>
5:13 pm - Tuesday April 18, 3290

ጦማሪዎች ለሃምሌ 7 ተቀጠሩ - ''ሃሰተኛ ቃል እንድሰጥ ማስገደድ ተደርጎብኛል''ጦማሪ በፈቃዱ ሃይሉ

Natnael Semayawi partyThe girl whp is beaten by policየዞን ዘጠኝ ጦማሪዎች ማህሌት፣ ኣቤልና በፈቃዱ በተሰጣቸው ቀጠሮ መሰረት ፍርድ ቤት የቀረቡ ቢሆንም፣ ሳይፈቱም ክስ ሳይመሰረትባቸውም ወደ ነበሩበት እስር ቤት እንዲመለሱ ተደርገዋል።። አቤል፣ ማህሌትና በፍቃዱ በፍርድ ቤቱ የተገኙት ከጠበቃቸው ኣመሃ መኮንን ጋር ነበር።

ጠበቃ አምሃ እንዳሉት ፖሊስ እንደለመደው 28 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ጠይቆ የነበረ ሲሆን፣ ዳኛዋ የጠበቆቹን አስተያየት ሳትጠይቅ 14 ቀን ጦማሪዎቹ በእስር እንዲቆዩ ፈቅዳለች።በዚህም መሰረት ቀጣዩ ቀጠሮ ለሃምሌ 7 ተብሎኣል ።በዚያች በነበረችው የ ኣስር ደቂቃ የችሎት ጊዜ ጦማሪ በፈቃዱ ዘሃይሉ ”በፖሊሶች ሃሰተኛ ቃል አንድሰጥ ማሰገደድ ተደርጎብኛል፣ ፖሊስ እኔ ያልተናገርኩት ቃል በራሱ ጽፎ አዘጋጅቶአል” ሲል  ለፍርድ ቤቱ ማስረዳቱ ተገልጾኣል።
በዛሬው ዕለት የጦማሪዎቹን የፍርድ ሁኔታ ለመከታተል ከ300 በላይ ሰዎች በስፍራው የነበሩ ቢሆንም የኣራዳን ግቢና ኣካባቢውን ለቀው እንዲሄዱ ፖሊሶች ሲያስገድዷቸው እንደነበር ለማወቅ ተችሎኣል።
ከአነዚህም መሃል፣ የሰማያዊ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊን ዮናታን ተስፋየን (ፎቶ ይመልከቱ) ”ፎቶ ስታነሳ ነበር” በማለት ወደ አስር ቤት አንደወሰዱት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።በተመሳሳይ መልኩ በስፍራው  የነበረች ኣንዲት ወጣትም (ፎቶዋን ይመልከቱ) ”ፎቶ ኣንስተሻል” በሚል በፍርድ ቤት ፊት ለፊት በፖሊሶች ተደብድባ ወደ አስር ቤት መወሰዷ ተመስክሮኣል።

Filed in: Amharic