>

ለአዲስአበቤነትህ፣ ለኢትዮጵያዊነትህ የሚከፈል ዋጋ ነውና ኩራት ይሰማህ!! (ኤርሚያስ ለገሰ) 

ለአዲስአበቤነትህ፣ ለኢትዮጵያዊነትህ የሚከፈል ዋጋ ነውና ኩራት ይሰማህ!!
ኤርሚያስ ለገሰ 
አዲስአበቤ! የጦላዩ ዘንዶ፣ እባብ፣ ቢጫ ወባ፣ የውሃ ጥም፣ የፀሃይ ሃሩር እንዴት እየገፋኸው ነው? በበታችነት ስሜት የሚሰቃዩት ተበቃዮችህ አውጫጭኝ እንዴት እያደረገህ ነው?…
ለአገር ባለቤትነትህ፣ ለነፃነትህ፣ ለአዲስአበቤነትህ፣ ለኢትዮጵያዊነትህ የሚከፈል ዋጋ ነውና ኩራት ይሰማህ። ነገ ተበቃዮችህ በአደባባይ ወጥተው ” የአዲስ አበባ አጥፊ ወጣቶች በጦላይ ተሃድሶ ተሰጥቷቸው ወደ ህብረተሰቡ ተቀላቀሉ!” የሚል ዜና ይሰሩብሃል። ነውራቸውን ገልጠው አልጨረሱምና ” አይደገምም!” የሚል ቲሸርትም ሊያለብሱህ ይችላሉ። ” ተሃድሶ ወስጄ ነበር! በድርጊቴ ተፀፀቻለሁ፣ ህብረተሰቡን እክሳለሁ!” እንድትል የመንግስትና የፓርቲ ሚዲያ ላይ እንድትናገር ሊያስገድዱህ እና ማይክ ፊት ሊገትሩህ እንደሚችሉም እናውቃለን።
ለአእምሮ ገራፊዎችህ እየሳቅክ የሚፈልጉትን በልላቸው። በዘር የማይሰባሰበው የአራዳ ልጅ ክብርና ኩራቱ በልቡ መሆኑን አሳያቸው። በአንተ የፀና ትግል አዲስ አበባ ለአዲስአበቤ እንደምትሆን የሰናፍጭ ቅንጣት ይህል ጥርጣሬ እንዳይገባህ። አዲስአበቤነት ኢትዮጵያዊነት ነው!
Filed in: Amharic