>

ቴሌ ከዚህ ሳምንት ጀምሮ የቀድሞ ከፍተኛ ባለስጣናትን ሞባይል ስልክ ቆርጧል!!! (ዘ ሚካኤል) 

ቴሌ ከዚህ ሳምንት ጀምሮ የቀድሞ ከፍተኛ ባለስጣናትን ሞባይል ስልክ ቆርጧል!!!
ዘ ሚካኤል 
 
 እነዚህ ባለስልጣናት ሲጠቀሙ የቆዩት መንግስት በሰጣቸውና በሚከፍለው ስልክ ነበር፡፡ አንዳንዶቹ በወር እስከ 200ሺ ብር ይጠቀሙ እንደነበር ለማወቅ ተቻሏል፡፡
ስልኩ ከተቆረጠባቸው መካከል በረከት ስምኦን፣ ዘርአይ አስገዶም አባይ ፀሀዬ ይገኙበታል፡፡ እንዲሁም ስልኩ ከተቆረጠባቸው አንዱ የሆኑት የቀድሞው የብሮድካስት ባለስልጣን
የነበሩትና “እንዴት የቴዲ አፍሮ እና የሃጫሉ ሁንዴሳ አራት ኪሎ ቤተ-መንግስት ግባ ” የሚለው ዘፈን በሕዝብ ቴሌቭዥን ይተልለፋል በሚል እብሪተኝነቱን በአደባባይ ያሳየው ሀላፊ አቶ ዘርአይ ቴሌ ድረስ በመሄድ ስልካቸው ለምን  እንደተቆረጠ ጠይቀዋል፡፡ የተሰጣቸው መልስም “የበላይ አካል ትዕዛዝ ነው” የሚል ነው::
Filed in: Amharic