>

ዐቢይ፣ አዲስ አበባ እና እነ ነፈዞ!!! (ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው) 

ዐቢይ፣ አዲስ አበባ እና እነ ነፈዞ!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው 
የምትፈልገውን ይነግሩህ እና የሚፈልጉትን ይሰሩብሀል!!
 
ወይ ጉድ! ዐቢይ በተሿሚው ታከለ ኡማ በኩል የአዲስ አበባን ነባራዊ ምኅዳር (demography) ለመለወጥና ኦሮሞን ተጠቃሚ ለማድረግ አዲስ አበባ ላይ እየሠራ ያለው ደባ፣ የመሬት ወረራ ወይም ዝርፊያ እና የሰነድ ማጭበርበር ወዘተረፈ. ጉድ አሰኝቶም የሚያበቃ አይደለም፡፡
የዐቢይ አሥተዳደር አሁን ከምትሰሙትና ከምታዩት የመሬት ዝርፊያና ወረራ በፊት እንቅፋት ይሆናሉ ብሎ ያሰባቸውን የመስተዳድሩን ኃላፊዎች በማንሣት እጅግ በርካታ የአዲስ አበባ ነዋሪ ላልሆኑ የኦሮሞ ወጣቶች የአዲስ አበባ መታወቂያ የማደል ሰፊ ሥራ ሲሠራ ነበር የሰነበተው፡፡ አሁንም አላቆመም፡፡
ይሄ ደባ የኦሮሞን ወጣቶች የኢኮኖሚ ተጠቃሚ ከማድረግ በተጨማሪ የአዲስ አበባን ምርጫ ለመብላትና በሕዝበ ውሳኔ አዲስ አበባን ኦሮሚያ ክልል የሚሉት አካል ለማድረግ ያስችላቸዋል፡፡ ይሄንን አስበው ነው ይሄንን ውንብድና በሰፊው እየከወኑ ያሉት፡፡
አስገራሚው ነገር በታከለ ኡማ ውሳኔ እየተሠሩ ያሉ ሰፋፊ እና ግዙፍ አሥተዳደራዊ የለውጥ ሥራዎች በሙሉ “በምርጫ የአዲስ አበባን አሥተዳደር ሥልጣን ያዘ!” ተብሎ ሲሠራ የቆየውና የሥልጣን ዘመኑ በመጠናቀቁ ቀጣዩ የአዲስ አበባ አሥተዳደር በሕዝብ ተመርጦ እስኪረከብ ድረስ ዕለታዊ አሥተዳደርን በተመለከተ ክፍተት እንዳይፈጠር በአደራ ጠባቂነት በተቀመጠ ጊዜያዊ ሹመኛ አካል ሊሠሩ የማይችሉና ሕግ የማይፈቅዳቸው ውሳኔዎችና ሕገወጥ ሥራዎች ናቸው እየተሠሩ ያሉት፡፡ ለነገሩ ከአሿሿሙ ጀምሮ ሕገወጥ የሆነንና ውንብድና የተሞላን ነገር እንዴት ሕጋዊ ነገር ይጠበቅበታል??? በሕገወጥ መንገድ የመጡትስ ይሄንን የውንብድና ተግባር ለመፈጸም አይደለም ወይ???
እጅግ የሚደንቀኝ ነገር ዐቢይ ሕግ ጥሶ ታከለ ኡማን ሲሾም ይህ ሕገወጥ ተግባሩ በሸንጋይ ቃላት ሸሽጎ የያዘውን ሸፍጠኛ ጠባብና ጠንቀኛ አስተሳሰቡንና ማንነቱን፣ በከተማዋ ብሎም በሀገር ላይ ሊሠራ ያሰበውን ውንብድና በግልጽ የሚያሳይ ወይም የሚጠቁም ሆኖ እያለ ከዚህ ተግባሩ በኋላም የሞቀ ድጋፍ እየሰጡ ሥልጣኑን ያደላደሉለትና አሁንም ስንት ነገር ዕያዩ ድጋፋቸውን በመስጠት ላይ ያሉ፣ ተስፋቸውን እሱ ላይ የጣሉና የተደገፉበት ከምሁራን እስከ ፖለቲከኛ ያለው ነፈዝ መንጋ ነው፡፡ እነኝህ ወገኖች እንዴት እንደሚገርሙኝ ባትጠይቁኝ ይሻለኛል፡፡
ይሄ ብቻ መሰላቹህ የሚገርመው እነኝህ ነፈዞች ይሄንን ሁሉ ጉድ ዕያዩና እየሰሙ አሁንም ዐቢይ ዐቢይ ማለታቸውን እኮ አላቆሙም!!! ከዚህ በላይ ንፍዘት ምን “አለ!” ልትሉኝ ትችላላቹህ???
አንዳንዱ ግን ማለቃቀስ ጀምሯል፡፡ ምን ዋጋ አለው አሁን ቢያለቅሱት እነ ነፈዞ??? ገና ከጅምሩ የዐቢይ ባቡር ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ብሎ ጭኖ ሲያበቃ ወደጎጡ ሲወስድህ ዝም ብለህ ተጉዘህ ስታበቃ አሁን “ለምን የራስህ ጎጥ ውስጥ ወስደህ አራገፍከን?” እያልክ ብትጮህ ምን ዋጋ አለው??? ያኔ ገና መሪውን ዚያዞር “ወራጅ አለ!” ብለህ ያልወረድከውንና ዓይንህ እያየ ጆሮህ እየሰማ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ እያለ አቅጣጫ ቀይሮ ወደ ጎጡ ጭኖህ ሲሸመጥጥ ዝም ጭጭ ብለህ የተጓዝከውን አሁን ብትንጫጪ ምን ይፈይድልሻል እነ ነፈዞ???
በጣም የሚገርማቹህን ነገር ልንገራቹህ? አጭሉጉ ዐቢይ እነኝህ አሁን እያለቃቀሱ እየጮሁ ያሉ ወዳጆቹን ወይም ደጋፊዎቹን “አሃ ለዛ ነው እንዴ? እንደሱ ከሆነስ እሽ!” አሰኝቶ በማጃጃል ዝም ሲያሰኛቸውና ድጋፋቸውን መስጠታቸውን እንዲቀጥሉ ሲያደርጋቸው ታያላቹህ፡፡
ምን ብሎ መሰላቹህ ዝም የሚያሰኛቸውና ድጋፍ መስጠታቸውን እንዲቀጥሉ የሚያደርጋቸው? “በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ ኦነግ ሰፊ ድጋፍ እንዳለው ታውቁ የለም እንዴ? ሕዝቡን ከኦነግ ጎራ ነጥለን ወደ እኛ ለማምጣትና ኦነግን ለማሸነፍ የምንጠቀምበት ዘዴ ነው፡፡ እና ታገሱ እንጅ? እንተማመን እንጅ? ሀገር የማረጋጋቱ ሥራ ምን ያህል ውስብስብና ጊዜ የሚጠይቅ እንደሆነ እያወቃቹህ ለምን እንደዚህ ትሆናላቹህ? ለዚህ የተቀደሰ ዓላማ ሲባል ገና እኮ ከዚህም የከበደ ነገር እናደርጋለን! እና እመኑን እንጅ አትጠራጠሩን እሽ??? ድግ የላቹህም በእኛ ይሁንባቹህ እሽ???” ብሎ ነው የሚያጃጅላቸው፡፡
እነ ነፈዞም አማራን የጎዱ መስሏቸው የኦሮሞን ሕዝብ ወይም የቁቤውን ትውልድ ጠባብ አድርገው ፀረ ኢትዮጵያ መርዘኛ ስብከት እየሰበኩ ከኦነግ ካምፕ ወይም ጎራ ውስጥ የከተቱት እነ ዐቢይ ወይም ኦሕዴድ መሆኑን እና “ኦሮሞ ሊያገኘው ይገባል!” የሚሉትን ጥቅም እንዲያገኝ ለማድረግ ከጀርባ ሆነው እየገፋፉ ኦሮሞ ሊያነሣ የማይገባውን ጥያቄ እንዲያነሣ እንዲያስተጋባ የሚያደርጉት እነ ዐቢይ ወይም ኦሕዴድ መሆኑን አያውቁም አያስቡምና ያምኑታል፡፡ አምነውትም መጃጃላቸውን ይቀጥላሉ፡፡
ቆይ ግን አሁን የአዲስ አበባ ሕዝብ ሆይ! ይሄንን የጠባብና ጽንፈኛ ኦሮሞዎችን ውንብድና በዝምታ ልንመለከት ነው ወይ??? ይሄንን ውንብድና በዝምታ ተመለከትን ማለትኮ ከተማዋን ያለ አንጃ ግራንጃ አስረከብን፣ አሳልፈን ሰጠን፣ የበይ ተመልካች ሆንን፣ “ወራሪ ሰፋሪ ነው!” መባልህን ተቀበልክ ማለት እኮነው ልብ ብለኸዋል??? ነገ ደግሞ “ውጣ!” ትባላለህ፡፡ ይሄንን ነው የምትፈልገው??? ካልሆነ ውጣ!!! ውጣና የነ ዐቢይን የውንብድና ተግባር ተቃወም አስቁም!!!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
Filed in: Amharic