ነብዩ ሲራክ
* ሳውዲዎች ትልቁን ባለስልጣን ወደ ኢትዮጵያ ልከዋል !
* የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አድልን ዶር ወርቅነህ ተቀብለዋቸዋል
* ንጉሱ ዶር አብይ ማምሻውን ከሚኒስትር አድል ጋር ተገናኝተዋል
በንጉስ ሰልማን ቢን አብድልአዚዝና በልጃቸወ በአልጋዎራሽ ልዑል መሐመድ ቢን ሰልማን የሚመራው የሳውዲ መንግስት ለአዲሱ በዶር አብይ አህመድ ለሚመራው የአሁኑ የኢትዮጵያ መንግሰት ከፍ ያለ አክብሮት እንዳለው አውቃለሁ ። ሳውዲዎች ለድጋፍ አክብሮት ማሳያ አንድ አካል የሆነ በታላላቅ ባለስልጣኖች የሚመራ ልዑክ ወደ ኢትዮጵያ ልከዋል ። ጠቅለል ሲል በዜና አንደሰማንው በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አደል ቢን አህመድ አል ጁቤር የሚመራው ልዑካን በቀጠናዊ እና የሁለትዮሽ ትብብርን በተመለከቱ ጉዳዮች ዙሪያ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶር ዐቢይ ጋር ይመክራሉ ተብሏል ።
ልብ በሉ ! ከልዑላን ቤተሰብ ውጭ ሆነው በሳውዲ ፖለቲካ ዘዋሪና ፈጣሪ አድራጊ ፣ የንጉሱና አልጋ ወራሹ አማካሪ ብቸኛ የምላቸው ታማኝ ከፍተኛ ባለስልጣን አደል ጁቤር ናቸው ብል ማጋነኔ አይምሰላችሁ ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አድል በንጉሳዊው የቤተብ አስተዳደር ጀምሮ እስከ ተራው ሀገሬ ተሰሚነት ያላቸው ብርቱው ፖለቲከኛና ዲፕሎማቱ አደል የኢትዮጵያ ጉብኝት ተስፋው ብዙ እንደሆነ ጠቋሚ መረጃ አለኝ ።
ከሳምንታት በፊት የምሰራበት ኩባንያ ውስጥ ከከፍተኛ ኃላፊዎችና ከባለቤቶቹ ጋር ስብሰባ ላይ ተቀምጨ አንድ ደስ የሚል መረጃ በአረብ አሰሪዎቸ በኩል ሲነገር ሰማሁ ። ጠቅለል ሲል የሳውዲዎች መንግስት በዶር አብይ አህመድ አዲስ አስተዳደር የተሰማውን ደስታና አብሮ የመስራት ተስፋ እንዳለው ተገለጸልን። ጆሮየን ቀጥ አድርጌ መስማቱን ቀጠልኩ ። ስብሰባው እንዳለቀ አለቃየ ወደ ኢትዮጵያ አንድ በኢትዮጵያ ያሉትን ስራዎች አጥኝ ተደራጅቶ እንደሚላክ ተረዳሁ። ኩባንያቸው ኢትዮጵያን ማዕከል አድርጎ በምስራቅ አፍሪካ ስራ ለመስራት ፍላጎት አንዳለው የሰማሁ ቀን የተሰማኝን ስሜት መግለጽ አይቻለኝም ፣ ብቻ ውስጤን ደስታ ተሰማው 🙂
ብዙው ሳይቆይ “ጉዳዩን አፋጥኑት !” ይባል ገባ … አጥኝው ወደ ሀገር ለማቅናት ከገጠሙት ችግሮች አንዱን ወደ ጅዳ ቆንስል ጎራ ብለን ተረዳን ። ኢትዮጵያ ዛሬም የአለም አቀፉን የሽብርተኞች ዝርዝር ሀገራት ተከትላ የፖኪስታን ፣ የአፍጋኒስታን እና የመሳሰሉት ሀገር ዜጎች ወደ ሀገሯ ለማስገባት በሯን በደንብ እንዳልከፈተች በኢምግሬሽንና በኢኮኖሚ ክፍሉ ጎራ ብየ ተረዳሁ ። መረጃውን ለአለቆቸ አቀበልኩ ማመን አልቻሉም ። የራሳቸው ባለሙያዎች ድርቅ የመታቸው ኩባንያዎች የተጠቀሱት ሀገሮች ባለሙያዎች በጅዳም ሆነ በሪያድ ኢንባሲ ወደ ኢትዮጵያ ለመጓዝ ቪዛ ያገኙ ዘንድ ከሁለት ሳምንት በላይ መጠበቅ አለባቸው ። የሳውዲ ባለሀብቶች ወደ ኢትዮጵያ ኢንቨስት ለማድረግ ፍላጎትና የመንግስት ድጋፍ ማድረግ የመጀመሩን አበረታች ተስፋ ጠልፈን ላለመጣል እንደ ሀገር ቤቱ የተጠላለፈ የሽብር ህግ በኢምግሬሽን አካበቢ ያሉትን ይህን መሰል ጋሬጣዎችን መንግስት ሊፈታቸው ይገባል ። እንግዳ ጠርቶ በርን ጥርቅም አድርጎ ዘግቶ አይሆንምና ይታሰብበት !
አዎ ፣ አንጻንራዊው ሰላምና የሀገራቱ ትስስር ብሎም ፖለቲካው ሳውዲና የተባበሩት ኢምሬት ፊታቸውን ወደ ኢትዮጵያ አዙረዋል። ካወቅንበት መጠቀም እንችላልን ። የዛሬው የሳውዲ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጉብኝትና ሰሞነኛው የሳውዲ ባለሀብቶች ምክክር የሚያሳየው ምልክት በሀገራቱ መካከል የተጀመረውን አበረታች ግንኙነት ጅማሮ ነው ። አበረታችነቱ ለሁለቱም ወገን ጠቀሚ ነው ስል ያለ ነገር አይደለም ። ዘርዘር አድርገን እንመለስበት ዘንድ ለዛሬው በዚህ ላክትም !
******