>
5:31 pm - Wednesday January 26, 2022

በረከትና ታደሰ "እንታሰር" ሲሉ በደብዳቤ  ጠየቁ!!! (አንዱአለም ቦኪቶ ገዳ)

በረከትና ታደሰ “እንታሰር” ሲሉ በደብዳቤ  ጠየቁ!!!
አንዱአለም ቦኪቶ ገዳ
* አቶ በረከት “የዘረኝት ጥቃት ሰላባ ነኝ” ያሉት ነገር ነው፡፡ ሲጀምር አማራ ካልሆንክ በ”ብሄረ አማራ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ” የተሰኘ እና ዘርን መሰረት አድርጎ በተቋቋመ የአማራዎች ድርጅት ውስጥ ምን ትሰራለህ?!  ሲቀጥል እራስህ ኮትኩተህ እንትፍ እንትፍ  ብለህ ያሳደግከው ዘረኝነት ዛሬ ደርሶ አንተን ቢበላህ ምኑ ላይ ነው የሚገርምህ!?
              ****
ከብአዴን አባልነት “የአማራን ህዝብ ጥቅም ሊያስጠብቁ አይችሉም እና በጥረት ኮርፖሬሽን ላይ በፈጠሩት ችግር ” በሚሉ ሁለት ርእሶች ስር የታገዱት ኤርትራዊው በረከት ስምኦን እና ኢትዮጲያዊው ታደሰ ካሳ (ጥንቅሹ)(…የጠነዛ ሽማግሌ ለምን ይሆን “ጥንቅሽ” የሚባለው?!) በኢቲቪ ና መሰል ተቋማት ጢባጢቤ እንዳልተጫወቱባቸው ዛሬ ቀን ጥሏቸው የሰይፉ ፋንታሁን አይነት የዘፈን ምርጫ ፕሮግራሞች ላይ ሃሳባቸውን እየገለጹ ነው፡፡ቂቂቂቂ….አይ ጊዜ ደጉ?!
 በርግጥ አቶ በረከት እድሉ በነበራቸው ጊዜ ከድሮውንም ቢሆን አሳታፊ እንዳይሆን አድርገው ያበጁት ሁሌም ስልጣን ላይ ላለው ብቻ የሚያሽቃብጠው አዝማሪውና ሊቀመኳሱ ኢቲቪ ዛሬ ፊት ቢነሳቸው ሊገርማቸው አይገባም፡፡(ኦው ሶሪ! ኢቲቪ ለካ የእኔን ጽሁፍ ሰኞ ጠዋት አቅርቦት ነበር!…በነገራችን ላይ ከ2 እና 3 አመት በፊት ኢሳት የእኔን ጽሁፎች በተደጋጋሚ ማቅረቡን አስመልክቶ በጻፍኩት ጽሁፍ ለኢሳት ምስጋናዬን አቅርቤ ነገር ግን ተሳክቶ ማየት የምፈልገው እዚህ አገር ላይ የእኔ ጽሁፍ በኢሳት ብቻ ሳይሆን ኢቲቪም ላይ ሲቀርብ ማየት  ነው ብዬ ነበር ..ያም ነገር ሰኞ እለት እውን ሆኗል፡፡( በእርግጥ የቀረበው ጽሁፍ ይህ ነው የሚባል ነቆራ አይደለም… ኢቲቪ ገና ብዙ ቢቀረውም ጅማሮውን አድንቀናል ለማለት ያህል ነው )
ለማንኛውም እነ በረከት ዛሬ ደግሞ ለሆነ ሚዲያ በላኩት “ለብአዴን የተላከ ግልጽ ደብዳቤ” በሚል ርእስ የተጻፈ እዬዬ  ስለ ንጽህናቸው ለመዘርዘር ሞክረው ግን በዋናነት ያፈጀና ያረጀ የነባር ወያኔዎችን (አንዱን በሌላው ላይ የማነሳሳት እና ብሎም የአብዬን ወደ እምዬ የማላከክ ቱባ ባህል) ለማስኬድ ሲሞክሩ ታይቷል፡፡ከዚሁ አይነቱ መሰሪ ዝባዝንኬያቸው ምሳሌ ለመጥቀስ ያህል…” አቶ ደመቀ በብአዴን ስብሰባ ላይ “አብይ ወደ ስልጣን የመጣው እኔን ስላልደገፋችሁኝ ነው መለስም ሲሞት በሃይለማርያም ያስበለጣችሁኝ ሆነ ብላችሁ ነው” ብለውን  ነበር”  ያሏት ነገር ነች፡፡
 አቶ በረከት ምናልባት ኤርትራዊ ስለሆኑ አያውቁት ይሆናል እንጂ አማራ ሲተርት “ለማያቅሽ ታጠኝ” ይላል እኮ!….እቺን እቺን ዘዴማ ከስንት አመት ሽወዳ በኋላ ባነን መሰለኝ እሳቸውን እና መሰል ሰንኮፎችን እየመነገልን መጣል የጀመርነው!…. ሆሆሆ!…የሳቸውን ክፋት እና መሰሪነት ብሎም በኢትዮጲያውያን ላይ የሰሯቸውን ደባዎች እንዘርዝር ብንል ጊዜስ ይበቃ ይሆን ግን !?
ሁሌም ግርም የሚለኝ ለነ በረከት አይነት ደንቆሮዎች(እነሱ “ነባር ታጋዮች” እያሉ ነው እራሳቸውን የሚጠሩት)  “ሰፊው ህዝብ በሙሉ ዘገምተኛ ነው” ብሎ ማን እንደነገራቸው ነው፡፡
ሌላው ደግሞ ያሳፈረኝ አባባላቸው በተለይ አቶ በረከት “የዘረኝት ጥቃት ሰላባ ነኝ” ያሉት ነገር ነው፡፡
  …ሲጀምር አማራ ካልሆንክ በ”ብሄረ አማራ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ” የተሰኘ እና ዘርን መሰረት አድርጎ በተቋቋመ የአማራዎች ድርጅት ውስጥ ምን ትሰራለህ?!  ሲቀጥል እራስህ ኮትኩተህ እንትፍ እንትፍ  ብለህ ያሳደከው ዘረኝነት ዛሬ ደርሶ አንተን ቢበላህ ምኑ ላይ ነው የሚገርምህ!?
በርዬ (በረከት ሲቆላመጥ ነው)” ዘረኝነት ጥምብ ናት ከሷ ራቅ “ስትባል ምን ነበር መልስህ?!
የሆነ ሆኖ በዋናነት በደብዳቤያቸው የተገለጸ  እና ቸል ሊባል የማይገባው አንድ ፍሬ ጉዳይ  አለ…በሬም ሆነ ታዴ “እኛ ስርቆት የለብንም..ሰርቃችኋል ካላችሁን ያለውን ማስረጃ ይዘን በህግ ፊት ለመሟገት ዝግጁ ነን” ብለዋል፡፡
እንግዲህ ጉዳዩ ስለ ስርቆት ከሆነ መታየት ያለበት በወንጀል ህግ (በሙስና ህግ) ነው ማለት ነው፡፡በራሱ ተነሳሽነት በወንጀል  ህግ ለመዳኘት  ለሚፈልግ መጀመሪያ በህግ አካል ፊት መቅረብ ግድ የሚለው በመሆኑ አሁኑኑ በጥያቄያቸው መሰረት ያለመከሰስ መብታቸው ተነስቶ (ይህ መብት ይኑራቸው አይኑራቸው አላውቅም) በቁጥጥር ስር ውለው (ያው ቀደም ብለው ከአለቃቸው እና የእድሜ ልክ መምህሬ ከሚሉት አቶ መለስ ጋር ተማክረው ለ ስዬ አብርሃ እንዳዘጋጁት የሙስና ክስ ዋስትና ባብዛኛው ጊዜ  የማያሰጥ በመሆኑ ) በማረሚያ ቤት ሆነው የሚሉትን ማስረጃ ይዘው መሟገት ይችላሉ፡፡
ይኸው ነው!
“በሰፈሩት ቁና መሰፈር አይቀርም” ይላል የአገሬ ሰው ፡፡
አዳሜ ገና ምን አይተሽ!?
የዋሁ  የምንወድህና የምትወደን ህዝባችን ግን
ባለህበት ይመችህ
Filed in: Amharic