>

ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ብጹእ አቡነ መርቆርዮስን ጎበኙ - መግለጫም ሰጡ

ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ብጹእ አቡነ መርቆርዮስን ጎበኙ – መግለጫም ሰጡ
 
«የኢትዮጵያ አንድ አካል የአንድ ዛፍ አንድ ቅጠል አይደለም። እንዲዉ ዝም ብሎ የሚረግፍ ሀገር አይደለም፣ እኛ ስለ ፈለግነዉ የምንጠብቀዉ ስላልፈለግነዉ የሚፈርስ ሀገርም አይደለም። ህዝቡ አንዱ በአንዱ ዉስጥ ያለ፣ማህበራዊ ትስስር ያለዉ ጭምር ነዉ። በዋዛ ፈዛዛ የሚበተን ሀገር አድርጎ ማሰብ ስህተት ነዉ።»
ሸገር ራድዮ
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዩስን መኖሪያ ቤታቸው ድረስ በመሄድ ጎበኙዋቸው፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉብኝታቸው ወቅት ለአቡነ መርቆርዮስ ቤታቸው በመምጣት እንደሚጠይቋቸው ከአሜሪካ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዙ ቃል በገቡላቸው መሰረት ሊጠይቋቸው እንደመጡና ከእርሳቸውም ጋር ስለ ይቅርባይነትና ስለፍቅር እንደተወያዩ ገልጸዋል፡፡
ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ጠቅላይ ሚኒስተሩ።  ብጹዕ አቡነ መርቆርዮስን መኖሪያ ቤታቸው ድረስ ተገኝተው በመጎብኘታቸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
ባለፉት 26 ዓመታት ለሁለት ተከፍለው የሀገር ቤትና የውጭ ሲኖዶስ እየተባሉ ሲጠሩ የነበሩት ሁለቱ ሲኖዶሶች ቃለ ውግዘታቸውን አንስተው ወደ ዕርቅ መምጣታቸው ይታወሳል።
ይህንንም ተከትሎ አራተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ እና ብፁአን አባቶች ከአስር ቀናት በፊት ነበር ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በመሆን አዲስ አበባ የገቡት፡፡
የአቡነ መርቆርዮስ ወደ ኢትዮጵያ መመለስን አስመልክቶ በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ደማቅ የአቀባበል ስነ ስርዓት ተከናውኗል፡፡
ኢትዮጵያ ከገቡ ከሦስት ቀናት ቆይታ በኃላም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶሶች የዕርቀ ሰላም መርሃ ግብር በሚሊኒየም አዳራሽ ማካሄዳቸው ይታወሳል፡፡
Filed in: Amharic