>

እጣቸው ላይለያይ የተጋመደው ሁለቱ ህዝቦች !!!  (ዘጋቢ፡-ግርማ ተጫነ)

እጣቸው ላይለያይ የተጋመደው ሁለቱ ህዝቦች !!!
 ዘጋቢ፡-ግርማ ተጫነ
የኦሮሞን እና የአማራን ህዝቦች አብሮነትና ቀጣይነት  የመወሰን አቅም ያላቸዉ ሁለት ወሳኝ ሰወች ዛሬ ባ/ር ገብተዋል። እድሉን በሚገባ እንጠቀምበት።
” ዛሬ ነሀሴ 3 ቀን 2010 ዓ.ም የOMN ስራ አስኪያጅ አቶ ጀዋር መሀመድ እና የስራ ባልደረቦቹ ወደ አማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት መዲና  ባህር ዳር አቅንተዋል:: በቡድኑ ውስጥ አቶ ኤልያስ ኢብሳ፣ አቶ ኪታባ መገርሳ፣ ፕሮፌሰር ህዝቄል ገቢሳ፣  አቶ ደረጀ ሀዋዝ፣ አቶ አቦማ ተርፋሳ እና የOMN ጋዜጠኞች ተካተዋል::  የክልሉ አመራሮች አቀባበል አድርገናል::
ክልላችን ከOMN ጋር በሚሰራቸው ስራዎች ላይ ከከፍተኛ አመራሮች ጋር ውይይት ያደርጋሉ” ::
በማለት አቶ ንጉሱ ያሰራጯትን አጠር መጠን ያለች መልእክት ተመለከትኩ። ጉዳዩ ሰሞኑን ሲነሳና ሲወድቅ እንደነበር ባዉቅም እንግዶቹ ዛሬ ባ/ዳር እነደገቡ ያወቅኩት ግን የንጉሱን መልእክት ካየሁ በሁዋላ ነዉ።
የነዚህን እንግዶች ወደክልላችን  መምጣት ተከትሎ አንዳንድ አስተያየቶችን አይቻለሁ; በድጋፍም በተወሰነ መልኩ ደግሞ ነቀፌታ የሚመስሉም ነገሮች። ይህም ግን በክፉ የሚታይ አይደለም።
እኔ በበኩሌ እንደ አንድ የአማራ ፖለቲከኛ; የፕሮፌሰር እስቂያስንና የጀዋር መሀመድን ወደ አማራ ክልል መጥቶ ከአማራ ጋር ለመወያየት መወሰናቸዉን እጅግ ወድጀዋለሁ። ለምን? እነዚህን ሁለት የኦሮሞ ፖለቲከኞች ፖለቲካዊ አመለካከት; አማራን የሚመለከቱበትን መነጽር ቢያንስ ከ2008 አ.ም ጀምሮ በጽሞና ተከታትያቸዋለሁ። በተለይም ጀዋር አማራንና የጎንደርን አብዮት አስመልክቶ ከኢሳት ጋር ያደረገዉን ዉይይት ; እንዲሁም ፕ/እስቂያስ ከኛዉ አቻም የለህ ታምሩ ጋር አማራን በሚመለከት ያደረጉትን ዉይይት ደጋግሜ አዳምጨዋለሁ።
በእኔ እምነት ሁለቱም ዉይይቶች እጅግ ጠቃሚ ነበሩ። በተለይም የኦሮሞ ፖለቲከኞች የአማራን ፖለቲካና አማራን እንደ አጠቃላይ እያዩበት የመጡበትን መንገድ; አሁንም ያላቸዉን እይታ ;ለወደፊትም ምን መሆን አለበት ብለዉ እንደሚያስቡ በግሌ ጥሩ ግንዛቤ አግኝቸበታለሁ።
ስለሆነም ለአማራ ክልል አመራር እነዚህን ታዋቂ የኦሮሞ  ፖለቲከኞች በአካል አግኝቶ ለ 1 ቀን  መወያየት መቻል; ከኦህዴድ ጋር ለ 27 አመት ያክል ተወያይቶ ከመጣዉ ዉጤት ይበልጣል ባይ ነኝ።
ስለሆነም እነዚህ ሁለት ሰወች ;በቀጣይ የአማራንና ኦሮሞን ህዝቦች ግንኙነት በመወሰን በኩል ወሳኝ ድርሻ( ምን አልባትም ከኦህዴድ በበለጠ-) እንዳላቸዉ መገንዘብ አለብን። ስለሆነም እነዚህን ወንድሞቻችንና ቡድናቸዉን  ወደ ክልላችን እንኳን ደህና መጣችሁ ብለን ፍጹም ልባዊ በሆነ ወንድማዊነት ልንቀበላቸዉ ይገባል።
ይህ ማለት ግን የዉይይቱ ተሳታፊወች ; በሁለቱ ፓለቲከኞች ላይ ስላላቸዉ ትዝብት; የአማራን ህዝብ በተመለከተ ስላላቸዉ እይታ; ኦሮምያ ዉስጥ የሚፈናቀሉ አማራወች ጉዳይና ይህ ድርጊት ስለሚቆምበት ጉዳይ; በኦሮሞና የአማራ ህዝቦች ቀጣይ ግንኙነት; ግንኙነቱን በማጠናከር በኩል ከነሱ ሰለሚጠበቅ ድርሻ; ወዘተ…የመሳሰሉትን ጥያቄወች አንስቶ መወያየት አይገባም ማለት አይደለም; እንዴዉም በዚህ መድረክ በነዚህ ነጥቦች ዙሪያ; በተቻለ መጠን ከነዚህ ወገኖች ጋር ተማምኖ መዉጣት ይገባል።
እመኑኝ የቀጣዩን የኦሮሞና የአማራን ህዝቦች መልካም ግንኙነት በመወሰን በኩል እነዚህ ወገኖች ሚናቸዉ ከባድ ነዉ; ትልቅ ትርጉም ሰጥተን ልናየዉና እድሉን በበጎ ተመልክተን ዉይይቱን ለበጎ ዉጤት እንዲበቃ የየቨኩላችንን ድርሻ እናበርክት።
የኦሮሞና አማራን ህዝቦች አብሮነትና አንድነት ተጠናክሮ ማየት የሚፈልግ ሁሉ ለዚህ ዉይይት መሳካት; ከሱ የሚጠበቀዉን  አስተዋጽኦ ከማድረግ ሊቆጠብ አይችልም።
ባሕር ዳር፡ነሀሴ 04/2010 ዓ.ም(አብመድ)  የኦሮሚያ ሚድያ ኔትወርክ ስራ አስኪያጅ እና አክቲቪስት ጀዋሪ ሙሃመድ  በባሕር ዳር አቫንቲ ብሉ ናይል ሆቴል ተገኝቶ ከወጣቶችና ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት እያካሄደ ነው፡፡
አክቲቪስት ጀዋሪ ሙሃመድ  በውይይቱ መክፈቻ ካደረገው ንግግር የተቀነጨበ፦
 
* ‹‹ባለፉት ዓመታት አማራ እና ኦሮሚያን ለመከፋፈል እሳት እና ጭድ ያቀበሉን ሙተንም ቢሆን አሁን የምንፈልገው ኢትዮጵያዊነት ላይ ደርሰናል።›› 
*  በራሳችን መፋቀድ በዚህ ፍጥነት ተቀራርበን በመስራታችን መሰረት ለሆኑ ህይወታቸውን ላጡ ዜጎች ታላቅ ምስጋና አለኝ።
* ለውጡን እውን ለማድረግ ተቀራርበን መስራት ይስፈልጋል። ለዚህም ነው ለለውጡ ከፍተኛ መስዋዕትነት ከከፈሉ ህዝቦች ጋር ለመወያየት የመጣሁት ።
*  ባለፉት ዓመታት አማራ እና ኦሮሚያን ለመከፋፈል እሳት እና ጭድ ያቀበሉን ሙተንም ቢሆን አሁን የምንፈልገው ኢትዮጵያዊነት ላይ ደርሰናል።
*  የሁለቱ ህዝቦች መቀራረብ እንደ አባት እና ልጅ ነው። ምሁራን እና አክቲቭስቶች ህዝቡን ለማቀራረብ መስራት የሚያስፍገን ጊዜ ነው።
የኦሮሚያ ሚድያ ኔትወርክ ስራ አስኪያጅ እና አክቲቪስት ጀዋሪ ሙሃመድ በብሉ ናይል ሆቴል ውይይቱ ተሳታፊዎች የተለያዩ ጥያቄዎችን ምላሽ ሰጥቷል።
ጃዋር መሀመድ በባህርዳር ካደረገው ንግግር የተቀነጨበ
 በጋዜጠኛ ( የሺሀሳብ አበራ )
የአማራ ብሄርተኝነትን የሚሰጋ ሰው ካለ የአማራን ጥያቄ ያስመልስ፡፡ ወልቃይትን ካስመለሰ፣አማራ በአማራነቱ አይቁም የሚል አማራን  እንዳይጠቃ ያድርግ፡፡ያ ሳይሆን የአማራን ብሄርተኝነት መስጋት ነውር ነው፡፡
ካርታን  በተመለከተ በ 1973  የተሳለ ነው፡፡እኔ እውቅና  የለኝም፡፡ ሁለታችን ለማጣላት እንድንጠራጠር ለማድረግ ታቅዷል፡፡የዛ ውጤት ነው፡፡
አማራ በኦሮሞያ ሁለተኛው ብሄር ነው፡፡ውክልና እንዲያገኝ በጋራ እንስራ፡፡እንሰራለን፡፡
አማራ እና ኦሮሞ እሳት እና ጭድ  ናቸው ስንባል ክብሪት አንጭርም፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ቀይ ካርድ ሆኗል፡፡አዲስ አበባ  የአዲስ አበባን  ናት፡፡አዲስ አበባ የከተማው ነዋሪ  መብት ይጠቀም፡፡በአዲስ አበባ ዙሪያ ያለው ኦሮሞ ግን ዘበኛ ሆኗል፡፡አዲስ አበባ የኦሮሞን አርሶአደሮች መብት ማክበር አለባት፡፡ የኦሮሞ አርሶአደርን መብት እናስጠብቃለን፡፡
..
 ወልቃይት  ጉዳይ በጠብመንጃ  አይታፈንም፡፡በዚህ ጉዳይ በጋራ እሰራለሁ፡፡እነ ኮሌኔል ማሰር ሰይጣናዊ ስራ ነው፡፡
..
ኮሌኔል ደመቀን በጣም አከብርሃለሁ፡፡
የወልቃይት ጥያቄ ይቀጥል፡፡
በህዝብ የተመረጠ መንግስት መጀመሪያ ይቋቋም፡፡ህገመንግስቱ ሆነ ሌላው በህዝብ  ምክክር የወጣ አይደለም፡፡
ግን አሁን  ህገመንግስት መቀየር ለአሁን ጥያቄ መሆን የለበትም፡፡ የምርጫ ህጉ ቀድሞ ይሻሻል፡፡
ለሁላችንም የሚሆን ስራዓት እንፍጠር!!
የባንዲራ ጉዳይ  የህዝብ ስሜት ይደመጥበት፡፡
የአማራ እና የኦሮሞ ህዝብ በተፈጥሮ አይነጣጠልም፡፡ሁለቱን ህዝቦች በመነጣጠል አይሆንም፡፡ነገር ግን የሃይል ፍክክር ውስጥ ናቸው፡፡መሆንም አለበት፡፡ እሳት እና ጭድ ሲሉን ሳያቃጥሉን ቀድመን አንዳላጥናቸው ።
Filed in: Amharic