>

በትግራይ ቲቪ የትግራይ ፖለቲከኞች ምን እንደሚያስቡ ግልጽ ሆኗል! (ወንዴ ብርሀኑ)

 በትግራይ ቲቭ የትግራይ ፖለቲከኞች ምን እንደሚያስቡ ግልጽ ሆኗል!
ወንዴ ብርሀኑ
“የትግራይን ጥቅም ለማስጠበቅ ኢትዮጵያ ጋር የግድ መቀጠል ላይኖርብን ይችላል!!
አብርሐ ደስታ
ህገ መንግስቱ ችግር የለበትም። አሁን እየመራን ያለው ህግ ሳይሆን የሆነ ግለሠብ የበላይነት ነው።
አሁን እኛ ቤታችን ትግራይ ላይ ብቻ እንስራ። ተፈላልገን አንድ ሆነን መስራት አለበት።
ክልሉ የፀጥታ ሰራዊት ያስፈልገዋል። ሁላችንም ትግራይ ላይ እናትኩር።”
“በትግራይ expense የምትቆም ኢትዮጵያ የምትባል ነገር አትኖርም!!!
ጌታቸው ረዳ
ህገ መንግስቱ በሚፈቅደው መልኩ መሻሻል ካለበት በፈቅደው መልኩ መሻሻል ይችላል።
የባህርዳር ሰልፍም ይሁን ሌላ ቦታ የታየው ልሙጥ ባንዲራ ከባንዲራው በላይ መታየት ያለበት አላማው intention ከትግራይ አንፃር ምን ነበር ሚለው ነው።
ጀኖሣድ ስጋት ይኖራል ግን እኔና ገዱ እንተዋወቃን ፣ ምናጠፋውም እኛው ነን መሆን ያለብን።
በነገራችን ላይ አማራና ትግሬ አማራና ኦሮሞ ትግሬና ኦሮሞ ህዝቡ ወንድማማች ነው ፀቡ የኢሊቶች (የልሂቃን) ነው።
ህወሀት ተዳክማለች ላላችሁኝ እውነቱን ልንገራችሁአሁን ያለውን ለውጥ ህወሀት ካልደገፈች ትጠፋለች። ሪፎርሙ ግን ካሜሪካ የመጣና በሊስት የሚሰጥ ከሆነ አንቀበልም።”
“እኛ መጀመሪያ የታገልነው የትግራይን ህዝብ ነፃ ለማውጣት ነው!!!
አባይ ፀሀየ
 መወሻሸት የለብንም።ቢያንስ እንደ ኤርትራ ሪፈረደም እናካሂዳለን ብለን ነበር ነገር ግን ትግሉ እየተደላደለ ሲሄድልን ኢትዮጵያን አሰብን።
አሁን ሠፊው የአማራ የሶማሌ የኦሮሞ ህዝብ ጋር አልተጣላንም። ፀቡ መሪወቻችን ባለስልጣናትና የፌስቡክ ቀስቃሾችና አክቲቪስቶች ናቸው….”
ትግራይ ትገንጠል ከሆነ ምታስቡት ንፁህ አጀንዳ ቅረፁና ታገሉ!!!
ዶ/ር አረጋዊ በርሄ
“አዎ ፋኖና ቄሮ ናቸው ይሄን የፈጠሩት። ባንድ ሰው ምክንያትኮ ነው ህግ ተጥሶ ለዚህ የበቃችሁት።
አሁን ለምን ጥርት ያለ አቋም አትይዙም? ትግራይ ትገንጠል ከሆነ ምታስቡት ንፁህ አጀንዳ ቅረፁና ታገሉ።
Filed in: Amharic