>
5:14 pm - Thursday April 20, 6519

በሀሰት የተገነባው የበረከት ባቢሎን (ቾምቢ ተሾመ)

በሀሰት የተገነባው የበረከት ባቢሎን

ቾምቢ ተሾመ

ሟቹ መለስና በረከት ከሚያስገርም ተፈጥሮቸው አንዱ ህዝብ ፊት ቆመው ሲዋሹ ለቅጽበት ያህል እንኳን ሀፍረት  አምሯቸውን ኮርኩሮት በፊታቸው ላይ ሲያልፍ የማይታይባችው ፍጡር መሆናቸው ነው፤ ሲዋሹ ወኔ በተላበሰ ድፍረት ቅንድባቸው ሳይታጠፍ ነው የሚዋሹት ፡፡

ገድለው ሟቹ እራሱ  ለሞቱ ምክንያቱ  ነው  ብለው አይናቸው አፍጥጠው መኮነን የሚችሉ ሰዎች ናቸው፤  2005 ምርጫ የህዝብ ድምጽ በቀን ዘርፈው ህዝቡ ሲቃወም ፤ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ወንጀለኞች ለማድረግ ትራንስፖርቴሽን ውስጥ ቦምብ ጠምደው የንጽሃንን ህዝብ ደም ያፈሰሱ እኩዮች ናቸው፡፡ ይህንን ድርጊታቸውን
የአሜሪካን ኢንባሲ፤ ወደ ስቴት ዲፓርትመንት ሲያስተላልፍ ዊኪሊክ ጠልፎ ያወጣው ሀቅ ነው፡ነገር  ግን መለሰ አውሮፓ ሄዶ ሰላማዊ ሰልፈኞችን ለምን  ትገድላላህ ተብሎ ሲጠየቅ ፈንጂ የሚወረውር ሰላማዊ ተቃዎሚ አላውቅም ብሎ ነው የተመጻደቀው፤ መለስና በረከት ውሽታም፤ ደም አፍሳሾች ብቻ ሳይሆኑ ውሽታቸውን በጠመንጃ እውነት ነው በሉ ብለው ህዝብ ላይ ሰቆቃን ሲነዙ የቆዩ መናጢዎች ናቸው፤ ነገር  ግን ውሸት ያለጠመንጃ ምን ያህል የጭድ ክምር እንደሆነ ግልጽ የሚያደርገው በቅርቡ እርቃኑን እየሮጠ ልብሴ አያምርም ወይ እያለ ለቃለ ምልልስ  ከሚዲያ ወደ ሚዲያ ሲሯሯጥ የከረመውን በረከትን በመስማት ነው፡፡

ስለማይረዱ ማንነታቸውን፤….  ከስራቸው ይልቅ ያምናሉ አፋቸውን  አይደል ጥላሁን  ያለን ??  ውሸታሙ በረከት ስይፉ ጋር ለቃለ ምልልስ የሄደበት ምክንያት ከበድ ያለ ጥናትና ማስረጃ  የሰበሰበ ጥያቄ እንደማይገጥመው ስለተማመነና እግረመንገዱንም የውሸት ፕሮፓጋንዳውን ለመንዛት ነበር፤ እንደ ጠበቀውም  ስይፉ ስለ አንተ እና ስለእርሶ ብዬ ልጥራህ ወይ የመሳሰሉ ቀላል ቅልልቦሽ ነበረ ለበረከት የሰጠው፤ ይሄም ሆኖ ግን ሊቀ ውሸት በረከት የራሱን ውሸት  አስተካከሎ እንኳን መዋሸት አልቻለም፡፡

እኩዩ በረከት  በአማራ ልጆች ህይወት ላይ ስቆቃ ነዝቶ እንዳልኖረ፤ ስንቱን ኢትዮጵያዊ በየእስር ቤቱ እንዳላጎረ፤ ስንቱን ኢትዮጵያዊ ከሀገር እንዳላስደደ አሁን የሰራው ወንጅል ቋት ሞልቶ ለህዝብ መጋለጥ  ሲጀምር እኔ ቤተሰቦቼ ከኤርትራ ስለመጡ ነው ብሎ እራሱን  እንደተጠቂ አድርጎ ያቀርባል፤ ቀጥሎም በዚያ ምክንያት ነው ከብዓዴን ከድርጅቱ የተባረርኩ ብሎ ያላዝናል፤ ይህንን ውሸቱን  ቋጣጥሮ ሳይጨርስ፤  እየተገፋ ያለበት ምክንያት ደግሞ “ኤርትራዊው” በረከት እንዲባረር ቀጭን ትእዛዝ ከኤርትራዊዉ ኢሳያስ አፈውርቂ ሰለተሰጠ ነው ይላል (ምንም እንኳን ከሁሉም በፊት በኤርትራ ተቃዎሚ ሬዲዮ ቀርቦ ባደም የኤርትራ ናት ብሎ ሲለፍልፍ የነበር ሰው ቢሆንም) ውሸቱን ሲያጣፍጥ ደግሞ እራሱ ሲያሽከረክረው የነበረው ድርጅት ዛሬ የኢሳያስ ተላላኪ ሆኖ ከድርጅቱ አባረረኝ ብሎ ይኮንናል፡፡

ይህ በረከት ብቻ መፍጠር የሚችለው የበሬ ወለደ  ውሸት ነው፤ ሁለተኛው ውሸት ደግሞ ደመቀን ጠቅላይ ሚኒስተርነት ስላልደገፍኩት ነው ድርጅቱ የጠመደኝ ብሎ በአንድ ድንጋይ ሁለት እኩይ የሆነ ነገር ለመስራት የሞክራል ፤ አንደኛው ይህንን ወሬ ነዝቶ በአማራውና በኦሮሞ ድርጅት መሃከል ክፍፍል ለመፍጠር፤ ሁለተኛ ደግሞ እነ አብይ ጎያ ገብቶ የሴራ ፋብሪካዉን ለመክፈት ነው፡፡ የዚህ ውሸት ችግር ግን ደመቀ ከውድድሩ እራሱን  ካገለለ የበረከት ድጋፍ ለምን እንደሚሻ ነው ፤ በረከት ካልሰማ ዶ/ር አብይ በአሜሪካው ጉብኝቱ የለማ ቲም ደመቀን ገዱንም ይጨምራል ብሎ ተናግሯል፤ ሁለተኛ የበረከት እኩይነት ለአብይ ሚስጥር አይደለም፤ ሀገርን አንድ ለማድረግ ሚስማርና መዶሻ እንጂ መጋዝ እንደማያስፈልግ ጠንቅቆ ያውቃል፡፡

በረከት በሰጠው ቃለምልልስ ግልጽ የሆነ ነገር ቢኖር በውሽትና በቅጥፈት የገነባው የባቢሎን ግንብ የእውነትን ጠጠር ሲነካው መቆም እንደማይችልና እንደሚፈረካከስ ነው፤  ሌላው የበረከት ባዶነት ደግሞ ልክ በግሪክ
አፈታሪክ  መልኩን በኩሬ ውሀ ነጽብራቅ እራሱን እያየ ከራሱ ጋር ፍቅር እንደወደቀው ናርሳሱስ ለውጡን በተመለከት በዚህ ግዜ፤ በዚህ ግዜ፤ በዚህ ግዜ ይህንን ጽፌ አቅርቤ አልተቀበሉኝም  እያለ እራሱን ኢትዮጵያ ውስጥ ብቸኛ ጭንቅላት እኔ ነኝ  ብሎ ሲመጻደቅ ማየት ነው፤ የበረከት ለውጥ የሚለው ሸረኝነት ግድያ እስራት እንዴት መካሄድ እንደሚቻል እንጂ ሌላ ነገር ሊሆን አይችልም ፡፡

40 ሺህ ወጣቶችን በየበረሃው ለወባ በሽታ እየዳረገ፤ በአንድ ምላጭ ቁጥሩ የበዛ እስረኞችን እያስላጨ፤ የአሽዋው ላይ ሴቶች ልጆቾችንና አዛውንትን በእምብርክክ እያስኬደ ሲያሰቃይ ፤ በየመንገዱ ስንት ላቅመ አዳም ያልደረሱ ልጆችን እያስገደለ ፤በኢትዮጵያ ውስጥ የፖለቲካ እስረኛ የለም እያለ ጥሩምባውን ሲነፋ የነበረ መሰሪ
ምንግዜም ቢሆን የለውጥ ጠበቃ ሊሆን አይችልም ፡፡ በረከት ሳያፍር ወጥቶ የለውጥ መሪ ነኝ ማለቱ ፍርድ አቅርቦ እስር ቤት የሚወረውረው ስላጣ ብቻ ነው፤ እንደሚሉትም የፍትህ መዝውር ይዘገያል እንጂ በረከት ላይ ደርሶ ፍትሃዊ እርምጃ እንደሚወሰድበት ምንም መጠርጠር አያስፈለግም ፡፡

  ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር

Filed in: Amharic