>
5:18 pm - Friday June 15, 5640

ጠበቃ ሄኖክ አክሊሉ ታሰረ (ጌታቸው ሽፈራው)

 

ጠበቃ ሄኖክ አክሊሉ ታሰረ

 

(ጌታቸው ሽፈራው)

 

በሽብር ክስ ተከስሰው ጠበቃ ላጡ በርካታ ተከሳሾች በነፃ በመቆም ሲያገለግል የነበረው ጠበቃ ሄኖክ አክሊሉ ዛሬ ጠዋት መታሰሩ ታውቋል። ጠበቃ ሄኖክ አክሊሉ ፒያሳ የሚገኘው ቢሮው እያለ በፖሊስ የተያዘ ሲሆን አዲስ አበባ ፖሊስ ወይንም ሶስተኛ ተብሎ የሚታወቀው እስር ቤት ታስሮ እንደሚገኝ ተገልፆአል።

የጠበቃ ሄኖክ ቢሮ ውስጥ የነበሩ ኮምፒውተሩና ሌሎች ቁሳቁሶችም በፖሊስ ተወስደዋል። ጠበቃ ሄኖክ አክሊሉ በሽብር ተፈርጀው የነበሩ ቡድኖች ስማቸው ከፀረ ሽብር አዋጁ ከተነሳ በኋላ በድርጅቶቹ ስም ክስ ተመስርቶባቸው ያልተፈቱ እስረኞችን ጉዳይ እየተከታተለ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።

ሄኖክ አክሊሉ ለእነ ንግስት ይርጋ፣ አቶ ማሙሸት አማረ፣ ለእነ ክንዱ ዱቤ፣ በቂሊንጦ ቃጠሎ ለተከሰሱት እነ መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ፣ በወልቃይት በአጠቃላይ በአማራ ተጋድሎና በማስተር ፕላኑ ጉዳይ ለተከሰሱት ጨምሮ ለበርካቶች ጠበቃ ሆኖ ያገለገለ ሲሆን ለአብዛኛዎቹ በነፃ ሲያገለግል ቆይቷል።

Filed in: Amharic