>
11:06 pm - Tuesday August 16, 2022

አዲስ አባበ የሰማንያ አንድ ጎሳ ሀገር ነች - ኦሮሞም አንዱ ነው!!! (ሉሉ ከበደ)

አዲስ አባበ የሰማንያ አንድ ጎሳ ሀገር ነች – ኦሮሞም አንዱ ነው!!!
ሉሉ ከበደ
እርግጥ ኦነግ እንደአሜባ ተቆራርጦ ተራብቶ አምስት ቦታ ይሁን እንጂ የሁሉም ልብ አንድ ነው-ኢትዮጵያን ማጥፋት!!!
 
* ወያኔ 1984 በወተር በቆቦ ከሁለት አመት በፊት ደሞ በካራሚሌ ና በሶማሌ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች  ያን ሁሉ ድሀ የኦሮሞ አርሷደር ካንድ ቤተሰብ እስከ አምስት ሰው ሲፈጅ ፤ ሲያስፈጅ ያልተሰጠ መግለጫ ዛሬ ከየት ለምን መጣ? !!”)
አለማየሁ እሸቴ”ማን ይሆን ትልቅ ሰው ” ብሎ መዝፈኑ ታላላቅ የሚላቸው ሰዎች አንሰው ሲያገኛቸው መሆን አለበት ብየ አመንኩ። የኦሮሞ ህዝብ ውክልና ባይሰጣቸውም የኦሮሞ ድርጅት ነን ፤ የኦሮሞ ህዝብ ተወካይ ነን ፥ የሚሉት እነጅሎሞሮን አቋማችን ብለው ሰሞኑን የሰጡት መግለጫ አገሬውን ሁሉ እንዳስደነገጠ እኔንም አስደንግጦኛል።ምኑ ያስደነግጣል ትሉ ይሆናል ። መግለጫውን ጃዋርም ይጻፈው ህውሀት አምጥቶ ይስጣቸው ፤  ሲሰጣቸው አንበብበውት ትልልቅ የምንላቸው ሰዎች ሁሉ ተስማምተውበት “አዎ ይሄ ነው አቋማችን በሰሞኑ የሀገሪት ወቅታዊ ሁኔታ ላይ” ብለው ማወጃቸው  ነው።
ኦነግ በድሜ ብዛት ተመንዝሮ ተዘርዝሮ አምስት ሆኖ አገርቤት ሰፍሯል።የሁሉም ተወካዮች የጋራ መግለጫችን ብለው ነው በኦቦ በቀለ ገርባ በኩል ያነበቡልን ። እርግጥ ኦነግ እንደአሜባ ተቆራርጦ ተራብቶ አምስት ቦታ ይሁን እንጂ የሁሉም ልብ አንድ ነው።ኢትዮጵያን ማጥፋትም የልብ ትርታቸው ነው።
አሳፋሪ ነገራቸው ሰብ አዊነት የሌለው አረመኔያዊ አቋማቸው ነው።ሰው ተገደለብን ። ሰው ተገደለ ሲሉ ሰው ማለት ለነሱ ኦሮሞ ብቻ ነው።”በቀለ ገርባ ይፈታ ” ብለን ያልጮኽነውን ያህል፤  የአማራ ወጣቶች “በቀለ ገርባ መሪያችን እንጂ አሸባሪ አይደለም” ብለው ያልጮኹለትን ያህል ወርዶ ወርዶ ከኦሮሞ በቀር ሌላውን ሁሉ የሚያጠፋ  ዝቅጠት ውስጥ ተገኘ።
“የኦሮሞን ማንነት ለማጥፋት እየተደረገ ያለውን ሙከራ በተመለከተ” ብለዋል ።የኦሮሞን ማንነት ሊያጠፋ የተነሳ ወገን መኖሩን ዛሬ ከየት አምጥተው ነው የሚያወሩት? ወያኔ አብዲ ኢሌን አሰማርቶ ያን ሁሉ ፍጅትና ሰቆቃ በወገኖቻችን ላይ ሲፈጽም ያላነሱትን ነገር  ዛሬ ምን ፈልገው ነው ህዝብን ለበቀል የሚያንሳሳ ነገር የሚያውጁት? ወያኔ 1984 በወተር በቆቦ ከሁለት አመት በፊት ደሞ በካራሚሌ ና በሶማሌ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች  ያን ሁሉ ድሀ የኦሮሞ አርሷደር ካንድ ቤተሰብ እስከ አምስት ሰው ሲፈጅ ፤ ሲያስፈጅ ያልተሰጠ መግለጫ ዛሬ ከየት ለምን መጣ? ቡራዩ ላይ አንድ ህጻን ባሰቃቂ ሁኔታ መገደሉን ነግረውናል ። አዎ የሰውን ልጅ መግደል  በኢትዮጵያ ውስጥም ሆነ በየትም ተቀባይነት የለውም። ወንጀለኛውን ለፍርድ ማቅረብ የመንግስት ሀላፊነት ነው። በቡራዩ አንድ ህጻን ብቻ አይደለም የሞተው።  ሀምሳ ሰዎች በገጀራና በዱላ ተቀጥቅጠው ባሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን አምነስቲ አረጋግጧል። የወንጀሉ ፈጻሚዎችም ቄሮ ነን የሚሉ የኦሮሞ ልጆች መሆናቸውን በቪዲዮም በፎቶም አይተናል። እነዚህ በቄሮ የተጨፈጨፉ ወገኖችቻችን ወገኖቻቸው   አይደሉም?  ሰዎች አይደሉም? በመግለጫው ለምን አልተጠቀሱም? በድርጊቱ ማዘናቸውን እንኳ ለምን አልነገሩንም?
“አዲስ አበባ የኦሮሞ ነች” ብለዋል። አዎ የኦሮሞ ነች ማንም እንዲነግረን አንፈልግም።ግን ለኦሮሞ ብቻ ማን ሰጠው? ኢትዮጵያ የምትባል ምድር በሰማንያ አንድ ጎሳ ደም የተገነባች ሀገር ነች። አዲሳባ የኢትዮጵያ እምብርት አካል ነች። ማናባቱ ነው ከዚህ ወዲያ ያንተ ከዚህ ወዲ የኔ ብሎ የመሸንሸን ስልጣን  የተፈቀደለት? ወያኔን የምንታገለው ለምንድነው? ” ሀገራችን የጋራችን ናት አትከፋፍሉን ” ብለን አይደለም? እነ ጅሎሞሮ ከወያኔ ተረክበውን ቀጣዩን ዘመናችንን በባርነት ሊገዙን ነው? አዲስ አባበ የሰማንያ አንድ ጎሳ ሀገር ነች። ኦሮሞ አንዱ ነው።
አይናቸውን የገለጠላቸው ኢሳት ላይም ዘምተዋል። ኢሳት ማለት የኢትዮጵያ ህዝብ አንድነት ባልተጠበቀ ሁኔታ ዳግም እንዲያንሰራራ ያደረገ ተቋም ነው።የኢትዮጵያ ትንሳኤ እውን እንዲሆን ያደረገ፤ እነዶክተይ አብይ አህመድ እያዳመጡ የተማሩበት፤የተገፉ፤ የተበደሉ፤  የታሰሩ፤ የተገረፉ ፤ኢትዮጵያውያን ከመላው የአለም ጥግ ከሀገርም ውስጥ ድምጻቸውን ያሰሙበትና ደራሽ ወገን ያገኙበት ተቋም ነው። በኢትዮጵያ ያሉትን ሰማንያ አንድ ጎሳዎች የሚወክል አንድ አድርጎ የተጓዘ ብሄራዊ ቅርስ የሆነ የሚዲያ ተቋም ነው።
እሱን ለማዘጋት ወያኔ በቢሊዮን የሚቆጠር ብር ሰርቆ ከደበቀበት ያስወጣው የጀግኖች መፋለሚያ ተቋም ነው። እርግጥ ለጸረ ኢትዮያ ሀይሎችና ለዘረኞች እንደኮሶ የሚመር ሊውጡት የሚያንገሸግሽ መድሀኒት ነው። ዛሬ ኢሳትን ጸረ ኦሮሞ ነው የሚሉት ራሳቸው ጸረ ኦሮሞ የሆኑ ኦሮሞዎች እያንዳንዳቸው በኢሳት ላይ ሲናገሩ ያላየ ያልሰማ የለም። ጃዋር የሚባለው የመርዝ ብልቃጥ በራሳቸው በኦሮሞዎቹ ዘንድ እንዲታወቅ ያደረገው ማነው? እነጃዋርና ጓደኞቹ መላው ኢትዮጵያዊ ኢሳትን የኔ ብሎ በሙሉ ልብ ሲከታተለው ሲያዩ ኦሮሞውም የኔ ብሎ ብሶቱን ሲገጽበት ሲያዩ በቅናት ተነሳስተው ኦሮሞውንማ መነጠል አለብን ብለው የኦሮሞ ሚዲያ ኔት ወርክ ብለው አቋቋሙ።
ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ አስር ሺ ሰው ቢጨፈጨፍ እነጃዋር አስራ አምስት ኦሮሞ አብሮ ካለ ያንን ቆጥረው ነው” አስራ አምስት ሰው ሞተ” ብለው በኦ.ኤም.ኤን የሚነግሩን።
 እስካሁን በለመድነው አሰራራቸው። ታዲያ በየትኛው የሞራል ብቃታቸው ነው ኢሳትን ጸረ ኦሮሞ ነው የሚሉን?
የዘሩን ፈደራሊዝም እንፈልገዋለን ብለዋል። አይደንቅም ወያኔ ቂጥ ስርስር ይሉ የነበረ  ጊዜ የወያኔን ህገመንግስት አጨብጭበው ተቀብለዋል። በጭብጨባ የጋለው እጃቸው ሳይቀዘቅዝ ነው ያኔ በርግጫ ብሎ ከሀገር ያባረራቸው። ያንን ህገመንግስት ሲያረቁ ከኦሮሞ ቀጥሎ ትልቁ የኢትዮጵያ ህዝብ አማራው አልተወከለም። ይህ ብቻውን ውድቅ ያደርገዋል የወያኔን ህገመንግስት። የጎሳ ፈደራሊዝም በአለም ላይ ዩጎዝላቪያ ብቻ ነበር። ያም ቦንብ ሆኖ ፈንድቶ  ሀገሪቱን  አፈረሳት። ወያኔ ካባረራቸው በኋላ ኦነጎች አስር ጊዜ ሳይጠራቸውም ሲጠራቸውም እንደውሻ ሲመላለሱ ሀያሰባት አመት አሳለፉ። ጦር አለን ይላሉ ጦርነት እሸንፈው አያውቁ። አርባ አመት ታገልን ይላሉ አንዲት መንደር ነጻ አላወጡ። እንደ ጥንብ አንሳ ሌሎች የጣሉት ነገር ላይ መረባረብ ያውቃሉ።እነጅሎሞሮ እባካችሁ እንደሰው አስቡ። እናንተ የኦሮሞን ህዝብም አትወክሉም።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
ሞት ለዘረኞች!! ፍቅርና አንድነት ያሸንፋል።
Filed in: Amharic