>

በኖርዌይ-ኦስሎ፤ በነገው ዕለት እንግሊዝና የመን ኤምባሲ ፊት-ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ ይደረጋል!

በዓለም ላይ ኣቶ ኣንዳርጋቸውን ለማስፈታት የሚደረጉት እንቅስቃሴዎች በመቀጠል ላይ ናቸው። andargachew posterየዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ፣ የግንቦት 7 ዋና ጸሓፊ ኣቶ ኣንዳርጋቸው ጽጌ የመን የታገቱበትን ምክንያት በማድረግ በኖርዌይ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያኖች የድርጅቱ ኣባላትና፣ ደጋፊዎች ሰላማዊ ሰልፍ ጠርቶኣል። ሰልፉ የሚደረገው በእንግሊዝና በየመን ኤምባሲ መሆኑ ታውቋል።

በነገው ዕለት  የሚደረገው ሰልፍ፣ የመን ውስጥ የታገቱት የግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዲሞክራሲ ዋና ፀሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ የተወሰደውን የአፈና እርምጃ ለመቃወምና፤ በዓለም ኣቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ ተጽዕኖ በመፍጠር ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በኣስቸኳይ ከእስር እንዲፈቱ፣ ብሎም ለኣሸባሪው ለወያኔ ስርዓት ተላልፈው እንዳይሰጡ መሆኑ ከዲሞኪራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድርጅት ኖርዌይ የተቃውሞ ሰልፉ ኣስተባባሪዎች ለማወቅ ትችሎኣል።

ሰልፉ በእንግሊዝ ኤምባሲ የሚሆንበት ምክንያት ኣቶ ኣንዳርጋቸው ጽጌ የእንግሊዝ  ዜግነት ያላቸው ስለሆነ፣ የእንግሊዝ መንግስት በጉዳዩ ጣልቃ እንዲገባና ተጽዕኖ እንዲፈጥር ለማሳሰብ እንደሆነም ተገልጾኣል።

Filed in: Amharic