>

ወያኔ በሀረርጌ ህዝብ ላይ የፈጸማቸው የኢኮኖሚ ደባዎች (አፈንዲ ሙተቂ)

ወያኔ በሀረርጌ ህዝብ ላይ የፈጸማቸው የኢኮኖሚ ደባዎች
አፈንዲ ሙተቂ
የኢህአዴግ መንግስት ለ27 ዓመታት በቆየው አገዛዙ በመላው የሀገራችን ህዝቦች ላይ ከባድ ሸፍጥና ጭቆና ሲያካሄድ መቆየቱ ይታወሳል። ይሁን እንጂ ጠንከር ያለ ህዝባዊ ተቃውሞ በሚታይባቸው ክልሎችና ዞኖች ላይ ሲፈጽመው የነበረው ደባ ፈርጀ ብዙ ነበር።
ከጅምሩ አንስቶ ጨቋኙን የኢህአዴግ አገዛዝ ከተጋፈጡት ማህበረሰቦች አንዱ የሀረርጌ ህዝብ ነው። ኢህአዴግም የህዝቡን ተቃውሞ ለማፈን በሚል በሀረርጌ ላይ መጠነ ሰፊ ዘመቻ አካሄዷል።
ኢህአዴግ በሀረርጌ ላይ  ያካሄደው ዘመቻ ዓይነተኛ መገለጫው የኢኮኖሚ ጭቆና ነው። በሀረርጌ ላይ የተካሄደው የኢኮኖሚ ጭቆና ደግሞ የሚከተሉትን ህገ ወጥ እርምጃዎች ያካተተ ነው።
1 “የመጀመሪያ ደረጃ የተቃውሞ ማዕከል ናት” ተብላ የተፈረጀችውን የድሬ ዳዋ ከተማን የንግድ እንቅስቃሴ በተለያዩ ዘዴዎች ማዳከም (ለምሳሌ ከተማዋን ከባቡርና ከአውራ ጎዳና መቁረጥ፣ በሀርቲሼክ መስመር ከባድ የኮንትሮባንድ መስመር በመክፈት የነጋዴዎች ትኩረት ወደዚያ እንዲሆን ማድረግ፣ የከተማዋ የኢኮኖሚ እስትንፋስ የሆኑ ፋብሪካዎችን ያለበቂ ምክንያት በመሸጥ ሰራተኞችን መበተን፣ ኢንቨስተሮችንና ነጋዴዎችን እያጉላሉ ከከተማዋ እንዲሰደዱ ማድረግ ወዘተ)
2 የሁለተኛ ደረጃ የተቃውሞ ጣቢያዎች ተብለው በተፈረጁት ከተሞች (ገለምሶ፣ ጉርሱም፣ ደደር) ደግሞ ነጋዴዎችን በኦነግ ስም በማሸበር መግደል፣ ማሰር፣ ከሀገር ማባረር፣ ንብረታቸውን መዝረፍ፣
3 በመላው የሀረርጌ ከተሞች የሃይል አቅርቦት እጥረት እንዲከሰት በማድረግ ፋብሪካዎችና ኢንዱስትሪዎች እንዳይበለፅጉ ማወክ (ለምሳሌ የገለምሶ ከተማ በ27 ዓመታት ውስጥ ለሶስት ተከታታይ ቀናት ኤሌክትሪክ አይበራላትም ነበር። ካለፈው የሚያዚያ ወር ጀምሮ ግን ይህ ችግር ተወግዷል)።
4 በነዚሁ ከተሞች ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በስተቀር ሌሎች ባንኮች ቅርንጫፋቸውን እንዳይከፍቱ መከልከል
5 በሀረርጌ ከተሞች የንግድና ኢንዱስትሪ የአክሲዮን ማህበሮች እንዳይመሠረቱ በልዩ ልዩ ዘዴዎች መከልከል፣ የተመሠረቱትን ማህበራት ደግሞ በኦነግ ደጋፊነት ማዋከብ፣ ንብረታቸውን መዝረፍ፣ መስራች ነጋዴዎችን ማዋከብ፣ ከሀገር ማባረር፣
6 በዓለም ዙሪያ የተደነቀውን የሀረርጌ ቡና CBD በተባለ በሽታ በክሎ ማጥፋት፣ ከበሽታው የተረፈውን የወያኔ ደጋፊ የሆኑ ነጋዴዎች ብቻ እንዲራኮቱበት ማድረግ
7 በደርግ ዘመን በኔዘርላንድ መንግስት ድጋፍ ተቋቁመው የነበሩ ሰፋፊ የቡና ማሻሻያ ፕሮጀክቶችን መዝጋት፣ ንብረታቸውን መመዝበር
8 በተመሳሳይ ሁኔታ ሀረርጌ የምትታወቅበትን አትክልትና ፍራፍሬ በበሽታ በመበከል ማጥፋት
9 በሀረርጌ ምድር ዘመናዊ መስኖዎች እንዳይሰሩ በጀት  በመከልከል ክልሉ ለተደጋጋሚ የድርቅ አደጋ እንዲጋለጥ ማድረግ
10 በመጨረሻው ሰዓት ደግሞ Ethio-Flora የተባለ ምንነቱ ያልታወቀ ግዙፍ ኩባኒያ ወደ ሀረርጌ እንዲመጣ በመጋበዝ የአካባቢውን bio-diversity የሚበክሉ ኬሚካሎችን እንዲጠቀም ፈቅዶ የተፈጥሮ ምህዳሩን እንዲያበላሽ ማሰመራት
11 ከጥንት ጀምሮ በትርፍ አምራችነቱ የሚታወቀው የሀረርጌ ገበሬ በጫት ምርት ላይ ብቻ እንዲያተኩር በመገፋፋት ከእህል አምራችነት ወርዶ እህል ሸማች እንዲሆን ማድረግ
12 የሀረርጌ ከተሞችን በአስፋልት መንገዶች ለማገናኘት የወጡ እቅዶችን በረቀቀ ዘዴ እንዳይተገበሩ በማድረግ ንግድና ኢንቨስትመንትን ማዳከም
13 በደርግ ዘመን ተከልለው የነበሩ ሰፋፊ የተፈጥሮ ደን ክልሎችን በመውረር ለወያኔ ሰራዊት የጣውላና የማገዶ ፍጆታ እንዲውሉ ማድረግ፣ በዚህም የአየር ሁኔታንና የዝናብ ሽፋንን ማዛባት
14 ሀረርጌ በኮንትሮባንድ ንግድ እንዲወረር በማድረግ ክልሉን ለህገ ወጥ ነጋዴዎች መናኸሪያነት መዳረግ
—-
እያንዳንዱ ነጥብ ቢዘረዘር በየራሱ መጽሐፍ ሊወጣው ይቸላል። ወደፊት በስፋት የምናየው ይሆናል።
Filed in: Amharic