>

የጀዋር ማህመድ አዲሱ ካርታ የህልሙ መፍቻ ቁልፍ!!! (ሸንቁጥ አየለ) 

የጀዋር ማህመድ አዲሱ ካርታ የህልሙ መፍቻ ቁልፍ!!!
ሸንቁጥ አየለ 
* ጀዋር የኦነግን ካርታ አሻሽሎ እና አሳድጎ ብሎም አስፋፍቶ አዲስ ካርታ ሰርቶ እያስተዋወቀ ነዉ::
“ሀበሾችን ጢባ ጢባ ነዉ የተጫወትኩባቸዉ” ያለዉ ጀዋር ማህመድ ከአማራ ክልል ሸዋን እና ወሎን ወደራሱ ካርታ ከቶታል::ከደቡብ በርካታ ወረዳዎችን ወደራሱ ካርታ አካቷል::
ከሶማሌ እና ከአፋር በርካታ መሬቶችን ነጥቆ በስልጣኑ የራሱ ካርታ እንዲሆኑ አድርጓል::
በኢትዮጵያ አንድነት የተሰለፉ ሀይሎችም ሆኑ በርካታ በአማራ ድርጅት ዉስጥ የተሰለፉ ሀይሎች ጀዋር “ተስፋፊዎች በመሃል ገቡብን እና እንጅ የኦሮሞ እና የትግሬ ድንበሩ አንድ ነው:: እንዋሰናለን::ተስፋፊዎችን ከመሃል እናስወግዳለን” ብሎ ቃለ መጠይቅ ሲሰጥ ነገሩን ትኩረት አልሰጡትም ነበር::አሁን በአዲሱ የጀዋር ካርታ ኦሮሚያ እና ትግራይ እንዲካለሉ አድርጎ ካርታ ሰርቶ የኢትዮጵያን ህዝብ ጢባ ጢባ ሊጫወትበት በልቡ ዝቷል::
ወያኔ ብዙሃኑን የኢትዮጵያን ህዝብ ሳያሳትፍ የሰራዉ ክልላዊ ካርታ የኢትዮጵያን ህዝብ እያተራመሰዉ እያለ ጀዋር ደግሞ አዲስ ካርታ ሰርቶ ብቅ ብሏል::
የጀዋር አዲሱ ካርታ የጀዋር እዉነተኛ ህልም መፍቻ ነዉ::ጀዋር እስላማዊነት የገነነባትን አዲስ ሀገር ለመፍጠር ቆርጦ እንደተነሳ ገና ድሮ ቁልጭ አድርጎ ነግሮናል::
ጀዋር ሙስሊም ያልሆነ ኦሮሞ ሰዉ ኦሮሞ አይደለም ሲል ቁልጭ አድርጎ ገና ዱሮ የተናገረዉ ሰዉዬዉ በፖለቲካ ታክቲኮቹ ላይ መገለባበጥ ቢታይበትም ካነገበዉ እዉነተና አላማ ግን ፍንክች የማይል ህልሙ ከትልቋ ኢትዮጵያ ይልቅ ታናሿ ኦሮሚያ መሆኑን አዉጆ የተነሳ ነዉ::
ከዚያም ከዚህም መሬት ሰራርቆ ትልቅ ክልል ሰርቶ ያችን ክልል ሀገር ማድረግ ዋናዉ የጀዋር ግብ መሆኑ ነዉ::ትልቋን ኢትዮጵያ አፈር አብልቶ ትንሿን ኦሮሚያን በልቡ የተመኘዉ ጀዋር የፖለቲካ ታክቲክ መገለባበጥ አድርጎ በአፉ ዲሞክራሲ ሲሰብክ በአዲሱ ካርታዊ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ደግሞ ሀገር ማፍረስን እየሰበከ ነዉ::
Filed in: Amharic