>

ነውር ጌጡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ!!!  (አቻምየለህ ታምሩ)

ነውር ጌጡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ!!!
 አቻምየለህ ታምሩ
ጃዋር መሃመድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞችን የነገድ ስብጥር የሚያሳይና ከኢትዮጵያ አየር መንገድ አገኘሁት ያለውን «መረጃ» ለጥፎ ነበር። አየር መንገዱ ለሐጂ የሰጠው መረጃ ብዙ የተሳከሩ ነገሮች ያሉበት በመሆኑ የመረጃውን ተዓማኒነት ለማጣራት ሞክሬ ነበር።  ምንም እንኳ እስካሁን ሙሉ መረጃውን ማጣራት ባንችልም ሐጂ ጃዋር የለጠፈውን  የአየር መንገዱን ስራ አስፈጻሚዎች መረጃ በሚመለከት ግን  ማጣራት ችለናል። ባካሄድነው  ማጣራት መሰረትም  አየር መንገዱ ለሐጂ ጃዋር የሰጠው ማስረጃ እጅግ አሳፋሪና አይን ያወጣ ነውረኛነት የተሞላበት  የቅጥፈት መረጃ ነው።
 ጃዋር በለጠፈው መረጃ መሰረት አየር መንገዱ 18 ስራ አስፈጻሚዎች እንዳሉትና ከዚህ ውስጥ 7ቱ [39%] አማሮች [ወይንም «ከአማራ ክልል»] እንደሆኑ፤ 1ዱ [6%] ኦሮሞ[«ከኦሮሞ ክልል»] እንደሆነና 5ቱ  ትግሬዎች[ከትግራይ ክልል] እንደሆኑ ያሳያል።  ከታች የታተመውን እውነተኛው ማስረጃ እንደሚያሳየው  ግን ከአየር መንገዱ ስራ አስፈጻሚዎች መካከል 8ቱ [47%] ትግሬዎች ሲሆኑ 3ቱ [17%]   አማሮች [ወይንም «ከአማራ ክልል»] እና 3ቱ [17%] ኦሮሞዎች[«ከኦሮሞ ክልል»]  ናቸው። እውነታው ይሄ ሆኖ ሳለ በአየር መንገዱ የአማራ ያልተመጣጠነ ድርሻ ያለ ለማስመሰል  በመሰሪነት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ የአማራ ነገድ ተወላጆች የስራ አስፈጻሚ ቁጥር 3 [17%]  ሆኖ ሳለ  የአማሮች [ወይንም «ከአማራ ክልል ናቸው የተባሉት»]  ድርሻ ወደ 7 [39%] ከፍ በማሳደግ በአማራ ላይ ያልተገባ ምስል እንዲፈጠር አድርገዋል። ይህ አይን ያወጣ ነውረኛነት ነው።
አየር መንገዱ የተሳሳተ መረጃ በመስጠቱ ይቅርታ ጠይቆ ስሕተቱን በአደባባይ  ማስተካከል ይኖርበታል። ለጀዋር የተሳሳተና የፈጠራ  መረጃ  የሰጠው አካልም መጠየቅ ይኖርበታል!  አየር መንገዱ  በስራ አስፈጻሚ ደረጃ ያወጣውን  የተሳሳተ የስብጥር  መረጃ  ማረም  ብቻ ሳይሆን እስከ ታች ተራ ሰራተኛ ድረስ የሰጠውን ማስረጃ ትክክለኛነት ማረጋገጥና  ሐቀኛና ተአማኒ የሆነውን  የስብጥር መረጃውን ይፋ ማድረግ አለበት!
Filed in: Amharic