>
8:07 am - Tuesday December 6, 2022

የአየር መንገዱ ሀላፊ ባይነሱም እንዲነሱ እንጠይቃለን!!!  (ቹቹ አለባቸው)

የአየር መንገዱ ሀላፊ ባይነሱም እንዲነሱ እንጠይቃለን!!!
ቹቹ አለባቸው
ዛሬ ከስአት በኃላ፤የአር መንገዱ ሀላፊ አቶ ተወልደ ከስራቸው ታገዱ የሚል ወሬ ሲሰራጭ ውሎ ነበር፡፡ ሰዎችም፤በውስጥ መስመር፤ፋና ያስተላለፈው ሰበር ዜና ነው በማለት፤ዜናውን በውስጥ መስመር ሲልኩልኝ ውለዋል፡፡ አንዳንዶቹ እውነት ነው በሚል፤አንዳንዶቹ ደግሞ አረጋግጥልን በሚል፡፡፡ እኔም ፋና ላይ ሳየው ዜናው አለ፡፡ ቆይቶ እንደሰማሁት ግን ፋና ሀክ ተደርጎ ነው እንጅ ነገሩ እውነት አይደለም የሚል ነገር መጣ፡ ለማንኛውም ባይነሱም ሊነሱ ይገባል ያስባሉኝን ነጥቦች በጥቂቱ ቆንጠር አድርጌ ላስነብባችሁ:-
አቶ ተወልደ፤(የዛሬው ወሬካለፋቸው)፤ ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ ሚያደርጓቸው በርካታ ምክንያቶች አሉ፡፡ ሌሎች ነገሮች ሳይከተሏቸው፤በራሳቸው ፈቃድ፤ ከነ ክብራቸው በራሳቸው ፍቃድ ስልጣናቸውን፤ቶሎ ቢለቁ ይሻላል በሚል ፤ወገናዊ ምክራችንን እንለግሳቸዋለን፡፡
ሉፍታንዛና ዶላራችን/ወርቃችን!
ለሁሉም፤ቢያንስ ካሁን በኃላ፤አየር መንገዳችን በአዲስ መንፈስ ሊመራ ይገባል፡፡ ግን- ግን፤ዶ/ር አብይ ሊያጣሩት የሚገባ ነገር አለ፡፡ ይሄውም፤በ2008 ዓ.ም የተቀሰቀሰውን አገር አቀፍ አመጽ ተከትሎ፤ዶ/ር አብይ ወደ ስልጣን እስከመጡበት ጊዜ ድረስ፤ ማታ ማታ፤በማይታወቁ ሰዎች እየታጀበ፤በኮንቴነር የታሸገ እቃ፤ ያለምንም ፍተሻ ወደ አየር መንገድ እንዲገባ ከተደረገ በኃላ፤ በጀርመኑ ሉፍታንዛ አየር መንገድ ተጭኖ የሚሄድ የሆነ ነገር ነበር አሉ፡፡ ይሄ ነገር ምን ይሆን? ዶላር ወይስ ወርቅ? እስኪ ዶክተራችን ይችን ነገር ያስመርምሯት፡፡ በርግጥ የአገሪቱ ዶላር፤በተለያየ መንገድ ሲሸሽ እንደኖረ ነግረውናል፡፡ እንዴው፤ሰሞኑን ወደ ጀርመን አገር እንደሚያቀኑ ስለሰማሁ፤እግረ መንገድዎትን የሉፍታንዛን ነገር እንዲመለከቱት ብየ እንጅ፡፡ ይሄ አየር መንገድ እኮ፤አየር መንገድ መስሎ ሲያስቦጠቡጠን ከረመ፡፡ይሄ ሁሉ ሲሰራ የኖረው፤አቶ ተወልደ አየር መንገዱን እየመሩ ባለበት ወቅት ነው፡፡
 የ Main Gate (ዋና በር) እና የስምንቱ (8) ቁጥር በሮች ይጠበቁልን!
እንግዲህ የአገራችን ሀብት፤ያላግባብ ሲወጣም ሆነ ሲገባ የኖረው በነዚህ ሁለት በሮች ስለመሆኑ አስተማማኝ መረጃ አለኝ፡፡ በነዚህ በሮች የሚገባና የሚወጣ ሰው፤ፍተሻ ብሎ ነገር አይመለከተውም፡፡ ስለሆነም፤የፈለገውን ነገር (በኮንትሮ ባንድ የሚወጡና የሚገቡ እቃዎች) ይዞ መውጣትና መግባት ይችላል ማለት ነው፤ማን ይጠይቀዋል፡፡ ሰለነዚህ በሮች አንድ አየር መንገድ ውስጥ የሚሰራ ወዳጀ፤ጥሩ አድርጎ አመላክቶኛል፡፡ በነዚህ በሮች ስንቱ ሰው ከብሯል መሰለህ አለኝ፡፡ በነዚህ በሮች የመውጣትና መግባት እድሉ ካለህ፤ባንድ አመት አላሙዲንን መሆንህ ነው ሲል አሳቀኝ፡፡እንግዲህ በነዚህ በሮች የሚገኘውን ጥቅም እነማን እንደሚቋደሱት ደግሞ ታውቆ ያደረ ነው፡፡ የህወሀት ሰዎች ይችን በር በጣም ይወዷታል አሉ፤እንዴውም፤ይሄው ወዳጀ እንዳጫወተኝ፤እነዚህ ወገኖች፤እንደሰባራ ውሻ፤በዝች አካባቢ አይርቁም ብሎኛል፤ ምክንያቱም፤ከወጭና ገቢው እነሱም ድርሻ አላቸውና፡፡
ብቻ አሁንም ዶ/ር አብይ አደራህን፤የእነዚህን ሁለት በሮች ነገር አደራ፡፡ ለዚህ ችግር መባባስ፤ትልቅ አስተዋጽኦ እያደረገ የኖረው፤የአየር መንገዱ የደህንነት ጥበቃ፤ በዋነኛነት በህወሀት የደህንነት ሰዎች መወረሩ ነው አሉ፡፡ ስለሆነም፤ዶ/ር አብይ ይሄንን ሁኔታ በቶሎ ቢቀይሩት ጥሩ ነው፡፡ ህወሀታዊያን በአየር መንገዱ የሚኖራቸው ድርሻ፤ከህዝባቸው ቁጥር ተመጣጣኝ እንዲሆን ቢደረግ ጥሩ ነው፤አሁን ግን መረጃዎች እንደሚያሳዩት፤እነዚህ ወገኖች ተቋሙን ወረውታል፡፡ ከዚያ ውጭ እነ አቶ ተወልደ ቢባረሩ እንኳን(መባረራቸው አይቀርም)፤ እነ አቶ ተወልደን በማባረር ብቻ፤ የከረመውን የአየር መንገድ፤በሽታ ማከም የሚቻል አልመሰለኝም፡፡ ስለሆነም፤በአየር መንገድ ውስጥ የሚካሄደው የማጥራት ስራ፤ እነ ተወልደን ማእከል ማድረጉ እንደተተበቀ ሆኖ፤ተጠናክሮ መቀጠል አለበት፤እኛም መረጃ ሞልቶናል፤ እናቀርባለን፡፡
የመቀሌ ባች (Mekele’s Crew) ነገር!
በአንድ ወቅት፤ ጉዞየን ወደ ባ/ዳር በአየር መንገድ ለማድረግ፤አየር መንገድ ቀድሜ ተገኝቸ፤ከዚያ ወዳጀ ጋር ጨዋታችንን እንነከዋለን፡፡ በዚህ መካከል፤ ቁጥራቸው ወደ አምስት(5) የሚሆኑ፤”ሸጋ ፤ሸጋ ወጣት ሴቶች፤ ሻንጣቸውን እየጎተቱ፤ ወገባቸውን እያውረገረጉ፤ ጫማቸውን ቋ-ቋ-ቋ እያደረጉ አልፈውን፤ ወደ ውስጥ  እየገቡ እያለ፤ ያ ወዳጀ፤ እነዚህን ልጆች ተመልተከታቸው፤ ተመልከታቸው፤ተመልከታቸው፤ አለኝ፡፡ እኔም አይኔን ሳልሞላ፤ከአይኔ እስኪርቁ ድረስ በአይኔ ተከተልኳቸው፡፡ ልጆቹ ካይናችን ሲርቁ፤ምንድን ነው ነገሩ? ስል ያን ወዳጀን ጠየቅኩት፡፡ እሱም የመቀሌ ባቾች (Mekele’s Crews) ናቸው አለኝ፡፡ አሁንም አልገባኝምና፤ ምን ማለት ነው? ስል አዙሬ ጠየቅኩት፡፡ ወዳጀም፤እዚህ አየር መንገድ ውስጥ አስተናጋጅ( Hosts) የሚባል ነገር አለ፡፡ በዚህ ስራ መስክ የሚሰማሩት ደግሞ በአብዛኛው ( ሙሉ በሙሉ)፤” ቆንጆ-ቆንጆ” ሴት ወጣቶች ተመርጠው ነው፡፡ እነዚህ ሴት ልጆች የዚሁ ዘርፍ ሰራተኞች ሲሆኑ፤ ሰልጠና የተሰጣቸው ለብቻቸው መቀሌ ውስጥ ስለሆነ፤ይሄን ሁኔታ ለመግለጽ ፤ሌሎች የተቋሙ ሰራተኞች “የመቀሌ ባች” እያሉ እንደሚጠቋቆሙባቸው ወዳጀ አጫወተኝ፡፡ ይሄ ወዳጀ ጨምሮ እንደነገረኝ፤ እነዚህ “የመቀሌ ባች” በመባል የሚታወቁት ልጆች፤መለያቸው፤ በመታወቂያ ቁጥራቸው( ID No.)፡፡
ነገሩ አሳዛኝም፤ አስቂኝም ነው፡፡ ህሀወት የበላይነቱን በአየር መንገድ ውስጥ፤ እነ ተወልደን በመጠቀም፤የአስተናጋጆችን ቦታ ሳይቀር እንኳን፤በሱ ሰዎች እንዲሞሉ ሲያደርግ ከርሟል፡፡ ክፉ በሽታ!
Filed in: Amharic