* ከታች ከተጠቀሱት 9 ወሳኝ ቦታዎች መካከል ኦዴፓ 5 ፣ ደኢህዴን 2 ፣ ህወሃት 1 ፣ አብዴፓ 1 ፣ ኢሶዶፓ 1 ሲያገኙ ፣ የኛዉ ጉድ አዴፓ በብላሽ ባዶዉን መዉጣቱ የትላንቱ ብአዴን የዛሬዉ አዴፓ ከተላላኪነትና ከአጋፋሪነት ያለፈ ድርሻን መወጣት የማይችል መሆኑን እንረዳለ!!!
አብይ አህመድና ከመጋረጃ ጀርባ የመሸጉት ስትራቴጂስቶቹ በደንብ የተጠና ፣ ስልታዊ ፣ በመደመር ሰበብ አዴፓን በመሸንገል የተተገበረ የፓለቲካ ጨዋታ በድል ጀምረዋል፡፡ የፌደራል ወሳኝ ሚኒስትር መስሪያቤቶችን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በኦሮሞ የመዉረርና የመቆጣጠር ፕሮዢ ለአማራዉ ህዝብ አይን ያወጣ ክህደትና ሸፍጥ ነዉ፡፡ ህዝባችን በአዴፓ ላይ ለሁለት ሳምንት ጥሎት የነበረዉን “ሊለወጡ ይሆን” ተስፋ ጊዜ ሳያባክን ስህተት መሆኑን ያሳየ ማኪያቬሊዊ ክስተት ነዉ፡፡ የአማራ ህዝብ አዲሱን የአብይ አህመድ ካቢኔ በምንም መልኩ እዉቅና የማይሰጠዉ ሲሆን ፤ ይህ አይን ያወጣ ሸፍጥ ግን በረከተ መርገምት ይዞልን እንደመጣ ግልጽ ነዉ፡፡ ባለጭምብሉ አብይ ጭምብሉን አዉልቆ ጥሎ በትክክለኛ ማንነቱ የተገለጸ ሲሆን ፤ ህዝባችን ለወራትም ቢሆን የማይጨበጥ ተስፋ በማድረጉ ጥቂት ሲጎትተን ነበር፡፡ ዛሬ ላይ ሆነን ግን “እኩል የጾታ ስብጥር” ካቢኔ በማዋቀር ስም በመሰራት ላይ ያለዉን የአብይ አህመድን ጭልጥ ያለ አምባገነንነት አይተንበታል፡፡ደመቀን በተቀነባበረ መንገድ በወታደር የደሞዝና ጥቅማጥቅም ጥያቄ ሰበብ በማስወገድ ቤተ-መንግስቱን ብቻዉን መያዝሞክሮ ከሸፈበት እየተባለ የሚታማዉ አብይ ፣ ዛሬ ደግሞ ቁልፍ ሚኒስትሪዎችንና በስራቸዉ ያሉ ተጠሪ መስሪያቤቶችን አዲስ ሹመትና አወቃቀር በማየት ብቻ አማራን ከወሳኝ የዲፕሎማሲ ፣ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ፣ ፀጥታ ፣ መከላከያና ደህንነት ተቋማት ሙሉ በሙሉ ያገለለ እንደሆነ ለመረዳት አብይም ሆነ ነብይ መሆንን አይጠይቅም፡፡ ዳግማዊትን የመሰለች ብቁ የአዲስ አበባ አማራ የአዴፓ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሆና በመመረጧ ኦዴፓና አብይ ደስተኛ አልነበሩም፡፡ ህጋዊ ከንቲባነቱ ለዳግማዊት ይገባል የሚለዉ ጥያቄ እንዳይነሳ ፣ ለአክራሪዉ ታከለ ኡማ የስልጣን ተፎካካሪ እንዳይፈጠር ፣ አማራም በአዲስ አበባ አስተዳድር ድርሻ እንዳይኖረዉ ዳግማዊትን ገሸሽ በማድረግ በሙስናና ብልሹ አሰራር የተጨማለቀዉን ታርጋ ለጣፊ መስሪያ ቤት እንድትመራ ሹመት ሰጠሁ ብሏል፡፡የአብይንና የኦዴፓን ቅጥ ያጣ የስልጣን ጠቅላይነት ጥም ፣ የአዴፓ የአማርኛ ቋንቋ ምሩቃንን ሚኒስትር በማድረግ ለአማራ ህዝብ ያስተላለፈዉ የሾርኔ መልዕክት ፣ ትምህርት ሚኒስቴርን ከሁለት ከፍሎ ለአማራ ማካፈሉ በራሳቸዉ የሚናገሩት ብዙ መልዕክት ነዉ፡፡ አብይ በሚኒስትሮች ምክር ቤት በመገዳደር የአማራን ህዝብ ጥያቄ ያነሳሉ ብሎ ያሰባቸዉን እንደ አምባቸዉ መኮንናና መላኩ አለበል አይነት አማራዎችንም ከካቢኔዉ አስወግዷል፡፡ የተሾሙ አማራዎችም ብዙዎች ለአዴፓ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት እንኳ ያልተመረጡ ዝቅተኛ ፕሮፋይል ያላቸዉ የአዴፓ አባላት መሆናቸዉ አብይ ለአማራ ያለዉን ንቀትና ጥላቻ በይፋ የሚያሳይ ነዉ፡፡ዳግማዊትን ጨምሮ ዶ/ር ሂሩትን የመሰሉ በህዝባችን ዘንድ በበጎ የሚታዩ የአማራ ልጆች ይህን ሸፍጥ በመቃወም አዲሱን ስልጣናቸዉን መልቀቅና የአብይ አህመድን አምባገነንነት በይፋ በመቃወም ከህዝባቸዉ ጋር ካልቆሙ ነገ እነርሱን አያርገኝ፡፡ አምባቸዉም እየተወራ ያለዉን የእንግዳ ተቀባይነቱን ስልጣን ከተቀበለ የፓለቲካ ሞት ለመሞት እንደተዘጋጀም በዚህ አጋጣሚ ይታወቅ፡፡ ከዚህ በኋላ ይህን ሸፍጥ ተቀብሎ አዴፓ ከአብዩ ኦዴፓ ጋር ከቀጠለ የአማራ ህዝብ መቸ ምን ማድረግ እንዳለበት ያዉቃል፡፡ የህወኃትን ቅልጥም ሰብሮ ለልምሻ የዳረገዉ ህዝባችን ክብሩን አዋርደዉ ሊገዙት ለመጡ አምባገነኖች ያደረገዉን ከፍሽስቶቹ ሞሶሎኒና የአገርቤት ተላላኪዎቹ የማይማር ለተመሳሳይ ስህተት መዳረጉ አይቀርም፡፡ኦዴፓ አዴፓን እንደ ስትራቴጅካዊ አጋር ሳይሆን ስልጣኑን የማደላደያ ታክቲካል አጋር አድርጎ ከተጠቀመበት በኋላ ከፌደራል ስልጣን በጠረባ መትቶ አባሮታል፡፡ ከታች ከተጠቀሱት 9 ወሳኝ ቦታዎች መካከል ኦዴፓ 5 ፣ ደኢህዴን 2 ፣ ህወሃት 1 ፣ አብዴፓ 1 ፣ ኢሶዶፓ 1 ሲያገኙ ፣ የኛዉ ጉድ አዴፓ በብላሽ ባዶዉን መዉጣቱ የትላንቱ ብአዴን የዛሬዉ አዴፓ ከተላላኪነትና ከአጋፋሪነት ያለፈ ድርሻን መወጣት የማይችል ፣ ለአማራ ህዝብ የዉርደትና የሃፍረት ምንጭ ከመሆን መዝለል የማይችል ድርጅት እንደሆነ እንረዳለን፡፡1. የሰላም ሚኒስቴር ተጠሪ የሆኑ አስፈፃሚ ተቋማት ዝርዝርi. የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎትii. የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲiii. የፋይናንስ ደህንነት መረጃ ማዕከልiv. የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽንv. የኢሚግሬሽን፣ ዜግነትና ወሳኝ ኩነቶች ኤጀንሲvi. የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ ኤጀንሲvii. የብሔራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽንviii. የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ስትራቴጂክ ጥናት ኢንስቲትዩት ናቸው።2. የአገር መከላከያ ሚኒስቴር ተጠሪ የሆኑ አስፈፃሚ ተቋማት ዝርዝርi. የሀገር መከላከያ ኢንጂነሪንግ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅii. ጋፋት አርማመንትiii. ሆሚቾ አሙኒሽን ኢንጂነሪንግiv. ደጀን አቪየሽን ኢንጂነሪንግv. ብራና ማተሚያ ድርጅትvi. የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝvii. የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅትviii. የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዕቃዎች ማምረቻ ድርጅት ናቸው።3. ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተጠሪ የሆኑ አስፈፃሚ ተቋማት ዝርዝርi. የውጭ ግንኙነት አገልግሎት ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩትii. የዲያስፖራ ኤጀንሲ ናቸው።4. ለገንዘብ ሚኒስቴር ተጠሪ የሆኑ አስፈፃሚ ተቋማት ዝርዝርi. የመንግስት የልማት ድርጅቶች የዞታና አስተዳደር ኤጀንሲii. የኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድiii. የመንግስት ግዢና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲiv. የመንግስት ግዢና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ናቸው።5. ለጠቅላይ ዓቃቤ ህግ ተጠሪ የሆኑ አስፈፃሚ ተቋማት ዝርዝርi. የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲii. የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ጽ/ቤትiii. የፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደርiv. የፍትህና የሕግ ምርምርና ስልጠና ኢንስቲትዩትv. የሠነዶች ምዝገባና ማረጋገጫ ኤጀንሲvi. የፌደራል ግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ናቸው።6. ለንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ተጠሪ የሆኑ አስፈፃሚ ተቋማት ዝርዝርi. የጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩትii. የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩትiii. የብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩትiv. የምግብ፣ የመጠጥና የፋርማሲቲካል ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩትv. የኬሚካልና የኮንስትራክሽን ግብዓቶች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩትvi. የስጋና ወተት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩትvii. የፌዴራል አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች ማስፋፊያ ባለስልጣንviii. የንግድ ውድድርና ሸማቾች ጥበቃ ባለስልጣንix. የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ባለስልጣንx. የኢትዮጵያ ብሔራዊ አክሬዲቴሽን ጽ/ቤትxi. የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲxii. የኢትዮጵያ ብሔራዊ የስነ-ልክ ኢንስቲትዩትxiii. የኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ኤጀንሲxiv. የኢንዱስትሪ ግብዓት አቅራቢ ልማት ድርጅት ናቸው።7. ለገቢዎች ሚኒስቴር ተጠሪ የሆኑ አስፈፃሚ ተቋማት ዝርዝርi. የጉምሩክ ኮሚሽንii. የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ናቸው።8. ለፕላንና ልማት ኮሚሽን ተጠሪ የሆኑ አስፈፃሚ ተቋማት ዝርዝርi. ማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲii. የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ናቸው።9. ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ተጠሪ የሆኑ አስፈፃሚ ተቋማት ዝርዝርi. የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽንii. የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽንiii. የአካባቢ፣ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽንiv. የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽንv. የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክvi. ቱሪዝም ኢትዮጵያvii. የቤተ መንግስት አስተዳደር ናቸው።አዴፓ ይህን ሹመት ተቃዉሞ በይፋ መግለጫ ካልሰጠና ከኢህዴግ እንደሚወጣ አስጠንቅቆ ባስቸኳይ የካቢኔ ማሻሻያ እንዲያደርግ ኦዴፓን ካላስገደደ የአማራን ህዝብ ጥቅም የማስጠበቅ ፍላጎት ፣ አቅምና ቁርጠኝነት እንደሌለዉ ቆጥረን የህዝባችን ጥቅም ፣ ፍላጎትና ክብር ያሚያስጠብቅ ትግል በማድረግ የአማራን ህዝብ ዳግም ዉርደትና አንገት የማስደፋት ሙከራ እናከሽፈዋለን፡፡አማራ በልጆቹ ትግል ታሪኩን ያድሳል!