>

የ-1972ቱ የኢትዮ-ሱዳን የድንበር ስምምነት ውል ምን ነበር? (አዳነ አጣ ነው)

የ-1972ቱ የኢትዮ-ሱዳን የድንበር ስምምነት ውል ምን ነበር?
አዳነ አጣ ነው
* ኢትዮጵያውያን እና ሱዳናዊያን እስከአሁን በይዞታቸው ስር የነበረውን መሬት ይሁን የእርሻ ይዞታ ይዘው እንዲቆዩ ሆኖ ለወደፊት የሁለቱ አገራት መንግስታት ድንበራቸውን በተመለከተ የየራሳቸውን ጥናት አካሄደው በሚደርሱት ስምምነት መሰረት የድንበር መካለል ይደረጋል የሚል ነበር፡፡ የ-1972 ስምምነት የሚባለው ውል ይህ ነው!
 
ስሞኑን የኢሀዴግ/ህወሀት ምክር ቤት የጋራ ስብሰባ ላይ ጠሚ አብይ አህመድ የኢትዮጵያ እና ሱዳን ድንበርን በሚመለከት  ከ1972 (እአአ) በኋላ የተፈረመ  የስምምነት ሰነድ አለመኖሩን ለምክር ቤቱ አሰረድተዋል፡፡ ጠሚ አብይ አህመድ አክለውም፣ የሁለቱ አገሮች ድንበርን በሚመለከት ከዚህ ከ1972 ስምምነት ውጭ የሚቀርብ ሰነድ ሆነ የስምምነት ፊርማ ተቀባይነት እንደማይኖረው አጽኖት ሰጥተው አስረድተዋል፡፡
ጠሚ አብይ አህመድ ከሱዳን ጋር ያለውን የድንበር ጉዳይ በተመለከት ይህ ለምክር ቤቱ ያደረጉት ንግግር ተክክል ነው፡፡ የጠ/ሚኒስትሩ በኢትዮ-ሱዳን ድንበር ዙሪያ የሰጡት ይህ የአቑም መግለጫ ንግግር፣  ትክክለ ባቻ ሳይሆን እሳቸው አሁን የሚመሩት የህወሀት/ኢህአዴግ የ27 አመታት ረጅም አገዛዝ ሲከተለው የነበረውን የሀገርን ጥቅም አሳልፎ የመስጠት ጠባሳ የክህደትታሪክን ቀርፎ ወደ ትክክለኛው የሀገር ጥቅም እና ልኡላይነት ወደ ሚያስጠብቅ መርህነት የተሸጋገረ መሆኑን ጠቕሚ ንግግር ነው፡፡
 ከአሁን በፊት ባለን ተመክሮ ኢሀአዴግ የሚባል የህወሀት መግዥያ መሳሪያ እንደ ድርጅት እስካለ ድረስ ጠሚ አብይ አህመድ ለምክር ቤቱ ያሰሙት ትክክል የሆነ ዲስኩር የመንግስት ፖሊሲ ሆኖ በስራ ላይ ይውላል ወይ? የተለመደ ጥርጣሬ አሁንም ቢሆን ስጋቱ እንዳለ መሆኑን ከወዲሁ መግለጹ አስፈላጊ ነው፡፡
ከአሁን በፊት በድህረ ገጾች እና በህብረተሰብ መገናኛ መረብ/Social Media and Web Sites በኩል በወያኔ እና በሱዳን መካከል የተደረሱ የስምምነት ሰነዶች እና ካርታዎች ለህዝብ እንዲደርሱ ለማድረግ ተመኩሯል፡፡ የወያኔ መንግስት ከሱዳን ጋር የተፈራረመው ብዙ የክህደት ሰነዶች አሉ፡፡ ኢትዮጵያን በመወከል ህወሀት ከሱዳንጋር ከተፈራረማቸው ብዙ ሰንዶች መሀከል በተለይ (1)  የሟቹ የመለስ ዜናዊ የብሄራዊ ጸጥታ አማካሪ የነበሩት በአቶ አባይ ጸህየ የተፈረመ የኢትዮጵያን ይዞታ ለሱዳን አሳልፎ የሚሰጥ የስምምነት ሰነድ (2) ይህንኑ የነአባይ ጸሀየ እና የሱዳን ባለስልጣናት መሀከል የተደረሰውን እና የተፈራረመውን ሰነድ ተግባር ላይ ለማዋል  በተለይ በደለሎ አካባቢ ለሱዳን የሚሰጠውን የእርሻ መሬት ተለይቶ በሁለቱ አገር የካርታ ባለሙያዎች የጓንግን ወንዝ ተሻግቶ የተሰራ ካርታ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
ሱዳን በአሁኑ ሰአት ምን እያደረገ ነው?፡፡ በአሁኑ ሰአት ከነብስ-ገበያ አስከ ታያ (ደቡብ መተማ) በሚያዋስነው የኢትዮጵያ ይዞታ ላይ ሱዳን 38 ኪሎ ሜትር ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ዘልቆ በመግባት ሰራዊቱን አስፍሮ የኢትዮጵያን መሬት ከመያዙም በላይ፣የአካባቢውን ደን በማውደም ከሰል በማምረት፣ የቀን ሰራተኞችን አድፍጦ መግደል እና የእርሻ ይዞታዎቹን እያስፋፋ ይገኛል፡፡በተለይ ውድ የሆነውን ቀርቃሀ/የበረሀ ሽመል እና የዱር እንሰሳት በሰፋት አውድሟል፡፡ እያወደመም ነው፡፡
ከላይ የተጠቀሰው እንዳለ ሆኖ ጠሚ አብይ አህመድ ፓርላማ ላይ ስለጠቀሱት የ1972 (እአአ) በኢትዮጵያ እና በሱዳን መሀከል የተደረሰው ስምምነት ውል ምን ነበር የሚለውን እንመልከት፡፡
ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ከጠቀሱት ከ-1972 የኢትዮ ሱዳን ውል በፊት በኢትዮጵያ እና በሱዳን መሀከል የነበረውን የፖለቲካ ግንኙነት መዳሰሱ የግድ ይላል፡፡ ከ-1972 በፊት ሁለቱም አገሮች ሱዳን እና ኢትዮጵያ በሁለቱም አገሮች ውስጥ የመገንጠል ጥያቄ ያነሱ አማጺያን ይንቀሳቀሱ ነበር፡፡ ሱዳን የኤርትራ ተገንጣዮችን ስትረዳ ኢትዮጵያ በብኩሏ የደቡብ ሱዳን አንያ-ኒያ/የእባብ-መርዝ የተባለ ጸረ ስሜን ሱዳን አገዛዝ ንቅናቄን ትረዳ ነበር፡፡ ባጭሩ በውቅቱ በኢትዮጵያ እና ሱዳን መሀከል ያለመተማመን ተፈጥሮ ሁለቱም መግስታት አንዱ የአንዱን ተገንጣይ ንቅናቄ/tit-for- tat መርሆ ተከትለው ይረዱ ነበር፡፡
ሱዳን በኢትዮጵያ የሚረዳው የደቡቡ ተቃዋሚ ንቅናቄ እየበረታ ሲመጣ በጊዜው የነበሩት የሱዳኑ መሪ ጃፈር መሀመድ ኑሜሪ አዲስ አበባን ለደቡብ የምትሰጠውን ድጋፍ እንድታቆም ለማስገደድ ሰራዊታቸውን ወደ ሁመራ አቅጣጫ ልጉዲ አካባቢ በ-1972 አዘመቱ፡፡ ሱዳን በዚሁ በ-1972 ድንበር ጥሶ ወደ ኢትዮጵያ ግዛት እንዲገባ ያደረገችው ጦር በልጉዲ አካባቢ ብቻ የተወሰነ ነበር፡፡አሁን እንደምታደርገው ከኦሚደላ/ጎጃም እስከ ልጉዲ ባለው የድንበር አክባቢን እንደ አሁኑ የሚያጠቃልል ጥያቄ አልነበራትም (ልግንዛቤ እንዲረዳ )፡፡
በወቅቱ በ-1972 የሱዳን ጦር ወደ ሉግዲ ዘልቆ መግባቱን ተከትሎ፣ አሁን ወያኔ-ትግሬ ስር የሚማቅቀው በተለይ፣ የወልቃይት ህዝብ፣የጠገዴ ህዝብ በአጠቃላይ ደግሞ የጎንደር ክፍለሀገር ህዝብ መሳሪያውን ወልውሎ የሱዳንን ተንኻሽ ጠብ-ጫሪነት ለመቀልበስ ለዘምቻ ተነሳ፡፡ህዝቡም በአንድ ድምጽ ፡ ለሱዳን እኛ ብቻ እንበቃለን የመንግስት ጦርን ድጋፍ አንሻም ሲል ህዝብ ከዳር እስከ ዳር ተነቃነቀ፡፡ በኢትዮጵያ ፓርላማ ውስጥ በጉዳዩ ብጥብጥ ተነሳ፡፡ህግ መወሰኛ ምክር ቤትም ውስጥ እነ አሞራው ውብነህ እንደ አምላክ የሚያቸውን ጃንሆይን “አንተ” ሲሉ ተቹ፡፡
ቀዳማዊ ሀይለስላሴ ግን ከአስመራ ወደ ሁመራ ጦር ኢዲመላለስ አዘዙ፡፡ህዝብ መንግስት ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ ምንም አይነት እርማጃ እንዳይወስድ ጥብቅ ትእዛዝ አስተላለፉ፡፡ ንጉሱ ጦሩ ወደ ሁመራ እና ወደ ጠረፍ አካባቢዎች ዝግጅቱን እንዳጠናቀቀ፣ ለሱዳኑ መሪ “ምን አየሰራችሁ ነው ያለው ሲሉ ለጀነራል ኑሜሪ መልእክት ላኩ”፡፡ ባጭሩ በንጉሱ እና በጀነራል ኑሜሪ መሀከል አሁን “የ1972 ስምምነት” የሚባል ስምምነት ተደረሰ፡፡
 ስምምነቱ እንዲህ ይላል፡ ኢትዮጵያውያን እና ሱዳናዊያን እስከአሁን በይዞታቸው ስር የነበረውን መሬት ይሁን የእርሻ ይዞታ ይዘው እንዲቆዩ ሆኖ ለወደፊት የሁለቱ አገራት መንግስታት ድንበራቸውን በተመለከተ የየራሳቸውን ጥናት አካሄደው በሚደርሱት ስምምነት መሰረት የድንበር መካለል ይደረጋል የሚል ነበር፡፡ የ-1972 ስምምነት የሚባለው ውል ይህ ነው፡፡ በዚህ ውል መሰረት ሱዳን ወደ ኢትዮጵያ ግዛት “ልጉዲ” የላከችውን ጦር አስወጣች፡፡የኢትዮጵያ ገበሬዎችም ብዙ ሳይቆዩ ይዞታቸውን እንደተለመደው ማረስ እና ጠረፋቸውን መጠበቅ ጀመሩ፡፡
ከ-1972 ስምምነት ውል በኻላ ሁለት መረታዊ የፖለቲካ እና የንግድ ክሰቶች በሁለቱ አገራት መሀከል ተከሰቱ፡፡ (1) ኢትዮጵያ በሱዳን ላይ የምትከተለውን መርሆ ቀይራ በደቡብ ሱዳን እና በስሜን ሱዳን መሀከል የነበረውን ጦርነት በስምምነት እንዲቆም አደረገች፡፡ በኢትዮጵያ አስታራቂነት በ-1972 “የአዲስ አበባ ስምምነት/Addis Abeba Agreemet”ተብሎ የተሰየመውን የሱዳን የእርስ በርስ ጦርነት ፍጻሜ እንዲያገኝ አደረገች፡፡
በዚህ ስምምነት መሰረት፣ የደቡብ ሱዳን በኩል የአማጺያኑ መሪ ጀነራል ጆሴፍ ላጉ አና የሱዳን መሪ ጀነራል ጃፈር መህመድ ኑሜሪ መሀከል ተፈረመ፡፡ይህ ስምምነት ደቡብ ሱዳን የራስ ገዝ አስተዳደር እንዲኖራት አደረገ፡፡ሱዳንም በብኩሏ የኤርትራ ተገንጣይ ሀይሎችን በግልፅ መደገፍዋን አቑረጠች፡፡
ሱዳን በ-1972 በተደረሰው ውል መሰረት የሁለቱም ዜጎች የያዙትን ይዞታ ይዘው ይቆዩ የሚለው ውል ከተፈረመ እና ብሎም የደቡብ እና ስሜን ሱዳን ጦርነት በኢትዮጵያ አስታራቂነት ከትቕጨ በኻላ የመሬት የይገባኛል ጥያቄ የትግሬ-ወያኔ አገዛዝ ስልጣን ላይ እስከ መጣ ድረስ አንስታ አታውቅም፡፡ (2) ሌላው ጉዳይ ንግድ በሁለቱ አገሮች መሀከል መልካም እንደምታ መፍጠር መጀመሩ፡፡ በኢትዮጵያ በልጉዲ ሁመራ እና በሱዳን “የዘመኑ ወርቅ” ተብሎ የሚታወቀው “የሙጫ/Arabic Gum” ንግድ ተጧጡፎ በሱዳን አና በኢትዮጵያውያን መሀከል የተለየ ወዳጅነት በመፍጠሩ ምክኒያት ሙሉ ሰላም ተፈጠረ፡፡
ወያኔ ኢትዮጵያን መግዛት ከጀምረ ጀምሮ ሱዳን እንደገና የመሬት ጥያቄ አነሳች፡፡ብዙ ኢትዮጵያውያንን ገደለች አፈናቀለች፡፡ ወያኔ በወረራ የያዘውን የሁመራ-ልጉዲ አካባቢ የትግራይ ስለሆነ የይገባኛል ጥያቄዋን አነሳች፡፡በምትኩ ሱዳን ወዳጄ የምትላትን ትግራይን በመተው ጠላቴ የምትለውን የኢትዮጵያን መሬት ወረረች፡፡ወያኔ-ትግሬ እና በረከት ሰሞኦን ሱዳንን አደነቁ፡፡ሱዳንን አትንኩብን አሉ፡፡
NB: በኢትዮ-ሱዳን ድንበርን በተመለከተ በተደጋጋሚ ከ1998 ጀምሮ በኢትዮጵያ ሪቬው, በሱዳን ትሪቡን፣ አዲስ ቮይስ ድህረ ገጾች ላይ በዚህ ጸሀፊ በሰፈው መጻፉ ይታወሳል፡፡
=====
ጠቅላዩ ” ከ1972ቱ ውል ውጭ የተፈረመ ሰነፍ የለም” ይበሉ እንጂ – የትግራይ-ወያኔ እና የሱዳን መንግስት በሚስጥር የተፈራረሙበት የድንበር ካርታ  በማስረጃ ተያይዞ ቀርቧል
=====
የወያኔ ወንጀል፣ የወያኔ ክህደት፣ የወያኔ ጸረ ኢትዮጵያዊነት በምን ይለካል?፡
ወያኔ ጸረ ኢትዮጵያ ነው ስንል ወያኔዎች እንደሚሉት የአይናቸው ቀለም ከእኛ ስለተለየ አይደለም፡፡እኛ የምንጠላቸው በዋናነት ወያኔዎች አበክረው በኢትዮጵያ ጥቅም ላይ ሲያሴሩ፣ ኢትዮጵያዊነትን ሲዋጉ፣ ለባእዳን አጎብዳጅ ሆነው ከሀገር ይልቅ የውጭን አገራት ጥቅም ለማስጠበቅ ሲሯሯጡ ስለምናይ እና ማረጋገጫ ስላለን ነው፡፡
ከዚህ በታች  የሚታየው ካርታ በወያኔዎች እና በሱዳን መንግስት መሀከል የኢትዮጵያን መሬት ለሱዳን አሳልፎ ለማስረከብ በካርታ ተነድፎ በስምምነት ደረጃ ጸድቆ የተፈራረሙበት ሰነድ ነው፡፡ይህ ማፕ ከመተማ ስሜን እና  በአብደራፊ መሀከል ጙንግን ተከትሎ በከፊል የታረሰ፣ ቀሪው ደግሞ በደን የተሸፈነ ለም የኢትዮጵያ የእርሻ መሬት ነው፡፡
ይህ ማፕ በእያንዳንዱ አቅጣጫ ሱዳን ምን ያህል ወደ የኢትዮጵታ ይዞታ ዘልቃ ገብታ በሜትር እና በኪሎሜትር ሳይቀር የሚሰጣትን ለም መሬት ግልጽ ባለ መልኩ የሚያሳይ ነው፡፡ ይህ  ውል መሬት ብቻ ሳይሆን  የጙንግን ውሀ እና ወንዝ ለሱዳን አሳልፎ የሚሰጥ ነው፡፡በዚህ ስነድ ላይ የፈረሙት ፡-
በኢትዮጵያ በኩል
(1) ጌታቸው ተክለጻድቅ
(2) ውሂብ ሙሉጌታ
በሱዳን በኩል
ሳልህ አዋድ  (የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ወኪል)
Filed in: Amharic