ቬሮኒካ መላኩ
* በዚሁ ከቀጠለ አገሪቱ እንደ ላቲን አሜሪካ
” ማፊያ ሪፐብሊክ ” ወይም እንደ ሲስሊ
” ዶን ሪፐብሊክ ” ትሆናለች
…
1~ ጃዋር መሀመድ እና ፅንፈኛ ብርጌዱ አዲስአበባ ሳሪስ ላይ ተደገሉ የተባሉት 43 ሰዎች እንደ ኢንዶኔዥያው አውሮፕላን የውሃ ሽታ ሆነው ሲቀሩ ሱዳን ወይም ግብፅ በርሃ ሞቶ በአሰቃቂ ሁኔታ ሆዱ የተሰፋ ምስኪን ወንድም ፌስቡክ ላይ ለጥፎ ህዝቡን ሲያሳፍረው ዋለ።
ይሄም አላዋጣ ሲል የኦነግ ባንዲራ ፊቱን አልብሶ ለጥ ብሎ የተኛ ልጅ ፎቶ ለጥፎ ሲያስገርመን ዋለ ። የኦነግን ባንድራ ለብሶ የተኛው ልጅ እንኳን የሞተ እንቅልፍ እንኳን የወሰደው አይመስልም። ምናልባት Play ውን በብቃት ለመጫወት የሚያበቃ አርቲስቶቹ Rhearse እያሉ የሚጠሩትን የቲያትር የልምምድ ጊዜ በደንብ ስላልነበረው ይሆናል።
…
2~ ሀይስኩል ተማሪ እያለሁ አንድ ያነበብኩት “ውሽንፍር ” የሚል ወደ አማርኛ የተተረጎመ መፅሀፍ ነበር። የዚህ መፅሀፍ ይዘት እንደሚከተለው ነው ፣ አንድ በአሜሪካ ያለ እጅግ ታዋቂ እለታዊ ዜና የሚያወጣ ጋዜጣ አታሚ ድርጅት ነው። ይሄ ጋዜጣ አሜሪካ ውስጥ የተፈፀሙ ትልልቅ ፖለቲካዊ ፋይዳ ያላቸውንና የህዝብ ስሜት የሚቀሰቅሱ ዜናዎችን ማንም ሌላ ጋዜጣ ሳይቀድመው ያወጣል። ዜናውን ማንም ስለማይቀድመው የጋዜጣው የሽያጭ ኮፒ ብዛት የትየለሌ ገቢያቸውም ተቆጥሮ የማያልቅ ሆነ ።
የዚህ ጋዜጣ ስኬት ያስደነቃቸው ሌሎች የጋዜጣ አሳታሚዎች በሚስጥር ቡድን አዋቅረው አነፍናፊ መርማሪ ጋዜጠኞችን አሰማርተው ያን የጋዜጣ አሳታሚ ድርጅት መሰለል ጀመሩ። መጨረሻ ምን ሆኖ ቢገኝ ጥሩ ነው ? ያ ታዋቂ የጋዜጣ አሳታሚ በአደራጃቸው ማፊያዎች ራሱ ወንጀሉን ፈፅሞ ፣ የሚገድለውንም ገድሎ ፎቶውን አንስቶ ዘገባውንና ዜናውን ሰርቶ ለጧት የቁርስ ጊዜ ንባብ ያደርስላቸዋል።
ምን ማለቴ ነው አሁንም የእነ ጃዋር አቅጣጫ ወደዚያ መሆኑ አየይቀርም።
3~ አሁን ሰሞኑን ይገባሉ ተብሎ ዜና የተሰራላቸው የኢህአፓ የአዛውንቶች በወጣትነታቸው አንድ የጠረባ ቡድን እንደነበራቸው በየመፅሀፉም አንብበናል በየኢንተርቪውም ሰምተናል ። ይሄን የጠረባ ቡድን ” The Crocodile ” ( አዞዎቹ) ይሉት ነበር ። ሲያንቆለጳጵሱት ደግሞ ” The ክሮክ ” ይሉት ነበር ። የዚህ የጠረባ ቡድን ስራ የኢህአፓ መሪዎች የሚሉትን የሚቃወም ሁሉ መጥረብ ነበር። ቀይ ሽብር ለሚባለው የደርግ ዘግናኝ ጭፍጨፋ የዳረገን ” ዘ ክሮኮዳይል ” የተባለው የጠረባ መንጋ የፈፀመው “ነጭ ሽብር ” እንደሆነ ይታመናል።
ጃዋርም ከኢህአፓ ትምህርት የወሰደ ይመስላል የራሱ የጠረባ መንጋ አለው።
…
4 ~ ጃዋር መሀመድ አገር ቤት እንደገባ በትእቢት ተወጥሮ አንድ በየአዳራሹ የሚደጋግማት አባባል ነበረች ። ይች አባባል ” እንደ አንድ ፖለቲካ ሳይንቲስት ልምከራችሁ ” የምትል ናት ። ልክ በረከት ስምኦን በ1983 የአዲስአበባ ዩኒቨሪሲቲ ሄዶ ልደት አዳራሽ የታሪክ ፕሮፌሰሮችን ሰብስቦ ታሪክ እንዳስተማረው መሆኑ ነው።
በመሰረቱ መንጋ ማስከተልና የፖለቲካ ሳይንቲስት መሆን እጅግ በጣም የተለያዩ ናቸው። ይልቁንስ የአእምሮ Wave lengthችን ሆነ ፖለቲካውን በመተንተን ከጃዋር ባዶ መፎግላት የሚበልጥ ስላለን ስሙን።
…
5~ በመሬት ላይም ሆነ በሳይበር ፈር የለቀቀውንና እና ጥላቻን ኢንስትጌት እያደረገ የሚውለውን ጃዋርን በጉያዋ እሹሩሩ እያለች የታቀፈች አገር ፣ ህዝብና መንግስት መፃኢ እጣ ፈንታቸው ምንድነው?
አገሪቱ በ 1970ዎቹ አደገኛ ማፊያ ይርመሰመስባቸው እንደነበሩት እንደ ላቲን አሜሪካ አገሮች ” ማፊያ ሪፐብሊክ ” ወይም እንደ ሲስሊ ” Don Republic ” ትሆናለች። ከፍተኛ ባለስልጣኖች ” ዶኑን ” ከተቃወሙ ይወገዳሉ ። አገሪቱም በሞት አፋፍ ላይ የምታጣጥር የ War lords መናሃሪያ ትሆናለች። ይህ ከመሆኑ በፊት ሳይቃጠል በቅጠል ነውና መንግስት የመንግስትን ሚና ይወጣ።