>
5:18 pm - Saturday June 15, 1985

መለስ ዜናዊ እንኳን ሞተ። ለአረመኔ ነብሰ-ገዳይ ሙት ዓመት፣ ሙሾና እንባ የለኝም። (ሃይሉ አባይ ተገኝ)

መለስ ዜናዊ እንኳን ሞተ። ለአረመኔ ነብሰገዳይ ሙት ዓመት፣ ሙሾና እንባ የለኝም።

ሃይሉ አባይ ተገኝ

‘አንተም ጨቃኝ ነበርክ
ሞትን አዘዘብህ፣
በመሠሪ ህሊናህ
ተንኮል ባረገዘው እሣት ነደድብህ።

– ህወሃት-ወያኔ የሞተችው መለስ ሲሞት ነው! ሠው ይሙት አይባልም። የመለስ ዜናዊ ሞት ግን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ትልቅ ግልግል ነው” (ግደይ ዘርዓፅዮን የህወሃት መስራችና የቀድሞ አባል)

ልክ ነው። ዓለም ሂትለርን ከአረመኔ ድርጊቱ ጋር በሞቱ እንደተሰናበተው ሁሉ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብም በፈጣሪ እርዳታ መለስ ዜናዊን ተገላገለው። አሜን!

‘የማንነት ንፅፅር ‘በናዚው አዶልፍ ሂትለርና በወያኔው መለስ ዜናዊ መካከል’!

1. ልክ የጀርመኑ ናዚ የአስተሳሰብ አቅጣጫ እምብርት በአርያን ዘር የበላይነት፣ በዘረኝነትና በፀረ-ፅዮናዊነት ላይ እንደተመሠረተው ሁሉ፤ የወያኔም አገዛዝ እሣቤ በወያኔዎች “ሐያልነት”፣ ጎሠኝነትና በፀረ-አማራነት ላይ በተነጥላ፤ በኢትዮጵያውያን ላይ በጅምላ ያነጣጠረ ነው::

2. በናዚዎች እይታ የሁሉም የበላይ፣ ንፁህና እንከን አልባው ዘር ተደርጎ የተቆጠረው የናርዶኒክ ዘር ሲሆን፤ በወያኔ ህወሃት ዓለም የአድዋ ጎሣ ከሁሉም ኢትዮጵያውያን በጠቅላላ፤ ከድፍን ትግራይ በተነጥላ ንፁህ፣ “የወርቅ ዘር” እና የበላይ ተደርጎ ይታሰባል::

3. የናዚ አባላት ለሂትለር ያላቸውን ታማኝነት በመሃላ እንዳረጋገጡት፤ የወያኔ-ህወሃት አባላትም ባጭር የተቀጨውን መለስ ዜናዊ <<ባለራዕዩ>> መሪያችን እያሉ ያመልኩትም ነበር::

4. አዶልፍ ሂትለር ጆሴፍ ጎብል በተባለ የፕሮፖጋንዳ ክፍል ሃላፊው የናዚ ተከታዮችን ድንጋዩን ውሐ ብሎ ያሳምናቸው ነበር:: መለስም የህወሃትን መንጋ ያለጥርጣሬ በሃሠት ይነዳቸው ነበር::

5. ናዚው ሂትለር ጭፍጨፋ የሚተገብርና በሚስጥር የተደራጀ ‘ገስታፖ (Gestapo)’ የተሠኘ የነብሰገዳዮች ጦር ነበረው:: መለስ- ወያኔውም ‘አግዐዚ’ የተሠኘ ተመሣሳይ ጨፍጫፊ ጦር አላቸው::

6. ሂትለርና የናዚ ፖርቲ የጀርመኖችን መላ ህይወት ይቆጣጠር እንደነበረው፤ መለስና ህወሃትም ኢትዮጵያውያንን በተመሳሳይ መልክ ጨፍልቆ ተቆጣጥሯል::

7. ሂትለር “ምንም እንኳ ውሸት ግዙፍ ነገር ቢሆንም ሠዎች እውነት አድርገው እንዲቀበሉት ተደጋግሞ መነገር ይኖርበታል” ይላል። ውሸት ልክ እንደ ሂትለር፤ የመለስና ህወሃት ልዩ መታወቂያ ብቻ ሣይሆን የማንነታቸው መለያና ባህል ነው።

8. ሂትለርና መለስ የጭካኔያቸው ምንጭ የበታችነት ስሜት የፈጠረባቸው የአይምሮ ቀውስና ሁለቱም ያረገዙት የቂምና የበቀል ፅንስ ነው።

9. ሂትለር ግድያን የተለማመደው በጀርመን ካቶሊኮች፣ የሰራተኛ ማህበር መሪዎች፣ ኮሚኒስቶችና አይሁዶች ላይ ነው። መለስም የመጀመሪያውን ጥይት የተኮሰው ኢትዮጵያውያንን በመግደል ሲለማመድ ነው።

10. መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያን አንድነትና ኢትዮጵያውያንን ልክ እንደ ባንዳ ቤተሰቦቹ የተፈታተነ የበቀል፣ የቂምና የጥላቻ መሃንዲስ ነው።

11. መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያን ሕዝብ አብሮነት በ”ጎሣ ፌደራሊዝም ወይም ዜናዊዝም” መርዝ አቀጭጮ በጎሣዎች መካከል ውጥረትና ግጭት እንዲሰፍን ያደረገ የሂትለር ፎቶ ኮፒ ነው።

12. መለስ በ”ጎሣ ፌደራሊዝም” ቫይረስ የበከላቸው የጎሣ ፓለቲከኞችን ፈጥሮ የሃገሪቱን ህልውና እንዲፈታተኑ ያስቻለ እኩይ ድውይ ነው።

13. መለስ በኢትዮጵያ ውስጥ ለተፈፀሙ የዘር ማምከን፣ ማፈናቀልና ጭፍጨፌ ጠንሳሽና ነዳፊ የሂትለር የበኩር ልጅ ነበር።

14. ደግነቱ መለስ ዜናዊ ሊበትናት ያቀደውንና ያሰባት ኢትዮጵያ ሣትፈረካከስ ክፋትንና አረመኔነትን የሚያመነጨው ጭንቅላቱ ፈንድቶ ይህችን ዓለም ተሰናበተ።

ጭፍጨፋ፣ ጭካኔ፣ ከሃዲነት፣ ውሸት፣ ማጭበርበርና ከንቱ ስሜት የሂትለርና የመለስ እንዲሁም የናዚና የህወሃት መለያ የጋራ ባህሪያቸው ነው:: ሁለቱም የእኩይ ጥላቻ ምርኮኞችና በበታችነትና ትልቅ የመምሰል ቅዠት ልክፍት የተጠናወታቸውና የራሣቸውም ሃጢያት ሠለባዎች ናቸው::

አይሁዶች፣ ጀርመኖችና በጭካኔ ምግባሩ ሠለባ የሆኑ የዓለም ሕዝብ ሂትለርን፤ ገፈት ቀማሾቹም ኢትዮጵያውያንም መለስ ዜናዊን ደግመው ደጋግመው ይሙቱ ይላሉ።

አዶልፍ ሂትለርና መለስ ዜናዊ የሚታወሱት በአረመኔነታቸው፣ በእንሠሣዊ ገቢራቸውና በገዳይነታቸው ብቻ ነው። ሁለቱም በፀረ-የሠው ዘር ምግባራቸው ነው።
ግልግል!!!!

Filed in: Amharic