>

ፍትህ ትላንት ላረዱን እና ለገደሉንም ጭምር (ሙስጠፋ ሃሰን)

ፍትህ ትላንት ላረዱን እና ለገደሉንም ጭምር

< ሙስጠፋ ሃሰን

የታዋቂው ግሪካዊ ፈላስፋ ኣርስቶትል በተከሰሰበት ወንጀል የጥፋተኝነት ውሳኔ ተሰጥቶበት በሞት እንዲቀጣ ሲወሰን የቀድሞ ተማሪዎቹና ኣድናቂዎቹ በድንገት የታሰረበትን እስር ቤት ሰብረው በመግባት ሊያስመልጡት እንደሆነ ሲነግሩት አርስቶትል ግን በጄ ሊላቸው አልፈለገም።ይልቁንም ታሪካዊ የተባለ ኣሁንም እሱ ካለፋ ሺህ ዓመታት በኋላ ብዙዎች የንግግራቸው መግቢያና መደምደሚያ የሚያደርጓትን ንግግር ነበር ያደረገው “እኔ ተወልጄ ያደግኩት በግሪክ ህግ ነው ይህ ህግ እኔን ሲያስደስተኝ የማከብረው ሲያስከፋኝ የምጥሰው ኣይደለም።እኔ ኣምልጬ ፍትህ  ከምትሞት እኔ ሞቼ ፍትህ ትኑር ነበር ያለው “

ኣርስቶትል ማምለጥ እየቻለ እድሉ እያለው ፍትህ እንዳትሞት ራሱን የሰዋው ጥፈተኝነቱን ኣምኖ ሞት ይገባኛል በሚል ሳይሆን እድሜ ልኩን ስለፍትህና ዴሞክራሲ ሲሰብክ የኖረ ሰው ፣የህግን የበላይነትና ሁሉም ከህግ በታች መሆን ኣለበት ሲል የኖረ ሰው ዛሬ በራሱ ሲደርስ ቢሸሽ ኣንድም ትውልዱ ይህንን የሱን ፈለግ ተከትሎ ስለሚፈስ ፣ኣሊያም ከዛ በኋለላ ህግ ኣክብሩ ለህግ ታዘዙ ብሎ ለማስተማር የሞራል ልእልናው ይኖረዋል ወይ ነው ??ጥያቄው አርስቶትል  የህግን እና ስርኣትን አስፈላጊነት ፣የፍትህን ትርጉም ኣስቀድሞ የተረዳ ከዘመኑ የቀደመ ባለ ምጡቅ ኣእምሮ በመሆኑ እሱ ኖሮ ፍትህ ከምትሞት እሱ ሞቶ ፍትህ እንድትኖር ህይወትን ያህል ከባድ ዋጋ ከፈለ ።

  • ወዳ ሃገራችን ወቅታዊ ሁኔታ ስንመለስ ፣ነፃነትን የማየውቁ ነፃ ኣውጪዎች ፣ስለ ፍትህ የማያውቁ የፍትህ እና ሰብኣዊ መብት ተሟጓቾች እንዲ የበዙበት ዘመን ኣለ ለማለት እቸገራለሁ።እርግጥ ነው በርካታ እጅግ ኣስከፊ ነገሮች ተከስተዋል፤ብዙ፡እጅግ ብዙ ነፍሶች ፡በግፍ ጠፍትዋል፣የበርካቶች ኣካል እንደ ከብት ስጋ ተመትሯል ፣ኣያሌ ዎንዶች ዘር ኣልባ ሆነዋል፣በርካታ ሴቶች ጡታቸው ተቆርጧል፣በርካቶች ያቻሉት እና እድል የቀናቸው በኣየር ፣ያልቻሉት በየብስና በባህር  ሲሸሹ የበራሃና የባህር ሲሳይ ሆነዋል፡፡እድል የቀናቸው ከሞት የተረፋች ነብሳቸውን ይዘው በሰው ሃገር በባርነት የተሻለ ቀን እስኪመጣ ኑሮኣቸውን ይገፋሉ። ይህቺ ኢትዮጽያ ሃገራችን በፍትህ እጦት ሳቢያ የጠፋው የሰው ነብስ፣የጎደላ ኣካል፣የፈረሰ ቤተሰብ፣የደረሱበት የጠፉ ዜጎች፣መኖራቸውን ህዝብ በይፋ በሚያውቃቸው እስር ቤቶች፣ፖሊስ ጣቢያዎችና ማጎሪያ ካምፕ፣መኖራቸውን ህዝብ በማያውቃቸው የሚስጥር እስርቤቶችና ካምፖች ታጉረው ሚሰቃዩትን እና የተሰቃዩትን ቤታቸው ይቁጠራቸው።በየ እስር ቤቱና ማጎሪያው የሚፈፀመውን የሰብኣዊ መብት ጥሰትና ኣካላዊም ሆነ ስነልቦናዊ ሰቃይ ቦታው ላይ ሆኖ የሚደረገውንና የተደረገውን ላላየ ለማስረዳት ሚሞክር ሁሉ የሚገጥመው ችግር ያንን ኣይነት ትራጄዲ ለመግለፅ ኣቅም ያለው ቋንቋ እንደሌለን እና ተግባሩ ቋንቋውን ቀድሞ እንደተፋጠረ ይገባዋል። ከሁሉም ሚገርመኝና ሚደንቀኝ ግን እንዴት ኣንድ በኢትዮጵያ ባህልና ስነምግባር፣የሃይማኖት ኣስተምህሮት ያደገ ሰው፣እንዲ ኣይነት በሰው ልጅ መግባቢያ በሆነው ቋንቋ ሊገለፅ የማይችል ገፍ ይፋፅማል?? ፣እንዴትስ ከሞራል የወረደ ፣የስነምግባር የጎደለው ኣስነዋሪ እንኳንስ ሊተገብሩት ሊያስቡት የሚያፀይፍ ሰራ  ይስራል።እኔ የዚህ ፅሁፍ ፃሃፊ መዓከላዊ። በሚባለው ዝነኛ እስር ቤት በነበርኩበት ግዜ በሰዎች ላይ ሲፈፀም ያዬሁት ግፍ እና በደል ምንስ ቋንቋ ይገልፀዋልና ለማስረዳት ልሞክር ብቻ ኣንዱ ተገልብጦ ወፌ ላላ በወፍራም የኮምፕዩተር ገመድ ውስጥ እግሩ ይገረፋል፣ኣንዱ ጥፍሩ በፒንሳ ተነቅሎ ፣ብልቱ ተቀጥቅጦ ደም ይሸናል ፣ሌላኛው ከድብደባው ብዛት በሽንትና ሰገራውን መቆጣጠር ኣቅቶት እላይ ላዪ ይፀዳዳል ስንቱ ተቆጥሮ ይዘለቃል።ከሁሉም ገርም ሚለኝ ግን ማናችንም በስም የማናውቃት ኣንዲት መርማሪ ሴት ምርመራ ክፍል ውስጥ ወንዶቹ ላይ ምርመራ በሚድረግበት ግዜ ምርመራው ሚካሄድበትን ግለሰብ በጀርባው ኣስተኝተው ረግጠው ሲይዙላት እሷ ፈፅሞ ኢትዮጵያዊ ባልሆነ ገጠ ወጥ ስነምግባር ልብሷን ገልባ ፊቱ ላይ ትሸናለች ኣንድ እንዶቹን ሽንቷን እንዲጠጡ ታስገድዳቸው ነበር ።ኣሁን ስማቸውን ለግዜው ዘነጋሁት በእድሜ ጠና ያሉ ኣባት ሸንታባቸው ሰውዬው ከእስር በዋስ እስኪፈቱ ድረስ ኣብደው እንደነበር መቼም ኣልዘነጋውም።በየቦታው እንዲህ ኣይነት ልብ፡ የሚሰብሩ እጅግ ኣሳዛኝ ታሪኮች በየ ጓዳችን ኣሉ።በየ ቦታው ህይወታቸው ያለፋ፣ኣካላቸው የጎደላ፣ቤተሰባቸው የተበተነ፣ኑሮኣቸው የተመሰቃቀለ በርካታ ዜጎች ያሉበት ሃገር ነው።ይሄን ሁሉ ዘመን የፍትህ ያለህ  ስንል ኖረናል እየኖርንም ነው።በተፋጥሮ የተሰጠንን መብት ተነፍገን ለኣመታት እየጮህን የሰሚ ያለህ ስንል ኖረናል እየኖርንም ነው።ይሁንና ትላንት ፍትህ ኣጥተን ስንሰቃይ በየ ወህኒ ቤቱ ስንንከራተት የነበርን ሁሉ፣ኡኡታችን ሰሚ ኣጥቶ የተቸገርን ሁሉ ዛሬ በዛች የፍትህ ወንበር ስንቀመጥ፣እኛ ዳኛ ስንሆን የፍትህ እጦት የሚያስከትለውን የስነ ልቦና። ቀውስ እና ጉዳት ከማንም በላይ የምንረዳው እኛ ሆነን ሳለ እንደምን ኣስችሎን ይግባኝ የሌለበት፣ ራስህን ተከላከል የማይባልበትን የትላንት ኣራጆቻችን እንኳን ያልፈፀሙትን ግፍ እንኳንስ በዚህ ዘመን ጥንት ጋርዮሽ ስርዓተ መህበር ለይ እንኳን ያልተፈፀመን ለዚያውም ምንም ራሱን እንኳን መከላከል በማይችል በመሰሉ ሚስኪን ደካማ ላይ በደቦ እንደታቦት ኣጅበን፡ልንፈፅመው ቻልን??ይሄ ሁሉ ትግል ፣ ይሄ ሁሉ መስዋእትነት በእውነት ምስኪኖችንና ኣቅመ ዳካሞችን ያለምንም ምህረት ገልብጠን ለመስቀል ነበር??ተረኛ ጨቋኝ ለመሆን?ተረኛ ጨካኝ ኣውሬ ለመሆን??ትላንት እነ በረከት፣አባይ ፀሃዬ፣ስበሃት ነጋ ታደሰ ካሳ ፣ሃይለ ማርያም ደሳለኝ ደመቀ መኮንን ፣ገዱ ኣንድምርጋቸው ፣ኣባዱላ ገመዳ ፣ኣብዲ ኢሊ፡በድንፋታ ዘመናቸው የነፈጉንን ዴሞክራሲና ፍትህ ፡የድንፋታ ዘመናቸውን ማክተም ፡የጡንቻቸውን መዛል የጅንበራቸውን ማዘቅዘቅ ኣይትን ፣ዛሬ የኛ ጀንበር ፈክታ ስትዎጣ ኣለም ኣይቶት የማየውቀውን መርገምትና ሰቆቃ ልናሸክማቸው ከተነሳን እውነት እውነት እላችኋ ትግላችን ከሽፏል።ኣትጠራጠሩ ኣብዮታችን  ተቀልብሷል።ይህንን ስርእዓት ለመቀየር መራር ትግል እያደረጉ የተሰውትም ደማቸው በከንቱ ነውና የፈሰሰው ደመ ከልብ ሆነዋል።ምክንያቱም ትግሉ ዘላቂ ሰላምና ዴሞክራሲ ማምጣት እንጂ ተራ እየተጠባበቅን በለበቅ ለመገራረፍ ኣልነበረምና።በኔ እምነት መጪው ግዜ የተሻለ እንዲሆን ይህ መጥፎ የታሪካችን ኣካልና የኣሁኑ ተግባራችን ኣንድ ቦታ ማቆሚያ ሊኖረው የገባል።ፍትህና ዴሞክራሲን የህንን ያህል ኣጥብቀን የፈለግነውና የታገልንለት ብሎም ብዙ መስዋእትነት የተከፈለበት ለኛ ትርጉሙ ና ዋጋው ብዙ የሆነን ነገር እጃችን ሲገባና ኣዛብተን የምንጠቀመው ከሆነ ዞሮዞሮ እዛው ይሆናል! !መጪው ግዜ የተሻለ እንዲሆን የሚመኝ ማንኛውም ዜጋ ፍትህን ገሎ ፍትህ ላማግኘት ሚሞክር ከሆነ የፍትህ ትርጉሙ ኣልገባውም ማለት ነው።ግለሰብም ሆነ ቡድን ኣሊያም ድርጅት ላጠፉት ጥፋት መጠየቅ ያለባቸው ህጉና የህጉን መሰረት ኣድርጎ መሆን ይኖርባታል።በረከትም ሆነ ኣብዲ ኢሌ፣ኣባይ ፃሃዬም ከሆነ ስበሃት ነጋ፣የጌታቸው ኣሰፋም ከሆነ ኣባዱላ ገመዳ መጠየቅ ያለባቸው ህጉንና ህጉን መሰረት አድርጎ መሆን ኣለበት።ከዚህ የፖለቲካ ትርፍ ላማግኘት የሚሮጥ ግለሰብም ከሆነ በድርጅት ይህንን ብርሃን ለኛ ለማሳየት በትግል ላይ ሳሉ በተሰውት ነብሰ ፣በተጎዱ፣በቆሰሉት፣በታሰሩት እና በተሰቃዩት ሰቃይ ላይ ቁማር የሚቆመሩ ቁማርተኞች እንጂ ፈፅሞ ኢትዮጵያዊ ስነምግባርም ሆነ ጨዋነት እያነሳቸው ብቻ ሳይሆንየሌላቸውም ናቸውና ኣምረን ልንዋጋቸው የገባል።

ምሳሌ፡

ኣቶ በረከትም ሆነ ታደሰ ካሳ ብዓዴን ከመኣከላዊ ኮሚቴ ኣባልነት ኣግዷል።ምክኒያት  ተብሎ በሚዲያ የተነገረው በጥረት ኮርፖሬሽን በፈጠሩት ችግር እንደሆነ ነው።እንደ እኔ  እምነት እነ በረከት ችግር ፈጣሪ ብቻ ሳይሆኑ ራሳቸውም ችግሮች ናቸውና ክስራቸው ተነቅለው ቢዎገዱ ደስታዬ ነው ።ይሁንና እኔን ደስ እንዲለኝ ህግ መጣስ ደንብም መፍረስ ዬለበትም። ስለሆነም ህግ ሲጣስ ደንብ ሲፈርስ ዝም ብሎ ማየት ኣግባብ ኣይደለም ህግ ና ስርኣት ይከበር ብዬ ኣሁንም ኡ እላለሁ። ለበረከትም ቢሆን !! ትግሉና ነፃ ማውጣቱ እኮ እነሱንም ያካትታል።እገዳው ለይ ተቃውሞ ዬለኝም ።እንደውም ዘገየ ባይ ነኝ።የታገዱበት መንገድ ግን ኣንድም ለፖለቲካ ቁማርና ትርፍ ፣ኣሊያም ግልፅ በቃል ነው።የሁለት ዝሆኖች ፀብ።ይሀውም

፩ኛ-ኣንድ ሰው ጥፋት ኣጥፍተሃል ተብሎ ውሳኔ ከማስተላለፉ በፊት

ሀ-ጉዳዩ በደንብ በገለልተኛ ወገን ተጣርቶ ሁለቱም ወገን ሲተማመኑ ወይም ተከሳሽ ማስተባበል ሳይችል ሲቀር ኣሁን ባለው ህግና ኣሰራር ደግሞ ይህንን ሚያጣራውና በኣዋጅ ስልጣን ፖሊስ ነው የሆኖ ሳለ እነሱ ከሳሽ እነሱ ፈራጅ ሆነው ነው ይህንን ውሳኔ ያሳለፉት

ለ-ካሳሽ በቂ መረጃና ማስረጃ ካለው ተከሳሽን መጀመሪያ በቃል ቀጥሎ በፅሁፍ ማብራሪያ ጠይቆ ሲያጣ ጉዳዩን ዎደ ህግ ተከሳሹ ባለበት ያቀርባል ተከሳሽም የፍርድ ቤት ቀርቦ መከላከል ሳይችል ሲቀር የጥፋተኝነት ብይን ይሰጣል ይህም ኣልሆነም

ሐ-ውሳኔው የተላለፈው እንደው በድርጅቱ ውስጠ ደንብ እንኳን ቢባል ተከሳሹ ራሱ በሌለበትና ራሱን መከላከል በማይቻልበት ሁኔት የተላለፈ ውሳኔ በመሆኑ ኣግባብ ኣይደለም

መ-ስብሰባውም ላይ ተገኝተው ራሳቸውን መከላከል እንዳይችሉ ደባ ተፈፅሞባቸዋል።ይሀውም ኣስቀድሞ በተከፈተባቸው የማሃበራዊ ሚዲያ ጦርነት ግለሰቦቹ ስነልቦና ላይ ከባድ ቀውስ እንደሚፈጠሩና ግልፅ ነው በዛ ለይ በረከት ደብረ ማርቆስ ታየ ተብሎ የተፈጠረውን የቅርብ ግዜ ትዝታችን በመሆኑ አይዘነጋም።ህዝቡ ምንም የማያውቁ ንፁሃንን ሳይቀር ገልብጦ በሚሰቅልበት፣በቁሙ በሚያቃጥልበት፣ዘግናኝ የመንጋ ፍትህ በተበራከተበት በዚህ ወቅት ባህር ዳር ላይ ብንገኝ ለህይዎታችን ያሰጋናል እና የጥበቃ ዋስትና ስጡን ሲሉ መነፈግ ኣልነበረባቸውም ።እንኳንስ ለነ በረከት ለ53 የኣፍሪካ ሃገር መሪዎች ዋስትና ሰጥታ ምታስተናግድ ሃገር ከባራክ ኦባማ እስካ ኢምሬትሱ ንጉስ ዋስትና ምትሠጥ ሃገር እንደው ለበረከት የሚሆን የጥበቃ ኣቅም ዬላትም??ሶማሊያን ደቡብ ሱዳንእና ኮንጎ ድረስ ሄዶ ሚጠብቅ ወታደር ኣንድ ዜጋውን መጠበቅ ኣቃተው??ይሄ መጅመሪያውንም እንዲገኝና ራሱን እንዲከላከል ኣልትፈለገም።

፪ኛ እሺ ይሁን ውሳኔውም ይተላለፍ ነገር ግን እኛ ጥፋተኛ ኣይደለንም ጉዳያችን ይጣራልን ብለው ሲጮሁና ኡ ሲሉ ሰሚ አጥተው የፍትህ ያለህ እያሉ ነው።ኣድማ በሚመስል ብቻ ሳይሆ የደቦ ፍርድ መሆኑ በግልፅ በሚታይ መልኩ የግል ስልክ እንኳን ኣይነሳላቸውም ለምን??በጣም የሚገርመው ሚዲያው ኣሁንም ድምፅ ለሌላቸው ደካሞች ድምፅ በመሆን ፋንታ ኣሰላለፉን ኣሳምሮ የጉልበተኞችና የሃይለኞች ጅራፍ እንደሆነ ነው ያለው ።በረከት ባሁን ሰኣት ደካማ ነው እንደኛ ሰሚ ያጣ ደካማ።ሀሳቡን ለማስረዳት እና ራሱን ለመከላከል ዎደ ሚዲያዎች ሲኳትን ለወትሮው በረከት ምን ኣለ እያሉ ያለለውን ኣሳምረውና ኣሽሞንምነው እ ያቀርቡ ያሰለቹን የነበሩ ሚዲያዎች ሁሉም በራቸውን ጥርቅም ኣድርገው ደጅ ሲያስጠኑት ነበር።ለምን ከተባለ በኣዲሱ ባለ ግዜ በፍቅር እብድ ክንፍ ብለው ኣዲሱን ባለ ግዜ ለማስደሰት ብቻ። በታደሰ ካሳም ሆነ በበረከት ላይ የተላለፈው ውሳኔ በኣንድ በኩል ነባር ቂም መወጫ በሌላ በኩል ደግሞ በመሃበራዊ ሚድያ በገፍ እየተበተነ ያለውን ብኣዴንን የማጥላላት ዘመቻ ለማርገብ የታለመ እንጂ በረከት ኣጥፍቷል ይቀጣና ይታረም ሚል ኣይደለም።ይሄ ሁሉ ወጣት ያለቀው ፣በየእስር ቤቱና ማጎሪያው የኣውሬ እራት የሆነው፣ኣገር ጥሎ የተሰደደው ለዚህ ኣልነበረም።ለእዉነተኛ ፍትህ ለሃቀኛ ዴሞክራሲ እንጂ።ማንም የቀድሞ በደዮችና ግፋኞችም ጭምር በሃቅ የሚዳኙበትን ስርዓት ለማምጣት ነበር ትግሉ።ትናንት እነ በረከትም ሆነ ህዋሀት በድንፈታ ዘመናቸው የነፈጉንን ፍትህ ዛሬ እኛ ተረኛ ስንሆን ከነፈግናቸው እኛ ከነሱ በምን ተሻለን?እንደው እኛስ ስለ ፍትህ ለማወራት እንዴት የሞራል ልእልና ይኖራናል??የተነጠቅነውን በጉልቱት ኣስመልሰን ይሆናል፣የተነፈግነውን በሃይል ኣስከብረን ይሆናል ነገር ግን ትላንት ላሰቃዩን ለበደሉን፣ላሰሩኑና ፤ለገረፉን ጭምር ሳንሸራርፍ እና ካልሰጠን እና ካላዳረስነው ፤ዛሬ ግዜና ኣጋጣሚው በእጃችን እያለ ካላስተካከልነው፣ኣስተማማኝ መሰረት ላይ ከላቆምነው እመኑኝ የዛሬው የኛ ጅንበር የጠለቀች ቀን ይሄንኑኑ ፍትህ ከሌሎች በለተራዎች እንለምናለን!!

ቸር እንሰብት

ሐሰን ሙስትጠፋ

Filed in: Amharic