>

ከቡራዩና አካባቢው ለተፈናቀሉ ዜጎች ታማኝ እና ቴዲ ደርሰውላቸዋል!!

ከቡራዩና አካባቢው ለተፈናቀሉ ዜጎች ታማኝ እና ቴዲ ደርሰውላቸዋል!!

ግዮን ሚድያ
አርቲስት ቴዲ አፍሮ አንድ ሚልዮን ብር ሰጠ
አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) በአዲስ አበባ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ቡራዩና አካባቢው በተፈጸመ ጥቃት ሳቢያ ለተፈናቀሉ ሰዎች ሐሙስ መስከረም 10 ቀን 2010 ዓ.ም. የአንድ ሚሊዮን ብር እርዳታ አደረገ፡፡

‹‹እርስ በርሳችን ተዋደንና ተፋቅረን መኖር ሲገባን በአገራችን እንዲህ ዓይነት ድርጊት መፈጸሙ ሊኮነን ይገባል፤›› ሲል  የተናገረው ቴዲ አፍሮ፣ ‹‹ባላሰቡትና ባልገመቱት ሁኔታ በተፈጸመ ጥቃት ሕይወታቸውን ላጡት ነፍሳቸውን በአጸደ ገነት ያኑርልን፣ ቤተሰቦቻቸውንም ያጽናልን፣ እንዲህ ዓይነት ነገር ድጋሚ እንዳይከሰት ለፍቅር ተግተን መሥራት ይገባናል፤›› በማለት መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

በተያያዘ :- አክቲቪስትና የሰብአዊ መብት ተሟጋች ታማኝ በየነ 115 ሺህ ዶላር በ ጎ ፈንድ ሚ አሰባስቦላቸዋል

በታማኝ በየነ የሚመራው ግሎባል አልያንስ ከቡራዩና አካባቢው ለተፈናቀሉ ወገኖች በ48 ሰዓታት ውስጥ ከ115 ሺህ ዶላር በላይ አሰባስቧል::

“እኔ ከሀያ ሁለት አመት በኋላ ወደ አገሬ ስመጣ ህዝቡ ከሚገባኝ በላይ ፍቅር እና አክብሮት ሰጥቶኛል እኔም ከልጅነቴ አንስቶ የማውቀው ኢትዮጵያዊነት ይህ ነው! ይሄ አሁን እየተሰማ ያለው በጥቅሉ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እየተሰማ ያለው ለማየት ቀርቶ ለመስማት የሚሰቀጥጥ ድርጊት በኢትዮጵያውያን ነው እየተደረገ ያለው የሚለውን ለማመን ተቸግሬያለሁ አዛውንቶች፣ነፍሰ ጡሮች፣ ህጻናት…. ” ሩህሩሁ ሆደ ብቡው ታማኝ ከዚህ በላይ መቀጠል አልቻለም  እንባ ቀደመው…ሳግ አነቀው።

  • ታማኛ እኮ ከወረት የነፃ ምርጥ የኢትዮጵያ ጀግና ነው
  • ታማኛ እኮ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ ነው
  • ታማኛ እኮ የህዝብ ቀድሞ ደራሽ ነው
  • ታማኛ እኮ ከህዝብ ጋር አልቃሽ ሆደ ብቡ ነው
  • ታማኛ እኮ ለተቸገረው ህዝቡ ለአዘነው ህዝብ ቀድሞ ደራሽ ነው ምን አለ እዳንተ አይነት ጀግና ሺ ሁኖ በተወለደልን
  • ታማኛችን የኔ ሆደ ብቡ አንተ የሚጠላ የኢትዮጵያ ጠላት ነው ሌለው ህዝብን እያፋጀ ለስልጣን ይሮጣል
  • አንተ ግን ካዘነው ከተጎዳ ከተጨቆነው ህዝብህ ጋ ደም እንባ ታለቅሳለህ ይሄ ነው ኢትዮጵያዊነት

ኢትዮጵያ ለዘላለም በክብር ትኑር

Filed in: Amharic