት ። ” ብለው የሚያስቡ ናቸው ፤
* እራሳቸውን ” ወርቅ ዘር ነን ” ብለው የማይኮፈሱ ናቸው ።
የነዶክተር ደብረፅዮን ጠላቶች ፦
* ዘረኝነት የሚዘሩትን፣
* በግፍ ነባር ነዋሪዎችንና ባለርስቶችን ገፍተው የራሳቸውን ወገን ባለ ርስት የሚያደርጉትን እንዲሁም የከተማና የገጠር ነዋሪዎች ላይ የንቅለ-ተከላ ስርአት የሚከውኑትን ፣
* ሕዝብን ከሕዝብ በማጋጨትና በመከፈፋል ስልጣን የሚያደላድሉትን ፣
* በአደባባይ በስናይፐር ሕፃን ገለው ” ባንክ ሲዘርፍ ተገደለ ” የሚሉትን ፤ እንዲሁም ዊክሊንክ እንዳለጋጠው በየታክሲው ቦንብ አፈንድተው ” አሸባሪ አፈነዳብን ” የሚሉትን ፣
* ” ሁሉን ካልጠቀለልኩና ካልገዛሁ ” በሚል። ልክፍት የተመቱትን የሚያወግዙ ናቸው ።
የነደብረፅዮን /የሕወሓት / ጠላቶች ፦
* ኢትዮጵያን እንደ ግል ካምፖኒያቸው በመቆጣጠር ፣ ሕዝቧንም በባርነት በመግዛት የሚዘርፉትን የሚቃወሙ ናቸው ፤
* የዜጋን ጥፍር የሚነቅሉትን ፣ የሚያኮላሹትን ማታ ሲገርፉ አድረው ጠዋት የዳኛ ካባ ለብሰው የፍትህ ወንበር ላይ የሚቀመጡትን የሚያወግዙ ናቸው ፤
* ለውጡን በሐይልና በተለያየ ሴራ ለመቀልበስ እንቅልፍ ያጡትን የሚጠየፉ ናቸው ።
ዶክተር ደብረፅዮን ሆይ ፦ ታዲያ ይሕ ሁሉ ከላይ የተጠቀሱትና ያልተጠቀሱትም የናንተ መአት የወረደበት ሃገርና ሕዝብ ማነኛውም እኩይ ነገር ቢደርስበት እናንተን ከመጠርጠር ውጪ ምን አማራጭ አለው?
ደግሞም ኢትዮጵያን ለ40 አመታት ለማጥፋት የተጋቹ ፣ ኤርትራን ለማስገንጠል ከኢትዮጵያ ሠራዊት ጋር የተዋጋቹ ፣ ኤርትራም ” ነፃነት ወይስ ባርነት ” በሚል አማራጭ እንድትገነጠል ሪፈረንደም ያዘጋጃቹ ፣ ከዚሁም ጋር ተያይዞ የወሎ ክ/ሐገር አንዱ አውራጃ የሆነውን አሰብን መርቃቹ ለኤርትራ በመስጠት ኢትዮጵያን ወደብ አልባ ያደረጋቹ…. የትኛውም አካል ኢትዮጵያ በሚገጥማት አሉታዊ ጉዳይ እናንተን ቢጠረጥር በየትኛው የሞራል ልእልናቹ መውቀስ ትችላላቹ ?