>
9:12 am - Saturday November 26, 2022

አንድ መሪ "ሀገር ትፈርሳለች" የሚል አሉባልታ ከጀመረ "እኔዉ ብቻ ነኝ አዳኝ"እንደማለት ነዉ!!! (ሚኪ አምሃራ)

አንድ መሪ “ሀገር ትፈርሳለች” የሚል አሉባልታ ከጀመረ “እኔዉ ብቻ ነኝ አዳኝ”እንደማለት ነዉ!!!
ሚኪ አምሃራ
 የዶ/ር አብይ የፓርላማ ዉሎ ለአስተውሎ ተመልካች የሚሰጠው ስእል፦
1. በመጀመሪያ ዶ/ር አብይ በህግ አዉጭ ፊት ሲቀርብ በዋነኛነት ስለ ፖሊሲ፤ ስለ ደህንነት፤ስለ ህግ የበላይነት፤ ስለኢኮኖሚ እና መሰል የሀገራዊ አጀንዳወች ላይ ማተኮር ሲገባዉ እራሱን ሴንተር ያደረገ ንግግር እንዲሁም እራሱን ለመከላከል እያንዳንዷን ስሙ የተነሳበትን አካባቢ በመጥቀስ መልስ ለመስጠት መሞከሩ፡፡ እራሱን መከላከል ከፈለገ ወይም ስለራሱ ማብራራት ከፈለገ ጋዜጠኛ ጠርቶ መግለጫ መስጠት ወይም በአንዱ ሬድዮ ወይም ቴሌቪዥን ኢንተርቪዉ መስጠት ነዉ፡፡
2. አንድ የሀገር መሪ ካልሆነ እለቃለዉ አይነት ንግግር በፓርላማ ፊት ማንሳት ድክመትን እንጅ ጥንካሬን አያሳይም፡፡ ሰወች ተቃወሙኝ ብሎ እዚህ ስሆን ፍልጌ አይደለም የሚል አባባል ከሀገር መሪ አይደለም ከአንድ አነስ ያለ የፋብሪካ መሪ አይጠበቅም፡፡ You projected a sign of weakness bro. A leader is a fighter. A leader is someone who stands firm in times of crisis.
3. የግድያ እና የመፈንቅለ መንግስት ጉዳይን የ PR (Public relation stunt) አካል ማድረጉ፡፡ ሁሌም እኔ ብሞት ሌላ ይተካል፤ ሊገሉኝ ነበር እና የመሳሰሉት ንግግሮች የpublicity ወይም የፕሮፖጋንዳ እንድ አካል አድርጓቸዋል፡፡ ይህ የግድያ ሙከራ የሀገር ድህንነት ጉዳይ ነዉ፡፡ የሀገር አንድንነት ጉዳይ ነዉ፡፡ ለፕሮፖጋንዳነት መዋል የለበትም፡፡ you are the commander in chief. Take actions on those who are trying to kill you. እንዲህ ሊያደርግ የሚችለዉ ሁለት ቡድን ነዉ ያለዉ፡፡ አንዱ ኦነግ ነዉ እሱንም መሪዎቹን በመንግስት ገንዘብ እዛዉ ቤተመንግስት ፊት ለፊት ያለ ሆቴል እየተቀለቡ ነዉ የሚኖሩት፡፡ ሁለተኛዉ ህወሃት ነዉ፡፡ እነሱም መቀሌ በመንግስት ገንዘብ የሆነ ሆቴል ዉስጥ እየተቀለቡ ነዉ ያሉት፡፡ እና የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስቴር እስከሆነ ድረስ ርምጃ መዉሰድ ነዉ፡፡ አለበለዚያ ሊገሉኝ ነበር በማለት እንዲሁም ማንነታቸዉን በግልጽ ባለማስቀመጥ በህዝቡ ዘንድ ብዥታ ይፈጥራል፡፡ ከዛም በላይ በሀገሪቱ የኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ ይኖረዋል፡፡ ኢንቨስተሮች ኮንፊደንስ አይኖራቸዉም፡፡ ዜጎች በኮንፊደንስ ወተዉ መግባት አይችሉም፡፡
4. ዶ/ር አብይ ሁሉም ሰዉ እንዲደግፈዉ የሚፈልግ ሰዉ ነዉ፡፡ ይህ ከኮንፊደንስ ጋር የተገናኘ ይመስለኛል፡፡ ደጋፊ አለዉ፡፡ ነቃፊ አለዉ፡፡ ከነቃፊዎቹ የሚማርበትን መዉሰድ፡፡ ከደጋፊዎቹም የሚማርበትን መዉሰድ ነዉ ያለበት፡፡ ነቃፊዎቹ በሱ ላይ የሰነዘሩትን እየተቀበለ ፓርላማ ድረስ ወስዶ የሚያወራ ከሆነ ያ የ statesman ባህሪ አይደለም፡፡ለትችት ስስ ቆዳ/Thin skin እንዳለዉ ያሳያል፡፡
5. ፓርላማ ላይ የግለሰቦችን ስም ማንሳትም ተገቢ መስሎ አይታየኝም፡፡ በዚህ ላይ በርግጥ እንደ ክፋት ባላየዉም ነገር ግን ከላይ እንዳልኩት ትልልቅ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ማተኮ አስፈላጊ ነዉ፡፡ የቢዝነስ ሰወችን እና የሚዲያ ሰወችን ለመሳሌ እነ አለምነህ ዋሴ ተብሎ የሚሰጥ ምሳሌ ትክክል አይመስለኝም፡፡ አንደኛ እኒህን ትቂት ሰወች endorse ማድረግ ነዉ፡፡ሁለተኛ እኒህ ግለሰቦች በስራቸዉ ተምሳሌት ለመሆናቸዉ ማረጋገጫ ማግኘት ያስፈልጋል፡፡ እነ አለምነህ ዋሴ ያልተረጋገጠ ወሬ እየለቀቀ ስንቴ ነዉ ያሳሳተን፡፡ አለምነህ ዋሴ ዶ/ር አብይን ከሌላ ፕላኔት እንደመጣ አድርጎ በተደጋጋሚ ስሎልናል፡፡ ዶ/ር አብይ በዚህ መድረክ ያሳየዉ የሚያንቆለፓፕሱትን ሰወች በማመስገን በሶሻል ሚዲያ ደግሞ ትክክል አይደለም የምንለዉን ለመኮርኮም ሞክሯል፡፡በነገራችን ላይ መማር የሚችለዉ ከሚነቅፉት ሰወች ነዉ፡፡ እኛ ወታደሮች የሄዱበት አግባብ በማንኛዉም መስፈርት ትክክል አይደለም ስንል ደጋፊዎቹ ዶ/ር አብይን እኮ ጭኮ ይዘዉ ሊጠይቁት ነዉ የሄዱት ያሉ ሰወች ናቸዉ፡፡ ከእነዚህ ምን እንደሚማር ጌታ ብቻ ነዉ የሚያዉቀዉ፡፡
6. የቡራዩ እና የሱሉልታ ገበሬ መንግስታችን ተነካ ብለዉ እየመጡ ነበር የሚለዉ የምላስ ወልምታ ይሆን ታቅዶበት ትክክለኛ አነጋገር አይደለም፡፡
7. ሀገር ልትበተን ነዉ እያሉ የድሮ ታክቲክ ይዞ መምጣትም ትክክል አይደለም፡፡ ግጭት፤ መፈናቀል፤ ሁከት አለ፡፡ እሱን መቆጣጠር ነዉ፡፡ አንድ መሪ ሀገር ትፈርሳለች የሚል አሉባልታ ከጀመረ እኔዉ ብቻ ነኝ ማድናት እንደማለት ነዉ፡፡
ባጠቃላይ ዶ/ር አብይ off script መናገር ከጀመረ የሚናገረዉ ነገር አንድምታዉ ምን እንደሆነ በወል የሚያጤን አይመስለኝም፡፡ ነገሮች አልከወን እያሉት ከሄዱ እና govern ማድረግ ካቃተዉ አብይ ወይ በደንብ ኦሮሞ ይሆናል ወይ በደንብ አምባገነን ይሆናል፡፡
Filed in: Amharic