>
6:22 pm - Wednesday November 30, 2022

አባቱ ዳኛ ልጁ ቀማኛ! (ቹቹ አለባቸው)

አባቱ ዳኛ ልጁ ቀማኛ!
ቹቹ አለባቸው
ይች የፌደሬሽን ም/ቤት አፈ ጉባኤ-ክብርት ወ/ሮ ኬሪያ የምትባል፤ሴት ደግሞ ምን እያለች ነው? እኒህ ወ/ሮ የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈጉባኤ በዛሬው ምሽት፤ በሰጡት መግለጫ፤ የወልቃይትና ራያ የማንነት ጥያቄ መቅረብ ያለበት ለትግራይ ክልል ነው ሲሉ ሰማኃቸው ።ሆኖም እነዚህ ወገኖች፤የትግራይ ክልል መንገስት የሚሰጣቸው መልስ፤ካለራካቸው ብቻ ነው፤ ቀጥሎ ላለው የመንግስት አካል(የፌደሬሽን ም/ቤት) ይግባኝ ማቅረብ የሚቻለው ብለውናል ።አይ ወ/ሮዋ፤የህጉንና ሂደቱን ነገር እንኳን ለኛ ለማስተማር ባልደከሙ ጥሩ ነበር፡፡ የኛ ችግር መቸ፤ህጉንና ሂደቱን አለማወቅ ሆነና፤የተቸገርነው እኮ “አባቱ ዳኛ ልጁ ቀማኛ” ሆኖብን ነው፡፡ሕወሀት የራያንና ወልቃይትን አማራዎች ማንነት፤ በኃይል ያፍናል፤የተቋቋመውን ኮሚቴ ህጋዊ አይደለህም ብሎ ያስረዋል፤ይገድለዋል፤ደብዛውን ያጠፋዋል፡፡ ከዚህ ሁሉ መከራ ተርፈው፤ጉዳዩን ለፌደሬሽን ም/ቤት የሚያቀርቡ አካላት ሲኖሩ ደግሞ፤ቂሊንጦ ላይ ተጠልፈው ይታሰራሉ፤ ያለበለዝያም፤ እርስዎ የሚመሩት መ/ቤት፤ጥያቂያችሁ ህጉን አልተከተለምና አልተቀበልነውም ይላቸዋል፡፡ ታድያ ህወሀትና የፌሰሬሽን ም/ቤት እንዲህ ተናበው፤የራያንና ወልቃይትን የማንነት ጥያቄ፤በተቀናጀ መልኩ በሚያፍኑበት ወቅት፤እንዴት አይነት ስርአትና ህግ እንድናከብር ነው የሚነገረን?
ክብርት አፈጉባያችን፤ ስለ እውነት፤የወልቃይት ኮሚቴ፤የትግራይ  መንግስት ቀርቶ፤አ/አበባ ለፌዴሬሽን ም/ ቤት፤ቅሬታ ለማቅረብ በሄዱበት ወቅት፤በርስዎ ድርጅት አፋኝ ቡድን መታፈናቸውን / መታሠራቸውን ሣያውቁ ቀርተው ይሆን? ቅድሚያ የትግራይን መንግስት፤ጠይቁ የሚሉን?። የትግራይ መንገስትማ ወንብዶ መስሎኝ፡፡ በወልቃይትና እራያ አትምጡብኝ ብሎ ካሰናበተን እኮ ከራረመ፡፡ ይሄን ቅሬታ ይዘን ወደ እርስዎ ቢሮ ስንመጣ ደግሞ፤ የሚሉንና ያሉንን ስማነወት፡፡ ስለሆነም፤ከታች ህወሀት፤ከላይ እርስዎ  እያሉ፤የራያና ወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ ይፈታል ብለን አናምንምና፤ጫናው ሳይበዛበዎት ጥግወን ቢይዙ፤ወገናዊ ምክሬን እለግስወታለሁ፡፡ይሄን ጉዳይ አይችሉትም፡፡
ከዛሬው ንግራቸው እንደተገነዘብኩት፤ወ/ሮዋ ነገረኛ ሳይሆኑ አይቀሩም፡፡ ይሄውም፤ እግረ መንገዳቸውን፤ የማንነተ ጥያቄውን አስታከው፤ የአማራን ክልል መንግስትና አዴፓን፤ በነገር ሸንቆጥ ያደረጉበት አነጋገር አሳዛኝ ብቻ ሣይሆን፤ ለህዝቡ ጥያቄ፤ ምላሻቸው ምን እንደሆነ ግልጽ ማሳያ ሆኖ አግኝቸዋለሁ፤።ለነገሩ መግለጫ ባይሠጡም ምላሻቸው ሊሆን የሚችለው፤ያው የህወሃት መግለጫ ነው ። ነገር ግን ቢያንስ በገለልተኝነት አገልግሎት እንዲሰጡበት የተመደቡበትን መ/ቤት፤እንዲህ በግላጭ፤ለህወሀት ፍላጎት ማስፈጸሚያ ሲያውሉት ስንመለከት፤የሴቱየዋን ለቦታው አይመጥኔነት እንድነገነዘብ አደረገን፡፡
ራያና ወልቃይት፡-
የወልቃይት አማራ ማንነት ጥያቄ፤ከራያው ቀደም ብሎ የተጀመረ መሆኑ ይታወቃል፡፡ እውነት ነው፤የወልቃይት ጉዳይ መላ አማራን አነቃቅቶ፤ የአማራን አብዮትም ወደ ከፍተኛ ደረጃ አድርሶታል፡፡ ይሁን እንጅ፤የወልቃይትን ትግል፤በቅርቡ በግልጽ ከተቀጣጠለው የራያ እንቅስቃሴ አንጻር ስመለከተው፤ ራያ ከወልቃይትና ጠገዴ ቀድሞ፤ነጻ የሚወጣ የአማራ አካባቢ እንደሚሆን እገምታለሁ፡፡እኔ የምመርጠው ግን ፤የሁለቱ አማራዎች አካባቢዎች ትግል፤በህጋዊና ሰላማዊ መንገድ ሆኖ፤በተቀናጀና በተናበበ መልኩ ቢካሄድና፤ ነጻነታቸውንም፤ባንድ ወቅት ቢቀናጁ ነው፡፡ያለ በለዝያ የሁለቱ አካባቢዎች ህዝባዊ ንቅናቄ በተናጠል የሚካሄድ ከሆነ፤ለህወሀት ፋታ መስጠት ነው፡፡ ስለሆነም፤ለህወሀት የሚቀርበው ህጋዊ ጥያቄ፤የተናበበና የተቀናጀ፤ግን ደግሞ ፍጹም ህጋዊና ሰላማዊ የትግል አግባብን በተከተለ መንገድ ቢሆን እመርጣለሁ፡፡
መንጋ እንቅልፉምና ሃሰበ ድውያን ተመልምለው ከተሰየሙበት ሸንጎ ምን የተሻለ ነገር ሊገኝ?
ኅ/ገብርኤል አያሌው
 
አልሰሜን ግባ በለው ይላል ሕዝባችን ሲተርት:: ክብርት አፈጉባዔ የሕግና የዲሞክራሲያዊ አካሄድ ትንተና በማቅረብ ነገሩን እያምታቱ ነው:: ወይ አልገባቸውም አለያም መረጃ የላቸውም:: ሌላው ቢቀር የወልቃይት ኮሚቴ ሕግን ተከትሎ የሄደበት መንገድ ከየት ተነስቶ የት እንደደረሰ የማያውቅ ኢትዮጵያዊ አለ ለማለት ይከብዳል:: የትግራይ ክልል አላቃችሁም ከማለት አልፎ አዲስ አበባ ፌዴሬሽን ም/ቤት ይግባኝ ለማለት የመጡትን ወደ ከተማ እንዳይገቡ ጫንጮ ላይ አግዶ በስንት ድርድር ጥያቄያቸውን ትተው ወደ መጡበት እንዲመለሱ የተረገውን ኢፍትሃዊ እርምጃ አፈጉባኤዋም ሆኑ ምክር ቤቱ ካላወቁ የሚያሳፍር ነው:: በዚህ ብቻም አላበቃም የወልቃይት ኮሚቴ አባሎችን በማፈን ትግራይ ውስጥ እንዲታሰሩ ተደርጏል:: በጎንደርም በኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን በሌሊት አፍነው እንዲወስዱ የተላኩትን ቅልብ የአጋዚ ወታደሮች ጀግናው ደምስሶ የፖለቲካውን ግለት ከፍ ማድረጉንም አያውቁም:: ለነገሩ መንጋ እንቅልፉምና ሃሰበ ድውያን ተመልምለው የተሰየሙበት ሸንጎ ምን የተሻለ ነገር ሊገኝ:: በፍትሕና በዲሞክራሲ ስም የሕዝብን ስቃይ ማርዘም:: መፍትሄው ሌላ ነው የሚያውቅ ያውቀዋል:: ደግሞም እሩቅ አይደለም:: በቅርቡ ይሆናል::
Filed in: Amharic