>

ህዝቤ ሆይ አትወናበድ! (ታዬ ደንደአ)

ህዝቤ ሆይ አትወናበድ!
ታዬ ደንደአ
ከትላንት ወድያ የኢትዮጵያ ህዝብ ተባብሮ በከፈለዉ ዋጋ አስደማሚ አብዮት ማካሄዱን እና የፀረ-ለዉጥ ቡድኑ ለዉጡን ለመቀልበስ በተለያዬ ዘዴ የህዝቡን አንድነት ለማላላት እየሰራ መሆኑን ገልጬ ነበር። ዛሬ ደግሞ  የሚከተሉትን ነጥቦች ላክል።
እዉነት ለመናገር አሁን ላይ የተደራጁ ሌቦች ተገርስሷል። ፈፅሞ የኢትዮጵያን የዴሞክረሲ ህደት የሚያሰናክሉበት አቅም የለቸዉም። ልፋታቸዉ ከንቱ ነዉ። በእርግጥ ትላንትም አቅም አልነበራቸዉም። ጉልበታቸዉ ህዝባችን ተንኮላቸዉን አለመረዳቱ ላይ ነዉ። በአንድ በኩል መተማመንን ሸርሽረዉ ጥርጣሬን አሰፉ። በሌላ በኩል ደግም ራሳቸዉን አግዝፈዉ ሳይኖሩ ተፈሩ። አሁንም ያ ተንኮል ቀጥሏል። ዘዴያቸዉን ማጋለጥ ግድ ይላል።
 
ዘዴ2 የመሪዎችን ስም ማጥፋት፦
 
የለዉጥ መሪዎች በህዝቡ ዘንድ ከፍተኛ ቅቡልነት ማግኘታቸዉ ይታወቃል። ለዉጡን ለማኮላሸት መሪዉን ከህዝብ መነጠል ወሳኝ መሆኑን የጥፋት ሀይሉ ተገንዝቧል። ስለዝህም የለዉጥ መሪዎችን ስም በሐሰት ፕሮፓጋንዳ በማጠልሸት በህዝቡ ዘንድ ክብር ለማሳጣት እቅድ እና ስትራቴጂ ነድፏል። አሁን በከፍተኛ የሀገር መሪዎች ላይ ዘመቻ ጀምሯል።
ዘዴ 3 ለዉጡን መካድ፦
 
የኢትዮጵያዉያን አብዮት ሊካዱ የማይችሉ ለዉጦችን አምጥቷል። ወሳኝ የፖለቲካ ጥያቄዎች ተመልሷል። የመጣዉ ለዉጥ ለመዘርዘር እንኳን ያደግታል።  ነገር ግን ለዘመናት የገነገነ ችግር በአንዲ ጊዜ አይፈታም። በየቦታዉ ጥቃቅን ችግሮች ይኖራሉ።
 ፀረ-ለዉጥ ሀይሉ እነዝህን ጥቃቅን ችግሮች በማጉላት ምንም ለዉጥ እንደሌሌ ለማሳመን ይፈልጋል። ለዝህ ደግሞ ህዝቡ ያገኛዉን ድሎች በመዘንጋት ባልተሟሉ ጉዳዮች ላይ ብቻ እንዲያተኩር ለማድረግ አቅዷል። ትንሽ ችግር ከተፈጠረ ነገሩን በማጋነን ሀገር በሙሉ የጠፋ ለማስመሰል ስልት ተቀይሷል።
ዘዴ 4 ህገ-መንግስትን እንደሽፋን፦
 
እዉነት ለመናገር ህገ-መንግስት በአግባቡ መከበር የጀመረዉ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ነዉ። ህገ-መንግስቱን በመጣስ በሀገርና በህዝብ ላይ ሲፈነጭ የኖረዉ ማን እንደሆነ ይታወቃል። ፀረ-ለዉጡ ግን ዛሬ የህገ-መንግስቱ ጠበቃ መሆኑን አይኑን በጨዉ ታጥቦ ይተርክልናል። ይህ “ታዳጊ” ክልሎችን ለማሳደም የተቀየሰ ስልት ነዉ። ነገር ግን እነዝህን ክልሎች በግልፅ ሞግዚት ስር አስገብቶ ነፃነታቸዉን እና ባጀታቸዉን በመዝረፍ ለ27 ዓመታት በታዳጊነት እንዲኖሩ ያደረጋቸዉ ማን እንደሆነ ግልፅ ነዉ። ይሄ ሁሉ እየታወቀ የዶር አብይ አስተዳደር “ህገ-መንግስቱን እያፈረሰ ነዉ” ተብሎ ጩሔት ተጀምሯል።
ዘዴ 5 የዉሸት ወሬ መንዛት፦
 
የፀረ-ለወጡ ቡድን ህሊዉና በዉሸት ላይ የተመሠረተ ነዉ። የተፈጠረዉ እና የኖረዉ በዉሸት ነዉ። ህዝቡ ዉሸቱን ሲያዉቅበት ታሞ ሞተ። ዛሬም በዉሸት ከመቃብሩ ሊነሳ አስቧል። ሰለዝህም  የዉሸት ወሬ መንዛት ጀምሯል። በየጊዜዉ “አገለ በዉሃ መርዝ ጠጥቶ ታሟል፣ እነእገለ ተጣልቷል፣ እዛጋ የሀይማኖት ጦርነት ተነስቷል፣ እገለ እንዲህ ብሏል፣ ጄነራል እገለ አዲስ አበባ ገብቷል” ይባላል። ተንኮላቸዉን ያልተገነዘበ ምንም ችግር ሳይኖር ይጨነቃል። በሐሰት ወሬያቸዉ ተሸብሮ ያሸብራል።
አሁን ምን ይጠበስ?
ለዉጡን ማሻገር ለኢትዮጵያ ህዝብ የህልዉና ጥያቄ ነዉ። ወደ ኀላ መንሸራተት አደገኛ ነዉ። ባርነት እና ችጋር ይበቃናል። አማራጫችን ለዉጡን ማስቀጠል ብቻ ይሆናል።  ለዝህ ደግሞ ከመቸዉም ጊዜ በላይ መንቃት እና መተባበር ግድ ይለናል። ህዝባችን መንቀት አለበት። የሴረኞችን ተንኮል ጠንቅቆ መረዳት ይጠበቅበታል። መንግስት እና ምሁራን ደግሞ መረጃን እና እዉቀትን በበቂ ሁኔታ ማሰራጨት አለባቸዉ። የአብዮቱ ዋስትና የህዝቡ ንቃት ነዉ ።ህዝቡ ከነቃ የፀረ-ለዉጡ መደበቂያ ዋሻ አይኖርም።
ዘዴ 5 ስለሞቱት እያለቀስን የአሁኑን ግፍ እንድንረሳ ማድረግ ፦ 
ከወዲያ እና ከወዲህ ተመሳሳይ ድምፅ!  ሀሳብ የሌለበት ንትርክ!  አሁን ክርክሮች ስለሀዉልቶች ሆኗል። ግማሹ የአኖሌ ሀዉልት እንዲፈርስ ይጠይቃል። ሌላዉ ደግሞ በምኒልክ ሀዉልት ላይ አተኩሯል። ይህ ጫወታ የማን እንደሆነ ይታወቃል። የእሳትና ጭድ ፖሊሲ አካል ይመስላል። ሀዉልት ሟቾችን ይመለከታል።
ጠላት ሆን ብሎ ትኩረታችንን ወደ ሟቾች ይስባል። በመሀሉ የኗሪዎች ጉዳይ ተዘንግቷል። ስለሞቱት እያለቀስን የአሁኑን እና የወደፊቱን ትዉልድ በጅምላ እንዳንገድል ያሰጋል።
 በ21ኛ ክፍለ ዘመን በዝህ ደረጃ መታለላችን ምን ይባላል? ሌላ ጋ መማሪያ የሆነ ታሪክ እኛ ጋ ለምን የግጭት መነሻ ይሆናል? ሰዉ እንዴት በገዛ እጁ በተከለዉ ሀዉልት ሰለባ ይሆናል? እዉነት እላለሁ፦ ሰዉ ከሀዉልት ይበልጣል!
ህዝቤ ሆይ፦
 
አትወናበድ! በላማህ ፅና! ጉልበትህ አንድነትህ መሆኑን እወቅ! የሴረኞችን አሉባልታ ትተህ በቆራጥነት አብዮትህን ጠብቅ!
ሠላም ዋሉ!
Filed in: Amharic