ሃሰን ሙስጠፋ
ጥቁር ነኝ ነጭ ነኝ፣ አረብ ነኝ፣ፈረንጅ ነኝ፣ኣበሻ ነኝ፣ኬንያዊ ነኝ ሱዳናዊ ነኝ፣ስልጤ ነኝ፣ አማራ ነኝ ፣ ኦሮሞ፣ትግሬነኝ ፣ጋምቤላ ነኝ፣ መዠንግር ነኝ ፣ ሶማሌ ነኝ ፣ጉራጌ ነኝ፣ሀረሪ ነኝ፣አፋር ነኝ፣ወላይታ ነኝ ፣ ወዘተ ዘርህን ቆጥረህ ብሔርህን ጠርተህ “ነኝ” ማለት ዘረኝነት ቢሆንም ሰውም ነህና ዞረህ ዞረህ በሰውነትህ እንድ ትሆናለህ! ! እኔ የኤከሌ ዘር ማለት ሰው ከመሆን የተለየ የሚሰጥህ ኣንዳችም ነገር ዬለም። ብሄሩን ጠርተህ ዘሩን ቆጥረህ የሰደብከው ያንጓጠጥከው ካለ ዞሮ ዞሮ ሰው ነውና በሰውነት ማእቀፍ ውስጥ ስትገባ ስድቡ ኣንተንም ይጨምራል።
የኣንድ ቡድን ወይም መንጋ ኣባልነት ህይወት ላለው ነገር ሁሉ በወል የተሰጠ መለያ ነው።ኣንበሳ ከነ ዝርያው ፣ነብር ከነ ዝርያው ፣ሚዳቆ እና ሌሎችም እንዲሁ ዘርና ሃረግ ኣመጣጥም ኣለቸው።ኣንተም ሰው ነህና ዘርና ሃረግህ ከሰው ስለሚመዘዝ እንኳን ደስ ኣለህ ።ስለሆነም ዘር ኣለህ ፣ሃረግ ኣለህ ።ሌላውም እንዲሁ የራሱ ዘርና ሃረግ ኣመጣጥ ታሪክ ኣለው። የየትኛውም ብሔር ተወላጅ ብትሆን፣የየትኛውም ሀይማኖት ተከታይ ብትሆን “ሰው ነህ!!”። ይህ የማይለወጥ የተፈጥሮ ሃቅ ነው!!ማንም ዘርና ብሄሩን መርጦ የተወለደ እንደሌለ ማወቁም ጠቃሚ ነውና እወቀው ።
ይሁንና በብሔር በዘር በኋይማኖት የተለያየህ ብትሆንም በሰውነት ትገናኛለህ። ስትፈጠር ሰው ሆነህ ተፈጥረሃልና ስታልፍም ሰው ሆነህ ነው ምታልፋው።ሰው ስትሆን ሳለህ ታሪክ ትሰራለህ ስታልፍ መሰሎችህ ያንተን ታሪክ ልምድ እና ክህሎት ባኣንድ ወይም በሌላ መልኩ መማሪያ ያደርጉታል።ሁሉም የሰው ልጅ በዚህ ኡደት ውስጥ ማለፉ ኣንድ ያደርገዋል።የየትኛውም የፖለቲካ ፖርቲ ደጋፊ ሁን ሰውነት አንድ ያደርግሐል። ቋንቋ ለሰው ልጆች ሁሉ እንደ መግባቢያ የተሰጠ ስጦታ ነው !!ዬትኛውም ቋንቋ ከየትኛውም ኣይበልጥም ።ምክንቱተም ቋንቋ ከመግባቢያነት የዘለለ ምንም ጥቅም ዬለውም !!
የተለያየ ቋንቋ ስለተናገረ ከሰውነት ኣውርዶ እንሰሰ ከፍ ኣድርጎ ልእለሰብ የሆነ በኣለም ላይ ዬለም ።ቋንቋው ተናጋሪ ኣጥቶ ቢጠፋ እንኳን ሰው እስካለ ድረስ በኣንድ ወይም በሌላ መልኩ የመነገር እድል ይኖረዋል ።ሰው ከጠፋ ግን የቋንቋ ህልውና ያከትማል!!ስለሆነም ቋንቋህ የተለያየ ቢሆንም ሰውነት ያግባባሐል። ምክንያቱም ዘርህና ብሔርህ ዞሮ ዞሮ “ሰው ነው !!” ብታምንም ባታምንም የሰው ዘር ነው። ማሰብ ለሰው ዘር በሙሉ በወል የተሰጠ ችሎታ ነው!! ስለዘህ እንደሰው የምታስብበት አእምሮ ተሰጥቶሀል!!ፈለግክም ኣልፈለግክ ሀሳባዊ ሆነህ ተፈጥረሀል።ስለሆነም ኣንት ጋር ሰው እና ኣሳቢ(ሃሳባዊ)ሆነህ በመፈጠርህ ምክንያት ምክንያትና ውጤት የተሳሰሩ መሆናቻውን ትረዳለህ።በጭራሽ የማይለያዩ ኣንዱ የለ ሌላኛው መኖር ህልውና እንደሌላቸው ይገበሃል።
ሰለዚህ ምክንያታዊም ነህ ማለት ነው ።ስው ስትሆን ምክምያታዊ ትሆናለህ ።ምክንያታዊ ሰትሆን የምትደግፈውም የምትነቅፈውም ሀሳብን ነው።ፀብህም ግጭትህም ከሰው ከሀሳብ ጋር እንጂ ከሰው ጋር ኣይሆንም። ቋንቋ መግባቢያ እንጂ ብሔር የለውምና እኔ የምናገረውን ቋንቋ መናገር አይችልም ብለህ አንድ ሰው ላይ ጉዳት ስታደርስ ዞሮ ዞሮ የጎዳኸው ያንተን ዘር ነው!!እንዴት ብሎ ኣልከኝ?? ምክንያቱም የሰው ዘር ነሴ ምክንያቱም ሰው ነሃ! ! ቋንቋ ለሰው ተፈጠረ እንጂ ሰው ለቋንቋ አልተፈጠረምና ለውጤቱ ብለህ ምክንያቱን ኣታጥፋ።ቋንቋ ውጤት ነው ሰው ምክንያት ነው ።ሰውን መግደል በየትኛውም ሃይማኖትም ሆነ የሰው ልጅ ኣስተምህሮ ወንጀል ነው ።በምድርም ያስጠይቃል በሰማይም ያስኮንናል ።ቋንቋ ግን እንደሱ ኣይደለም ። የየትኛውም ባንዲራ ቀለም የሚወክለው የሆነን መሃበረሰብ ወይም ቡድን ነው ይሁንና ይህ ቡድንም ሆነ መሃበረሰብ ግን በውስጡ ሰው ኣለ ሰለዚህ ውክልናው ሰው ነው።ሰውን አክብር። ፋኖም ሁን ሁን ዘርማም ሁን ቄሮም ሁን የታገልከው ሰውን ከመሰለህ ተሳስተሃል ።የታገልከው ክፉ አሳብን ነው ይህ ባይሆን ኖሮማ ይቅርታ ብሎ ነገር ድርድር ብሎ ሃሳብ ትርጉም ኣይኖረውም ነበር።የታገልከው ስርአት አልበኝነትን ነው፣የታገልከው ጨለማ ሀሳብን ነው!!የታገልከው ግለኝነትን እና መሃበረሰባዊ ጉዳትን ነው።ያሰው ያንን ክፉ ሃሳብ ሲተው ወንድሜ ብለህ ታቅፋዋለህ ምክንያቱም ያንተ ትግል ከክፉ ሃሳቡ ጋር እንጂ ከሰውዬው ኣይደለማ!! ይሁንና ብቻህን ታግለህ የጣልከው ስርኣት ብቻህን ታግለህ ያቆምከው እውነትም ዬለም።በመጥፎ ስርዓት ውስጥ ጉዳቱ የወል እንደሆነ ሁሉ ያንን ክፉ ስትዓትም ካስወገድክ በኋላ ጥቅሙንም የጋራ ለማድረግ መታገል ኣለብህ።ኣንት ብቻህን እንዳልተጎዳህ ሁሉ ብቻዬን ልጠቀምም ኣትበል።ስለዚህ የተሻለች አንድ ሀገር ለማምጣት የሚፈልግ ሁሉ በተለያየ መልኩ ታግሏልና ትግል በኔ ቀረ ኣትበል። የሰው ዘር ስለመሆንህ ይህን ያህል ከነገርኩህ ሰው ስለሆንክ ይበቃሀል። ወይ ሀሳቤን ትጋራለህ ወይ ሐሳቤን በሐሳብህ ትሞግታለህ ነገር ግን ከኔነቴ ጋር ከሆነ ፀብህ ራስህን መርምር ።እንደ ምክር ግን ፀብህ ከእኔ ጋር ሳይሆን ከሐሳቤ ጋር ይሁንእላሃለሁ። የምትጠላውም ሀሳቤን እንጂ እኔን አይሁን የሚለውን ኣክልልሃለሁ። ሰፊውን ሁለንተና (UNIVERSE) እንድትገዛ ከሁለንተና (UNIVERSE) ራሱ የሰፋ አእምሮ እጅግ የተወሳሰበ ኣሰራር ያለው ግን ጥርት ኣድርጎ ሚያስብ ማሰቢያ የተሰጠህ የሰው ዘር ሆነህ ተፈጥረሀልና እንደ ነቁጥ ጠበህ አትገኝ።
ኣስተያየት ካላችሁ ጸሃፊውን በዚህ አድራሻ hssen631@gmail.com ማግኘት ይችላሉ።