>
5:14 pm - Tuesday April 20, 6771

በሶማሊያ ክልል የጅምላ ዘር ማጥፋት ጄኖሳይድ ነው የተፈጸመው!!! (ታደለ ጥበቡ)

በሶማሊያ ክልል የጅምላ ዘር ማጥፋት ጄኖሳይድ ነው የተፈጸመው!!!
ታደለ ጥበቡ
የግራኝ አህመድ ሰይጣናዊ ርዝራዦች በቤተክርስቲያናችን እና በምዕመናን ላይ ያደረሱብን ግፍ ታሪክ የማይረሰው ነው።
የሰውን ልጅ በእሳት ማቃጠል፤ቤተክርስቲያንን ማወድም ከisis የማይተናነስ የሽብር ተግባር ነው።አሁን መልሰን ቤተክርስቲያናችን ማነጽ ይገባናል።ሶማሌ ክልል ለሚኖሩ ምዕመናንም ከጎናቸው የምንቆምበት ወቅት ነው።
~ ዝምታው ይብቃ !  ድምጻችን ይሰማ !  ኢትዮጵያዊ የሆነ ሁሉ እስላም ክርስቲያን ሳይል ድርጊቱን ያውግዝ።አሁንም አስቸኳይ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ስደተኞች በፍጥነትና፣በስፋት ይረዱ።
~ መንግሥቱ ይኽ ዘግናጭ የዘር ጭፍጨፋ ተሰምቶት አንዳች ነገር ካለደረገ ግን ሌላ የደረሱኝን ዘግናኝ መረጃዎች ለመልቀቅ እገደዳለሁ። ለማናችንም የማይጠቅም ዘግናኝ ነገር አልኳችሁ። ለዐቢይ አህመድ መንግሥት መልእክቴን አድርሱልኝ። ኦርቶዶክሳውየን ተዘጋጅታችሁ ራሳችሁን ጠብቁ። አከተመ ።
~ የፌደራሉ መንግሥት ዐማራ ሲበደል፣ ኦርቶዶክስ ስትወድም ግድ የሚሰጠው ስለማይመስለኝና የሐዘን ቀኑን ስለማይፈጽም በዐማራ ክልል የምትገኙ ዜጎች በክልላችሁ ውስጥ ከቻላችሁ ባንዲራውን ዝቅ አድርጋችሁ አሳዩን።
~ የመምህራኖቹ ላፕቶፖች የማስተማሪያ ቁሳቁሶችና መኖሪያ ቤቶቹ ስለወደሙ የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲም ሊዘጋ መሆኑን መምህራኑ መረጃውን አድርሰውኛል። እዚያም ጭንቅ ላይ ናቸው። በረሃብና በውኃ ጥም።
~ አሁን በኢትዮጵያ ውስጥ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኙና የዐማራው ነገድ ከሌሎቹ ብሔር እኩል የሚቆጠሩ ከሆነና ሕገመንግሥቱም እንደ ኢትዮጵያዊ ዜጋ የሚያያቸው ከሆነ አሁን በሥልጣን ላይ ያለው የኢትዮጵያ መንግሥት በአስቸኳይ የ3 ቀን ብሔራዊ የሐዘን ቀን በመላ ሀገሪቱ ያውጅ። የምን ደባብቆ፣ ሸፋፍኖ ማለፍ ነው። ጥፋቶችን ሁሉ በቀን ጅብ እያሳበቡ ማምለጥ ከተጠያቂነት አያድንም።
~ በመላ ሀገሪቱና የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች፣ ቁንስላ ጽሕፈት ቤቶች ባሉባቸው ሀገራትና በኢትዮጵያ ንግድ መርከብ ላይ የሚውለበለብ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ለ3 ቀን ዝቅ ይበል። ዐማራና ኦርቶዶክስ የሀገሪቱ ዜጎች መሆናቸውን መንግሥቱ ከልቡ የሚያምን ከሆነ ይኽን ያድርግ።
~ በጅግጅጋ የተፈጸመውን ዘግናኝ የዘር ማጥፋት ድርጊት የኢትዮጵያ መንግሥት በአስቸኳይ የወንጀሉን ፈጻሚዎች በቁጥጥር ስር ያውል። አስቸኳይ ፍርድም የሀዘን መግለጫም ይስጥ።
~ የዐማራ ወጣትና ህጻናት ልጃገረድ ሴቶች በእናቶቻቸው ፊት በግሩፕ ተገደው ተደፍረዋል። እናቶች ተፈንክተዋል፣ አባቶች ተቀጥቅጠው ተፈንክተዋል። ህጻናት ያለወላጅ ቀርተዋል። ንብረት በሙሉ ወድሟል። ካህናት ዲያቆናት መታረዳቸው ሳያንስ በእሳት ተቃጥለዋል።
~ መንግሥት ቅዳሜ ችግሩ ተፈጥሮ እስከ ትናንት ሐሙስ ድረስ በጅግጅጋ ቅዱስ ሚካኤል የተጠለሉ ክርስቲያኖችን ሊረዳ አልፈቀደም። መከላከያውን ዘግይቶ ነው የላከው። ቀይ መስቀል ትናንት ሐሙስ ነው በቦታው የደረሰው። አሁን ጥቂት ሩዝና መጠነኛ ድንኳን ማደል የጀመረውም ትናንትና ከሰዓት በኋላ ነው። አሁንም መንግሥቱ በቂ ትኩረት ለዐማራውና ለኦርቶዶክሱ አልሰጠም።
~ ይኼ የጅጅጋው አይነት የዘር ማጥፋት ችግር ትግራይም ጎንደርም፣ ወሎና ጎጃም ወለጋና ጅማ በቀጣይ የማይመጣ፣ የማይደርስ መስሎህ ከታየህ አንተ ሞኝ ነህ። አዎ ተዘልለህ አትቀመጥ። አሁን መፍትሄ የሚያስፈልግበት ወቅት ነው።
~ ይኽን ጥፋት ያዘጋጀው ህውሓት ነው። አብዲኢሌን አሰልጥኖ ለዚህ ያበቃው ህውሓት ነው። አብዲ ኢሌ ያሰባሰባቸው ወጣቶች ስልጠና የወሰዱት በህውሓት ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦች እንደሆነ የመረጃ ምንጮቼ ይናገራሉ። ወጣቶቹ ልክ እንደ ቄሮ፣ ፋኖና ዘርማ ለእነዚህም #ሄጎ የሚባል ስያሜ ነው አብዲኢሌ የሰጣቸው። ወጣቶቹን የጅጅጋዎቹን ሌላ ከተማ፣ በሌላ ከተማ ያሉትን በጅጅጋ በተጠና መልኩ ይህን ዘግናኝ ድርጊት እንዲፈጽሙ አድርገዋቸዋል። የሶማሌ ልዩ ኃይል ተብዬውም ሽፋን ከመስጠት አንስቶ የሚቃጠሉትን ክርስቲያኖች አንዳንዶቹን ከመታረዳቸው በፊት በጥይት የሚጥልላቸው እሱ እንደነበረ ነው የተነገረው።
~ አብዲ ኤሌ ብቻ መታሰሩ መፍትሄ አይሆንም። ይኽን ዘግናኝ ጭፍጨፋ የፈጸመን ግለሰብ ለምን ይነካል ሲሉ የነበሩና ከፍተኛ ጭቅጨቃ፣ ከለላ፣ ውትወታ ሲያደርጉለት የነበሩ በትግራይ ስም የሚነግዱ ህውሓቶችና አክቲቪስቶችም በሕግ መጠየቅ አለባቸው። አዎ መጠየቅ አለባቸው። አብዲኢሌ እንደሆነ ነገ አምባሳደር ተደርጎ መሾሙን እንሰማለን። የጉድ ሀገር።
ማስታወሻ ~ ለኦርቶዶክሳውያን የተዋሕዶ ልጆች በሙሉ።
በቀል የእግዚአብሔር ነው። እኛ ማንንም አንበቀልም። ፍትሕ ግን እንፈልጋለን። ፍትሕ ! ፍትሕ !  ፍትሕ !
~ ነባሩ እስልምና በምንም አይነት ይኼን ዘግናኝ ድርጊት እንዳልፈጸመ መቶ በመቶ ማረጋገጥ ይቻላል። እንኳን እስልምና ነባሩ የሶማሌ ነዋሪ በድርጊቱ ክፉኛ ደንግጧል። ብዙ ዐማራዎችን በቤታቸው ደብቀው ያተረፉ፣ እስከአሁንም አስጠግተው ያሉ ሙስሊም ሶማሌዎች እንዳሉ የመረጃ ምንጮቼ ገልጸውልኛል። እናም ችግሩ ያለው አስተዳደሩ ላይ ብቻ ነው። መጠየቅም፣ መሟገትም ያለብን አስተዳደሩ ላይ ብቻ ነው። እናም እስልምናን አንኮንንም። በእስልምና ስም የተፈጸመውን ወንጀል ግን ሙስሊም ኢትዮጵያውን በሙሉ ሊያወግዙት ይገባል።
~ ነባሮቹ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችም ልክ እንደኛው ተጠቂዎች ከሆኑ ሰነባብተዋል። ትናንት በኮምቦልቻ ወሎ በእስላሞቹ መስጊድ ውስጥ የተፈጸመውን ዘግናኝ ጭፍጨፋ መመልከት ብቻውን በቂ ነው። እናም ጊዜው ነባሩ እስልምናና ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች በጋራ ቆመው ሀገሪቷን የሚታደጉበት ጊዜ ነው ባይ ነኝ።
~ ሌላው በሶማሊ ክልል አሁን ከሞት የተረፉትን ስደተኞች በስልክ ሳነጋግር የሚሰጡኝ መልስ የሚያስለቅስ ነው። እኔ በአብዛኛው የምጠብቀው ስለተደፈሩት ሴት ልጆቻቸው፣ ስለወደመው ንብረታቸው፣ ስለጠፋው ሀብታቸው ይቆጫሉ፣ ይንገበገባሉ ብዬ ነበር የምጠብቀው። እነሱ ግን በሚገርም ሁኔታ የሚያንገበግባቸው የአብያተ ክርስቲያናቱ መቃጠል ነው። የካህናቱ መታረድ ነው። ” አሁን ገንዘብ የለን በምንና እንዴት አድርገን መልሰን እንሠራቸዋለን ነው የሚሉት። እናም የእምነታቸው ጽናት ይገርማል። አቦ እንኳንም ክርስቲያን ሆኜ ፈጠርከኝ ያስብላሉ።
~ እኔም አልኳቸው አብያተክርስቲያናቱ ከቀድሞው በማረ መልኩ በኢትዮ ሶማሊያ ምድር ዳግም በቅርብ ጊዜ በመላው ዓለም ላይ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ርብርብ በአጭር ጊዜውስጥ ተመልሰው ይሠራሉ። ይኽ ቃሌ ነው። መጀመሪያ ግን ፍትሕ !  ፍትሕ !  ፍትሕ ! ። አስቸኳይ ጥበቃና እርዳታ ለጅጅጋ ክርስቲያኖች። አበቃሁ።
ለሞቱት ነፍስ ይማር!!
Filed in: Amharic