>
5:13 pm - Monday April 19, 5171

መደመር እና ደመራ!!! (ዘመድኩን በቀለ)

መደመር እና ደመራ!!!
 ዘመድኩን በቀለ
 በደመራው እንደ መጀመሪያ የሚቆጠር ለጊዜው 10 አብየተክርስቲያናት ተደምረዋል፣ ከ15 በላይ የሚሆኑ የቤተክርስቲያኒቷ አገልጋዮችና ልጆችም በሰይፍ ታርደው፣ በቤንዚል ተቃጥለው ተደምረዋል። ይኼ ለሙከራ ያህል ነው። ዋና ደመራው ገና አልተጀመረም። ይኼ ማማሟቂያ ነው።
~ ይኼን ሐዘን ለማረሳሳትም ከአስመራ ሻአቢያ ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስን ፈትቶ ለኦቦ ለማ በማስረከብ ደመራውን ያዳፍኑታል ተብሎም ይጠበቃል። ይኸው ነው።
 ” የኋለኛይቱ ስሕተት ከፊተኛይቱ ይልቅ የከፋች ትሆናለች።” የማቴ 27፣ 64። ማነህ ባለ ሳምንት?  የምትደመር በስለት በእሳት?
የመደመር + ተረክና ጥንተ ታሪኳ ! 
~ ህውሓት/ ኢህአዴግ 17 ቀን ያኽል በዝግ ሱባኤ መከረ። መከረ፣ መከረና፣ በአዲስ መንፈስ፣ በአዲስ ብቃት፣ እንደ ዘንዶ ቆዳውን፣ እንደ ንሥር ክንፉን አድሶ፣ አራግፎ፣ ቀይሮ ዐይናችን እያየ ጆሮአችን እየሰማ ከች አለ። ከች ብሎም ሀገር ምድሩን የኢህአዴግ ደጋፊ አድርጎት አረፈው።
በ18ቱ ቀን ምክክር ህውሓት የጦስ ዶሮ እንድትሆንና ዋጋ አፈንድትከፍልም ተስማምተዋል። መሳሪያና ገንዘብ እስካላችሁ ድረስ ምንም አትሆኑም። ለጊዜው በቅኔም ቢሆን ስም ሳንጠራ እናንተን እየሰደብን፣ እየወቀስን ካልሆነ በቀር ልናሸንፍ አንችልም። ስለዚህ ህውሓት ጭዳ ሁኚ ተባለች። ኦህዴድ የፓስተሩን ምላስ ለዚህ ትግል መረጠ። ብአዴንም ስልጣኑ አካባቢ ዝር ሳይል ዳርዳሩን ኦህዴድን እያጀበ እንዲያቅራራ ተመደበ። ደቡብ ኖሮም አልጠቀማቸውምና ገለል አደረጉት። ጨዋታው ተጀመረ።
መደመር የሚባል አዲስ መፈክር፣ አዲስ ቀመር ተመረጠ። ማን ከማን ጋር እንደሚደመር አይታወቅም። ብቻ መደመር፣ መደመር፣ መደመር ሆነ። ተባለ። ዐማራውን ለመደመር “ኢትዮጵያ” የሚል ስም ደጋግሞ እንዲጠራ፣ የሚወዳት የኢትዮጵያ ባንዲራን አቅፎ እንዲዘምር፣ እንዲጨፍር አደረጉት። መደመሩ፣ ሻአቢያን ኢህአዴግ አደረገው፣ ግብጽን ኢህአዴግ አደረጋት፣ ኤምሬትስማ በግልጽ ባይነገረን ነው እንጂ የኢህአዴግ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባልስ ሳትሆን ትቀራለች። ኦነግ ከነበታትኔ ዓላማው፣ ኦብነግ፣ ኢህአፓ፣ ደርግ ሳይቀር ዝም ብለህ ተደመር፣ ተባለ። ሁሉም አቅሉን ስቶ ተደመረ።
አዳሜ አሁን ሁልሽም ማኖ ነክተሻል። ተደምረሻልም። አቅልሽንም ስተሽ መደመር፣ መደመር ብለሽ አሽቋልጠሻል፤ ቃል ኪዳንም ገብተሻል። በየወንዙ፣ በየስቴዲየሙ፣ በየአዳራሹ፣ በየእስቴቱ ተደምሬያለሁ። አባቴ ይሙት፣ ከእናቴ ይነጥለኝ፣ ልጆቼን ይንሳኝ ብለሽ ምለሻል። አማምለሻል። በቴሌቭዥን ካሜራ ለሚመጣው 50 ዓመት የሚታይ ፊልምም በእያንዳንድሽ ተሠርቶብሻል። እናም በመደመሩ ተቃዋሚው ከስሮ ኢህአዴግ በዝረራ አሸንፏል። እመኑኝ ኢህአዴግ አሸንፏል። ይኼንንም ደግሞ አቢቹ ደጋግሞ ነግሮናል። ” ኢህአዴግ ደክሟል የምትሉ አላችሁ። ኢህአዴክ አልደከመም፣ አልተዳከመም። እንዲያውም ከመቼውም ጊዜ ይልቅ ተጠናክሮ ነው የሚገኘው። በማለት ነበር አቢቹ ለዲያስፖራውም ለአዲስአበቤውም አስረግጦ የተናገረው። ከምር አድናቂው ነኝ።
~ መደመር የሚባለው ነገር እውነት ከምር መስሎት እንዳይታለል። የትግራይ ህዝብ ፍሬን እንዲይዝና በግርግሩ እንዳይሸወድ፣ እንዳይዘናጋም ህውሓት መቐለ ከትማ ምርጥ ሥራ ሠርታ ህዝቡን እንዳይደመር አድርጋዋለች። ህዝቡም ህውሓት ያቀረበችለትን ያለመደመር ቀመር በሚገባ ተቀብሎ ተግባራዊ አድርጎ ተርጉሞላታል።
~ ምን አልባት ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ልጅ እግር ቢጤ ስለሆነ የመደመር ፍልስፍናውን ከመጠን በላይ ለጥጦት ይሆናል። በዚህ የተነሳም በቀጥታ በሚተላለፉና ኤዲት በማይደረጉ ንግግሮቹ ” የቀን ጅብ ” የሚለውን ንግግሩ ዳህፀ ልሳን ብትሆንም ይህች ቃል ህውሓትን ክፉኛ ጎድታታለች። እነ ደብረ ጽዮን ሳይቀሩ ” የቀን ጅብ ” ማለት እኛ አይደለንም። አቢቹ እኛን ለማለት አይደለም የተናገረው። የኦሮሞ፣ የዐማራ፣ የደቡብም ጅቦችን ለማለት ነው የተናገረው በማለት ዳኽጸ ልሣኗን ለማስተባበልና ህዝቡን ለማረጋጋት እንቅልፍ እስኪያጡ ድረስ ቃሏ ብዙ ሲደክሙም የታዩት ለዚህ ነው።
አሁን የጠ/ሚ ዶኮ ዐቢይ አህመድ የአገልግሎት ዘመን ያበቃ ይመስላል። አቢቹን ከሳሎን ወደ ጓዳ፣ ከጓዳም ወደ መጋዘን ሳይከቱት አይቀርም። ጠሚዶኮ ዐቢይ ከአሜሪካ መልስ ወይ ታሟል። ወይ ታግቷል ስለዚህ አይታዩም፣ አይዳሰሱም። አይናገሩም፣ አይጋገሩም። እየሆነ ያለው ይኸው ነው። ምን አልባት ሰሞኑን ሶማሊያው እልቂት የዳቦ ስም አውጥተው ብቅ ይሉ ይሆናል። ለማንኛውም አቢቹ አሁን ሳይለንት ሙድ ላይ ተደርጓል። ኢንዴዢያ ነው።
★ መደመሩ ወደ ደመራ ሲቀየር ! 
~ በየትኛውም ክፍለ ዘመን በኢትዮጵያ ውስጥ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ሲደረግ፣ ወረራ፣ አመጽና፣ ሰልፍም ሲወጣ ለሰልፉና ለዐመጹ ድምቀት ሲባል ጥንታዊቷን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን #ደመራ ማድረግ፣ በእሳት መለኮስ፣ ማቃጠል፣ ማውደም፣ የቆየ፣ ያለና የነበረ እንደ ቋሚ ሕግ የሚቆጠር ልማድ ነው። አማጺዎች እሷን ካላቃጠሉ፣ እሷን ካልደመሩ፣ አብዮታቸው የሚሳካ አይመስላቸውም። ትኩረትም አያገኙም። እናም ደመራው አሁን ከምሥራቅ ኢትዮጵያ ተጀምሮልናል። ከ10 በላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት #ተደምረዋል። ከ15 በላይ አበው ካህናትና ምዕመናንንም ለደመራው እንደ ችቦ አገልግለዋል። አንገታቸው በካራ እየታረደ፣ ቤንዚል እየተርከፈከፈባቸው ተደምረዋል። ደመራ፣ ደመረ፣ ተደመረ፣ ያው አንድ ነው።
~ ለምስራቅ ኢትዮጵያው ደመራ ከቤንዚል ሌላ፣ ከካህናት ሌላ የዐማራው ነገድ ደምም ያስፈልግ ነበርና አረጋውያን የዐማራ ካህናት፣ የዐማራ ዲያቆናት ተፈልገውና ተመርጠው  አንገታቸውን በቢለዋ ታርደው፣ ቤንዚን ተርከፍክፎባቸው ከተደመረችው ቤተክርስቲያን ጎን እነሱም በእሳት ተቃጥለው እንዲደመሩ ተደርገዋል። አረሩ፣ ከሰሉ፣ ዐመድም ሆኑ። በረከታቸው ይድረሰን።
~ እዚህ ላይ በዚህ ደመራ ላይ የኦሮሞ እና የትግሬ ነገዶች እንዲጎዱ አልተደረገም። ትግሬዎቹ በደማሪዎቹ ጥበቃ ተደርጎላቸዋል ተብሏል። ኦሮሞዎቹም አስቀድመው እንዲወጡ ተደርገዋል። ያኔ ኦሮሞዎቹን ሙልጭ አድርገው ከሶማሌ ክልል ሲያስወጡ የጠረጠረ አንድም ሰው የለም። ኦሮሞ ራሱን ለማጠናከርና ቀጣዩ ገዢ መደብ ሆኖ ለመውጣት ሲል የተፈጸመ የፖለቲካ ሴራ ነው የሚሉ አሉ። ለዚህም ማሳያ የሚሆነው ደግሞ ክርስቲያን የሆነውን የሸዋ ኦሮሞ በሙስሊም ኦሮሞ ለመተካት የተደረገም ሴራ ነው የሚሉ አሉ። እናም ተፈናቃይ የተባሉትን በሙሉ ከምስራቅ ኢትዮጵያ አንስተው በማምጣት የሸዋ ክርስቲያን ኦሮሞን መሬቱን ቀምተው አስፍረውበታል። ያኔ ኦሮሞ ከሶማሊያ ይውጣ ሲባል ዐማራው አልገባውም ነበር። ጭዳው ዐማራ፣ በጉ ዐማራ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ እረፍት እነሳዋለሁ እንዳለችው ህውሓት ዕቅዷን በሚገባ አሳክታለች።
~ ወዳጄ ደመራው አሁን ወደ ድሬደዋ ደርሷል። ከድሬደዋ አልፎ እንደማይመጣ ምንም ማረጋገጫ የለህም። ህውሓት ኦርቶዶክስ የዐማራው መገለጫ ነው ብላ 27 ዓመት ሙሉ በአቢዮታዊ ዲሞክራሲ ስብከት ያጠበመቀቻቸው ሁሉ አሁን ያንን ጠላት ፣ ጨቋኝ የተደረገን ዐማራና፣ የዐማራ ምልክት ነውና መጥፋት አለበት የተባለው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መጥፋት አለባቸው በተባለው መሰረት ይኸው በሶማሊያ በስፋት በተጠና መንገድ ተፈጽሟል።
~ ጠሚዶኮ ዐቢይ እንዲናገር እንጂ፣ እንዲሰብክ፣ እንዲያወራ ፣ እንዲያስጨበጭብ እንጂ ምንም ነገር እንዲያዝ ሥልጣን እንደሌለው በጅጅጋው ድርጊት አይተናል። አለቀ በቅርቡ ቁጥር ሁለት ጅጅጋ የት እንደሆነ መጠበቅ ብቻ ነው። ተመልከቱ አብያተ ክርስቲያናቱ በሙሉ ተቃጥለው ምድረ በዳ መሆናቸው ከተረጋገጠ በኋላ መከላከያው እንዲገባ፣ አብዲኢሌም በፈቃዱ ስልጣኑን ለቋል እንዲል ተደረገ። ይኽቺ ናት ጫዋታ። እናም ደመራው ይቀጥላል። ደመራ፣ ደመራ፣ ደመራ።
~ አሁን ዲያስፖራው ማኖ ነክቷል። ጠሚዶኮ ዐቢይ አህመድ በእጅ በእግር ገብተው የህዝብ ድምጽ የነበረውን የዲያስፖራውን ማኅበረሰብ በ12 ቁጥር ሚስማር ቀርቅረውለታል። ያውም እንዳይላወስ አድርገው ነው የቀረቀሩለት። አሁን ዲያስፖራው አፍ የለውም። አፉ በፕላስተር ሳይሆን በላሜራ ተበይዶ ተለጉሟል። ዲያስፖራው አይናገር፣ አይጋገር፣ ዝም፣ ጭጭ ፣ ጮጋ ብሎ እንዲደመር ተደርጓል። ተደምሯል፣ ተደምሯል፣ በቃ ተደምሯል። አሁን አይደለም በጅጅጋ የሚሞት ሰው፣ የሚቃጠል ቤተክርስቲያን፣ የሚታረዱ ካህናትና ምእመናን የኢትዮጵያ ህዝብ በሙሉ በእሳት፣ በጥይትና በሰይፍ በአውቶሚክ ቦንብ ጭምር የሚጨርሰው አካል ቢመጣ ዲያስፖራው አሁን ትንፍሽ አይላትም። ምንስ አፍ አለውና ይተንፍስ። አቢዬ ለኔ፣ አቢዬ ለኔ አንተን ያያ አይኔ ሌላ፣ ሌላው ለምኔ ብሎ እኮ ሌላ ላለማየት በዘፈን መኃላውን አረጋግጧል።
አስሬ ለክቶ አንዴ የሚቆርጥ ይመስለኝ የነበረው አክቲቪስት ታማኝ በየነ እንኳ ስለተደመረ አሁን የመቃወም ወኔው ተሰልቧል። ሼም ኦን ዩ ማለት የለም። አቢቹ ታማኝን ያህል ቆራጥ፣ ብልህ ይመስል የነበረን ሰው በዋሽንግተን ምድር መሬት ለመሬት አንበርክኮታል። አሰግዶታል። እናም አሁን አዳሜ ከዝም፣ ጭጭ በቀር ወሬ የለም። ግንቦት ሰባት አንዳርጋቸው ጽጌን አስፈትቶ ሌሎች አባላቱን በእስርቤት ሲማቅቁ ቢያይም እሱ ደንታው አይደለም። ምክንያቱም ተደምሯላ።
~ የመደመሩ ስሌት ስንት የተለፋበትን የHR128 ጉዳይ አፈር ከድሜ አብልቶታል። በአጠቃላይ መደመሩ ዲያስፖራውን ጢባጢቤ ተጫውቶበታል። ለወትሮው አንድ ሰው ሲሞት፣ ሲገደል መላውን አለም ያንቀጠቅጥ የነበረው የዲያስፖራ ማኅበረሰብ አሁን ሼም ይዞት ከ50 በላይ ሰው በሶማሊያና በድሬደዋ፣ ከ10 በላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተክርስቲያናት ከነ አገልጋይ ካህናቶቿ እንደ በግ ታርደው እንደጧፍ ሲነዱ ቢያዩም አንዳቸውም ትንፍስ አላሉም። ምንስ አፍ አላቸው?
~ ሌባው፣ ነፍሰገዳዩ፣ ዘራፊው የማይጠየቅበት ” መደመር” ገና ብዙዎችን ሳይረመርም በቀላሉ አይፋታንም። አብዲ ኢሌ ይኽን ሁሉ የዘር ማጥፋት ፈጽሞ አንዳች የሚጠይቀው ኃይል የለም። ምክንያቱም መደመር ነዋ።
“#የመደመሩ” ትርጉም ስናጠቃልለው መደመር የተሰኘው የአቢቹ ቀመር ለኦርቶዶክሳውያን የተዋሕዶ ልጆችና ለዐማራው ነገድ አባላት መደመሩ “ደመራ” መሆኑ ተረጋግጧል። ደመራው በሶማሌ ክልል ብቻ ያበቃል ብላችሁ አትጠብቁ። ደመራው በቀጣይም በሌሎቹ የሀገሪቱ ክፍልም ይቀጥላል።
ትግራይ የራሱ ጦር አለው። ሶማሌም የራሱ ጦር አለው። ኦሮሞም የራሱ ጦር አለው። አፋር ከነ መሳሪያው ነው። ቤኒሻንጉልና ጋምቤላ በህውሓት ጦር የተደራጀ ነው። ደቡብ ብቻ ነው ዘብረቅረቅ ያለ ነገር ያለው። ዐማራው ግን ከእግዚአብሔር በቀር ምንም ነገር የለውም። ዐማራ ራሱን መከላከል እንዳይችል እንኳ በሚቀጥለው ዓመት በድኗ ብአዴን በዐማራው እጅ የሚገኘውን ራስን መከላከያ መሣሪያ በዘመቻ ልታስፈታው ዕቅድ አውጥታ ቅድመ ዝግጅቷን አጠናቃለች። ከዚያ በሚልየን የሚቆጠር ዐማራ የመስቀል ደመራ ሆኖ ያልቃል። ይሄ የእነሱ እቅድ ነው።
ፎቶ መግለጫ
1- ጃዋር ወደ ሀገር ቤት ገብቷል። ስለቱም ሰምሮለት በባዶ እግሩ የቄሮን የትግል ሜዳ ረግጧል።   ለኢንጅነር ስመኘው ሹፌር የነፈገች ሀገር ለጃዋር ጦር ሰራዊት መድባ ታስጥበቀዋለች
2 ጠ/ሚር ዶ/ር አብይ በኢንጅነሩ ጉዳይ ከአሜሪካ መልስ መግለጫም አልሰጡ ለቅሶም አልደረሱ። ለታክቲክ ይሁን በእገታ ብቻ እንጃ ድምጻቸው ጠፍቷል።
 
3 ጃዋር አዲስ ካርታም አስተዋውቋል። ኦሮምያን ከትግራይ ጋር ድንበርተኛ አድርጓታል።
 
ሻሎም !  ሰላም !
ነሐሴ 1/2010 ዓም
ከራየን ወንዝ ዳር።
Filed in: Amharic