>

የኦሮሚያ ክልል መንግስት የአቋም መግለጫ፦ (ቃል በቃል የተተረጓመ) 

የኦሮሚያ ክልል መንግስት የአቋም መግለጫ(ቃል በቃል የተተረጓመ) 
ዳዊት እንደሻው
በአሁን ሰአት በአንድ አንድ የኦሮሚያ  አካባቢዎች እየተደረገ ያለው እና ለማድረግ እየታሰበ ያለው ሰልፍ ከጥቅሙ ጉዳቱ ስለሚበልጥ ለጠላት ሰፊ አጋጣሚ ይፈጥራል!!
 የመደማመጥ እና የመረዳዳት ባህላችንን አጎልብተን ማጣጣም የጀመርነውን አሸናፊነት እናጠናክር። የኦሮሞ ህዝብ ለረጅም አመታት ለመብቱ ተከራክሮ መስዋእት ሆኖ መብት አጥቶ ለልማቱ ደክሞ ደሃ ሆኖ ጥያቄው ተቀባይነት አጥቶ  ነበር።
ይሁን እንጂ በተደረገው መራራ ትግል ጥያቄው ሁሉ ተሰምቶ ማንነቱ ተከብሮ መብቱ ተጠብቆ ከራሱ አልፎ ለሃገር የሚጠቅም እንደሆነ በተጨባጭ እያሳየ ነው። ሊፈቱ የሚገቡ የፖለቲካ ፣ ኢኮኖሚ  የማህበራዊ ጥያቄዎች እና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ከስር ከስር እንዲፍቱ ስምምነት ተደርሶ እየተሰራ ነው።
የኦሮሚያ ክልል መንግስት የፖለቲካ ሜዳውን በማስፋት የኦሮሞ ህዝብ ትግልን ወደፊት ለማሻገር በውይይት እየተሰራ ባለው ስራ መሰረት በኢኮኖሚ ረገድ የሚታየውን ችግር ለመፍታት የተለያዩ ድርጅቶችን በማዋቀር እየተሰራ ነው። የመልካም አስተዳደር ችግር ለመፍታትም ከላይ እስከ ታች አሰራሩን እያስተካከለ ሲሆን ለህዝብ ተቆርቆዋሪ የሆኑ በተለይ ሴት አመራሮችን ወደ ስልጣን በማምጣት እንደ ሃገርም ሆነ እንደ ክልል ምሳሌ የሚሆን ስራ እየተሰራ ነው።
በአጭር ጊዜ ብዙ ነገር እየተሰራ ነው የኦሮሚያ ክልል መንግስትም የትኛውንም ችግር በሰላም እና በመረጋጋት ለመፍታት እየሰራ ነው።  ሰላም እና የህግ የበላይነት አለመከበር ችግር ጋር ተያይዞ የዜጎች መፈናቀል፣ ዝርፊያ እና ሌሎችን በዘላቂነት ለመፍታት የኦሮሚያ ክልል መንግስት እንደ ከዚህ ቀደሙ አሁንም የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ከወጣቶች/ቄሮ ጋር እየሰራ ነው አሁንም ይሰራል።
ህዝብን የሚጠቅም ስራ እየተሰራ ባለበት ጊዜ ደግሞ ጥቅማቸው የተነካባቸው አካላት ሌት ተቀን እየሰሩ እንደሆኑ መታወቅ አለበት።
 በአሁን ሰአት በአንድ አንድ የኦሮሚያ  አካባቢዎች እየተደረገ ያለው እና ለማድረግ እየታሰበ ያለው ሰልፍ ከጥቅሙ ጉዳቱ ስለሚበልጥ ለጠላት ሰፊ አጋጣሚ ይፈጥራል።
ይሄን ለማስቆም ደግሞ ወጣቶች-ቄሮ ሰላማቸውን ለመጠበቅ አካባቢያቸውን በመጠበቅ ከመንግስት ጋር መስራት አለባቸው። አሁን ጊዜው ተደማምጠን አብረን ለመስራት አንድነታችንን የምናጠናክርበት ጊዜ ነው።
አሁን የኦሮሚያ ክልልን የሚያስተዳድር መንግስት ብቻ ሳይሆን የሀገሪቶ መንግስት ሆኖ ኢትዮጵያን የሚያስተዳድር ሃይል እና ወደ ትክክለኛ ዲሞክራሲ ለማሸጋገር ሃላፊነት ያለው ነው።
 ህዝባችንም ይሄን ተረድቶ በትእግስት እና በመረጋጋት ተደማምጦ ችግር ባለበት ቦታ ሁሉ አባ ገዳዎች፣ ሀገር ሽማግሌዎች፣ምሁራን እና አመራሮች ሁሉ አብረው ሊሰሩ ይገባል። መንግስትንም በመደገፍ የተጀመረው ለውጥ እንዳይደናቀፍ እንድትሰሩ የኦሮሚያ ክልል መንግስት ጥሪ ያቀርባል።
Filed in: Amharic